ከ8ኛ-10ኛ ክፍል ያሉ የዜማ እና መዝሙር መማሪያ መጻሕፍት ተለቀቁ

በሥርዓተ ትምህርቱ መሠረት የዜማና መዝሙር ትምህርት ከቅድመ መደበኛ እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ ከግዕዝ ትምህርት ጋር አብሮ  የሚሰጥ መሆኑ ይታወቃል።

በመሆኑም ከቅድመ መደበኛ እስከ 4ኛ በመጽሐፉ ተካቶ የታተመ ሲሆን፣ ከ5ኛ – 7ኛ ክፍልም በኹለተኛው የማስተካከያ ኅትመት ተካቶ የሚታተም ይሆናል።

ከ8ኛ-10ኛ ክፍል ባለው የግዕዝ ዜማ ወመዝሙር ክፍለ ትምህርት ታትሞ በወጣው መጽሐፍ ላይ በተወሰነ መጠን ተካቷል። ሙሉው የመጽሐፉ ይዘት በመንበረ ፖትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምርያ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት መካነ ድር ላይ ማግኘት የሚቻል መሆኑን እናሳውቃለን።

✍️ መጻሕፍቱን ለማውረድ ከዚህ በታች ያሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ፦

ሦስተኛ ዙር የ፲፪ኛ ክፍል የምርቃት መርሐ ግብር

 

በሙከራ ትግበራ ቀድመው ከጀመሩ እና በልዩ ምዘና ከመካከለኛ ክፍል ከጀመሩ አጥቢያዎች መካከል በ2017 ዓ.ም በሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ሥርዓተ ትምህርት መሠረት የ፲፪ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ምዘና የተመዘኑ ተማሪዎች ምረቃ

ዕለተ እሑድ መስከረም ፲፩ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም

በጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ

ከቀኑ ፯ ጀምሮ