የጥናት ግብዓት መረጃ ስለመጠየቅ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ በዓለም ዐቀፍ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ከሚሠራቸው ሥራዎች መካከል ቀዳሚ የሆነው ሥርዓተ ትምህርት (Curriculum) የተቀረጸለት ወጥ ትምህርት ለተተኪው ትውልድ ማዳረስ እንደኾነ ይታወቃል፡፡ ይኽም ዕውን ይኾን ዘንድ ለብዙ ዓመታት ሙከራ ሲደረግበት የቆየው የሰንበት ትምህርት ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት በአኹኑ ጊዜ በብዙ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡
ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከሚሠሩ ሥራዎች መካከል በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር በሥራ እና በኑሮ ምክንያት በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ተገኝተው መማር ለማይችሉ እና ቤተ ክርስቲያን ባልተመሠረተችባቸው ሀገሮች ለሚኖሩ ኦርቶዶክሳውያን ትምህርቱን ተደራሽ ለማድረግ የቨርችዋል እና የርቀት ትምህርት ሥርዓት በማዘጋጀት ላይ በመሆኑ ለዝግጅቱ ተጨማሪ ግብዓቶችን ለመሰብሰብ ይረዳ ዘንድ ይኽን መጠይቅ ማዘጋጀት አስፈላጊ ኾኖ ተገኝቷል። ስለዚኽ በግል፣ በቤተሰብና እና በጽዋ ማኅበር በኩል የትምህርቱን አገልግሎት ማግኘት የምትፈልጉ ኹሉ ቀጥሎ በቀረበው ቅጽ መሠረት መረጃችሁን እንድትልኩልን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡