በአንድነቱ ትግበራ ላይ የሉ ፕሮጀክቶች

በስልታዊ ዕቅዱ መሠረት ማስፈጸሚያ ፕሮጀክቶች ተዘጋጅተው ለጠቅላይ ቤተ ክህነት የቀረቡ ሲኾን በስልታዊ ዕቅዱ የተለያዩ ዋና ዋና ግቦችን ለማሳካት በፕሮጀክት እንዲመሩ አቅጣጫ ተሰጥቶበት በቅዱስ ፓትርያርኩ በኩል በቋሚ ሲኖዶስ ታይቶ ትግበራ ተጀምሯል፡፡

ፕሮጀክቶቹም ሰፊ ከመኾናቸው የተነሣ በሦስት ዘርፍ ተለይተው ቀርበዋል፡፡ ይኸውም፡-

  1. ሥርዓተ ትምህርት ዝግጅትና ትግባራ ዘርፍ፣
  2. የሚዲያና ቴክኖሎጂ ዘርፍ፣
  3. የአቅም ማጎልበቻ እና  መዋቅራዊ አሠራር ዘርፍ

1. ሥርዓተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ዘርፍ

  1. የሰ/ት/ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት መምሪያ መጽሐፍ ዝግጅት፣
  2. የሰ/ት/ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት መምሪያ መጽሐፍ ዝግጅት (እንግሊዝኛ፣ ኦሮምኛ እና ትግርኛ) ትርጉም ዝግጅት፣
  3. ከ1ኛ እስከ 4ኛ ክፍል 27 መጻሕፍት ዝግጅት፣
  4. ከ5ኛ እስከ 8ኛ ክፍል 28 መጻሕፍት ዝግጅት፣
  5. ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል 26 መጻሕፍት ዝግጅት፣
  6. ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል 81 መጻሕፍት ትርጉም (በእንግሊዝኛ፣ ኦሮምኛና ትግርኛ) ዝግጅት፣
  7. የሰ/ት/ቤቶች መምህራን ማሠልጠኛ ተቋም ምሥረታ፣
  8. የሥነ ጥበባት ማበልጸጊያ ማዕከል ምሥረታ፣
  9. የትምህርት መሣሪያዎች ማምረቻ ተቋም ምሥረታ፣
  10. የተጓዳኝ ትምህርቶች ማበልጸጊያ ማዕከል ምሥረታ፣

2. የሚዲያና ቴክኖሎጂ ዘርፍ

  1. የሰ/ት/ቤቶች ትምህርት በቴሌቪዥን ስቱዲዮ ግንባታና ግብዓት ማሟላት ፕሮጀክት፣
  2. የሕትመት ዝግጅት ፕሮጀክት፣
  3. የሶሻል ሚዲያ አገልግሎት ፕሮጀክት፣
  4. ቨርችዋል ማስተማርያ ማዕከል ማልማትና ማደራጀት ፕሮጀክት፣
  5. ሶፍትዌርና አፕልኬሽን ማልማት ፕሮጀክት፣
  6. የመረጃ ማደራጃ ዳታ ቤዝ ማልማት ፕሮጀክት

3. የአቅም ማጎልበቻ እና መዋቅራዊ አሠራር ዘርፍ

  1. የአመራርና አገልጋዮች ማፍሪያ ተቋም ምሥረታ
  2. መዋቅራዊ ማስፈጸሚያ መመሪያና ማንዋል ዝግጅት ፕሮጀክት፣
  3. የአመራርና ተተኪዎች መደበኛ ስልጠና ፕሮጀክት፣
  4. መዋቅራዊ ክትትል፣ መረጃ እና የስልታዊ ዕቅድ ትግበራ ሥርዓት ፕሮጀክት