ትዌድሶ መርዓት ወትብሎ (2)

ወልድ እኁየ ቃልከ አዳም(4)

ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ (3)

ሐረገ ወይን

እንተ በምድር ሥረዊሃ

ወበሰማይ አዕፁቂሃ

ሐረገ ወይን

እንተ በሥሉስ ትትገመድ ወታፈሪ ለነ አስካለ በረከት

ሐረገወይን

ሲሳዮሙ ለቅዱሳን

ሐረገወይን

ሠርዐ ሰንበተ በቃሉ ወጸገወ ሰላመ ለኩሉ

(ቅዱስ ያሬድ)

ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ

ናሁ አስተርአየ ጽጌ መርዓቱኒ ትቤ

ወልድ እኁየ ይምዕዝ ከርቤ

ናሁ አስተርአየ ጽጌ

ዕንባቆም ነቢይ ግብረ ምግባሩ ለወልድ አንከርኩ ይቤ

ናሁ አስተርአየ ጽጌ

ንጉሠ ሰላም ክርስቶስ ዓቢይ ልዕልናከ

ወመንክር ስብሐቲከ ለዕረፍት ሰንበተ ሠራዕከ

(ቅዱስ ያሬድ)

ረኃበ ወጽምአ አዘክሪ ድንግል ረኃበ ወጽምአ (2)

ምንዳቤ ወኃዘነ አዘክሪ ድንግል (2)

(አባ ሕርያቆስ፣ ዜማ በሊቃውንት)

አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ (2)

ክበበ ጌራ ወርቅ  (2) አክሊለ ጽጌ

ክበበ ጌራ ወርቅ  (2) አክሊለ ጽጌ  (2)

(አባ ስብሐት ለአብ፣ ዜማ በሊቃውንት)

እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ድንግል (2)

ምስለ ሚካኤል ምስለ ሚካኤል ፍሡሕ ወገብርኤል  (2)

(አባ ስብሐት ለአብ፣ ዜማ በሊቃውንት)

እስከ ማእዜኑ እግዝእትየ

ውስተ ምድረ ነኪር ትሄልዊ፣

ገሊላ እትዊ(4) ሀገርኪ ገሊላ እትዊ(4)

(አባ ስብሐት ለአብ፣ ዜማ በሊቃውንት)

ኢየሓፍር ቀዊመ ቅድመ ሥዕልኪ (2)

ወርኃ ጽጌረዳ(3) አመ ኀልቀ ወርኃ ጽጌረዳ  (2)

(አባ ስብሐት ለአብ፣ ዜማ በሊቃውንት)

ድንግል መከራሽን ጥቂት ላስታውሰው

በሄሮድስ ዘመን ፍጥረት ያለቀሰው

አንቺ የአምላክ እናት ደግሞም እመቤት

እንደ ችግረኛ በቃሽ ለስደት

አቤት በዚያን ጊዜ ያየሽው መከራ

ያለቀስሽው ልቅሶ ይቅር አይወራ

የክርስቶስ እናት አንቺ ስደተኛ

ካንቺ ጋር ስደቱን አሳስቢልን ለእኛ

አዝ……

አዛኝቷ ማርያም በጠራሁሽ ጊዜ

እንድትደርሽልኝ በመከራ ጊዜ

መከራ ያየ ሰው መቼም አይጨክንም

አትጨክኚብኝ አደራሽን ማርያም (2)

አዝ…..

እሴብሕ ጸጋኪ ኦ እግዝእትየ ማርያም

ዕፅ ልምልምት ወፍሬ ጥዕምት (3)

ሐረገ ወይን (3) አንቲ ማርያም

ዓጸደ ወይን (3) አንቲ ማርያም

ትመስሊ ፊደለ ወትወልዲ ወንጌለ

ወታገምሪ መስቀለ

አዝ……

ትመስሊ ሰማየ ወትወልዲ ፀሐየ

ወታገምሪ አዶናየ

አዝ…..

ትመስሊ መሶበ ወትወልዲ ኮከበ

ወታጸግቢ ርሁበ

አዝ……

ትመስሊ መቅደስ ወትወልዲ ንጉሠ

ወታገምሪ መንፈስ ቅዱሰ

አዝ……

ትመስሊ ታቦተ ወትወልዲ ጽላተ

ወታገምሪ መለኮተ

አዝ…..

ትመስሊ ደመና ወትወልድ ኅብሰተ መና

ወታገምሪ ጥዒና

አዝ……

ትመስሊ ገራኅተ ወትፈርዪ ሰዊተ

ወታጸድቂ ነፍሳተ

አዝ…….

ትመስሊ ስኂነ ወትወልዲ መድኅነ

ወትፌውሲ ድውያነ

አዝ…….

ትመስሊ ምሥራቀ ወትወልዲ መብረቀ

ወታለብሲ ዕሩቀ

አዝ….

ለአብ መርዓቱ ለወልድ ወላዲቱ

ለመንፈስ ቅዱስ ጽርሐ ቤቱ

(አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ)

ንግሥተ ሰማያት ወምድር ማርያም ድንግል

ተፈጸመ(6) ማኅሌተ ጽጌ

(አባ ስብሐት ለአብ፣ ዜማ በሊቃውንት)

ከማሃ ኀዘን (2) ወተሰዶ  ኀዘን (2)

ርእዮ ለይብኪ ዓይነ ልብ ዘቦ ዓይነ ልብ  (2)

(አባ  ስብሐት ለአብ፣ ዜማ በሊቃውንት)

(በቀኝና በግራ)

ስደትሽን ጭንቀትሽን ስናስታውሰው  (2)

ድንግል ምንኛ ነው የሚያሰቅቀው  (2)

ርዳታን ስትሺ ብዙ ተጨነቀሽ  (2)

ለኛ ሕይወት ሆነን ድካም ስቃይሽ  (2)

እንደ ሌሎች ሁሉ ድንግልም ሞታለች (2)

ኃይለ ልዑል ጋርዷት በክብር አርፋለች  (2)

ዕድል ፈንታ ሲሆን ለማንም ሰው ሞት  (2)

የማርያም ሞት ግን ልዩ ነው በእውነት  (2)

በጌቴሴማኒ ያረፈው ሥጋሽ  (2)

ለድኩማን ብርታት መድኅን ነው ፈዋሽ  (2)

(በኅብረት፣)

ዕልል ዕልል እንበል እኛ የሰው ልጆች (2)

እርሷም እንደ ልጇ ከሞት ተነሥታለች (2)