ከላይኛው ሀገር ከሰማያት ወርዶ

ከድንግል ማርያም በሥጋ ተወልዶ

ድንግል ማርያም ሆይ ያስገኘሽው ፍሬ

ለሕዝቦች አርአያ ተጠመቀ ዛሬ

መለኮት ኃያሉ ተኝቶ በበረት

እጅ መንሻ አመጡለት ሦስት ነገሥታት

ድንግል ማርያም ሆይ ያስገኘሽው ፍሬ

ለሕዝቦች አርአያ ተጠመቀ ዛሬ

ሎሌ ወደ ጌታው ነው እንጂ የሚሄድ

ጌታ እንዴት ይመጣል አገልጋዩ ዘንድ

አዝ•••

አጠምቅ ነበረ ባንተ ስም ሕዝቡን

እንዴት ብዬ ላጥምቅ አንተን ጌታዬን

አጥምቀኝ እኔን እንዲህም እያልክ

ከሣቴ ብርሃን ወልዱ ለቡሩክ

አዝ•••

እንደዚህ እያለ ሲያጠምቅ በልብ

መንፈስ ቅዱስ መጣ በአምሳለ ርግብ

አብም መሰከረ በደመና ሳለ

የምወደው ልጄ ይኽ ነው እያለ

አዝ•••

ወደ ሀገራቸው ለመሄድ ሲነሱ

በሄሮድስ በኩል እንዳይመለሱ

መልአኩ ነግሯቸው እነሱም አምነው

በሌላ ጎዳና ገቡ አገራቸው

አዝ•••

ሰማይና ምድርን እንዳልደነገገ

ከሕፃናት ጋራ በገሊላ አደገ

ከግብፅ ሲመለስ ኖሮ በስደት

ናዝራዊ ለመባል ኖረ በናዝሬት

ከድንግል ተወልዶ እኛን ሊቀድስ (፪)

ተጠመቀ ኢየሱስ ባሕረ ዮርዳኖስ (፪)

መጥምቁ ዮሐንስ ምንኛ ታደለ

ከነቢያት ሁሉ ሥልጣኑ ከፍ አለ

አዝ•••

ትንቢቱን ሊፈፅም አስቦ ክርስቶስ

ተጠምቆ አዳነን በባሕረ ዮርዳኖስ

አዝ•••

ምሥጢረ ሥላሴ ታየ የዚያን ዕለታ

ምን ይከፈለዋል ለአምላክ ውለታ

አዝ•••

እመቤቴ ማርያም ምነኛ ታደልሽ

ከአዳም ልጆች ሁሉ አንቺ ተመረጥሽ

አዝ•••

ቸሩ አምላካችን መድኃኔ ዓለምን

ኑ እናመስግነው ባንድነት ሆነን

ዮሐንስ አጥመቆ ለኢየሱስ (፪)

በፈለገ ዮርዳኖስ በፈለገ ፈለገ ዮርዳኖስ (፪)

(ቅዱስ ያሬድ)

ሖረ ኢየሱስ (፬)

እም ገሊላ (፫) ኀበ ዮሐንስ (፪)

(ቅዱስ ያሬድ)

ሄደ ኢየሱስ ሄደ ኢየሱስ (፪)

ከገሊላ ከገሊላ ከገሊላ ወደ ዮሐንስ (፪)

ሖረ ኢየሱስ  ሖረ ኢየሱስ(፪)

እም ገሊላ ኀበ ዮሐንስ እምገሊላ ኀበ ዮሐንስ (፪)

(ቅዱስ ያሬድ)

መጽአ ቃል እምደመና ዘይብል ዘይብል (፪)

ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር(፪)

(ቅዱስ ያሬድ)

(ትርጉም)

መጣ ቃል ከደመና እንዲህ የሚል (፪)

የምወደው የማፈቅረው ልጄ ይህ ነው (፪)

ኀዲጎ ተሥዓ ወተሥዓተ ነገደ (፪)

ማእከለ ባሕር (፬) ቆመ ማእከለ ባሕር (፪)

(ቅዱስ ያሬድ)

ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ (፪)

ተጠምቀ ሰማያዊ በእደ መሬታዊ (፪)

ተጠምቀ ሰማያዊ በእደ መሬታዊ (፪)

ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ

አምላክ ሆይ ሕዝቦችህ ዳኑ በልደትህ

አምላክ ሆይ ሕዝቦችህ ዳኑ በጥምቀትህ

ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ

ኀዲጎ ተሥዓ ወተሥዓተ ነገደ (፪)

ማእከለ ባሕር ቆመ ማእከለ ባሕር (፪)

(ቅዱስ ያሬድ)

ወተመሰሉ ሰብአ ዓይን አባግዐ ላባ ወማይ (፪)

ለኀበ አባግዕ ዘዮም ዘዮም ወጥምቀት ዐባይ (፪)

(አርኬ፣ ዜማ በሊቃውንት)

ነድ ለማየ ባሕር ከበቦ (፪)

ማየ ባሕር ኀበ የሐውር ጸበቦ (፪)

(ነግሥ ፣ ዜማ በሊቃውንት)

(በመቀባበል)

እሰይ እሰይ ተወለደ

እሰይ እሰይ ተጠመቀ

ከሰማየ ሰማያት ወረደ

ከድንግል ማርያም ተወለደ

እርሱ ባይወለድ   እሰይ እሰይ

ቸሩ አምላካችን      >>     >>

እርሱ ባይጠመቅ   >>     >>

መድኃኒታችን        >>     >>

መች ትገኝ ነበረ     >>    >>

ገነት ርስታችን       >>    >>

አዝ•••

ብርሃነ ወጣላቸው እሰይ እሰይ

ለእውነት ወገኖች    >>    >>

በጨለማ ጉዞ         >>    >>

እንዲያ ሲሰለቹ       >>    >>

አዝ•••

እንደ ጠል ወረደ   አሰይ እሰይ

ከሰማይ ወደ እኛ    >>    >>

ወገኖቹን ሊያድን    >>    >>

ከክፉ ቁራኛ           >>    >>

አዝ•••

(በኅብረት)

እግዚአብሔር አብ ላከ እሰይ እሰይ

አንድያ ልጁን                >>    >>

እርሱ ወዷልና               >>     >>

እንዲሁ ዓለሙን            >>    >>

ዮሐንስኒ ሀሎ ያጠምቅ (፪)

በሄኖን በቁሩበ ሳሌም  (፪)

(ቅዱስ ያሬድ)

ወረደ ወልድ (፮)

እም ሰማያት ውስተ ምጥማቃት (፬)

(ቅዱስ ያሬድ)

እንዘ ሕፃን ልሕቀ በዮርዳኖስ ተጠምቀ (፪)

በዮርዳኖስ (፬) ተጠምቀ በዮርዳኖስ (፪)

(ቅዱስ ያሬድ)

በፍሥሓ በፍሥሓ ወበሰላም (፪)

ወረደ ወልድ (፬) ወልድ ውስተ ምጥማቃት (፪)

(ቅዱስ ያሬድ)

(በኅብረት)

ግነዩ ለእግዚአብሔር እስመ ኄር(፪)

እስመ ለዓለም ምሕረቱ እስመ ለዓለም(፬)

እናመስግንሽ የአምላክ እናት በዝማሬ (፪)

የዓለም ቤዛ ነውና የማኀፀንሽ ፍሬ(፬)

ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ካንቺ ተወልዶ(፪)

መለኮት ወረደ ዮርዳኖስ እኛን ለመቀደስ(፬)

በድንግልናሽ የወድሽው ክርስቶስ(፪)

የድኩማን ብርታት ነው የሕሙማን ፈውስ(፬)

በዮሐንስ እጅ ተጠመቀ ዕዳችንን ፋቀ(፪)

በቸርነቱ ጠብቆ ከበደል አራቀን (፬)

ስምሽን የጠራ ዝክርሽንም ያዘከረ(፪)

በመንግሥተ ሰማያት ይኖራል እንደተከበረ (፬)

ብርሃነ መለኮት ያደረብሽ አዳራሽ(፪)

ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ድንግል አንቺ ነሽ(፬)

እመቤታችን እናታችን ማርያም(፪)

የተማፀነሽ ይድናል ለዘለዓለም (፬)

ድንግልናሽም ሳይለወጥ ወልድን የወለድሽ (፪)

የጌታችን እናት ማርያም ድንግል አንቺ ነሽ(፬)

(ሢራክ ታደሰ)

(በመቀባበል)

በጎል በጎል ሰብአ ሰገል (፬)

በጎል ሰብአ ሰገል ሰገዱ ሎቱ (፬)

ፀሐይ (፫) ፀሐይ ሠረቀ (፬)

ፀሐይ ሠረቀ ክርስቶስ ተጠምቀ (፬)

አንቺ ዮርዳኖስ (፬) ምንኛ ታደልሽ (፬)

የእግዚአብሔር መንፈስ ከላይ ወርዶልሽ (፬)

የዓለም መድኃኒት ተጠመቀብሽ (፬)

ድንግል ማርያም (፬) ንጽሕት ቅድስት (፬)

የጌታ እናት ምሥጋና ይገባሻል (፬)

ከሴቶች ሁሉ አንቺ ተመርጠሻል (፬)

ዕልል ዕልል (፬) ደስ ይበለን (፬)

ወልድ ተወልዶ ነፃ አወጣን (፪)

ዮሐንስ ሲያጠምቀው ድል አገኘን (፪)

በእደ ዮሐንስ ተጠመቀ ኢየሱስ ናዝራዊ (፪)

ሰማያዊ (፭) ኢየሱስ ናዝራዊ (፪)

እግዚኡ መርሐ ዮርዳኖስ አብጽሐ (፪)

ወበህየ ዮሐንስ ወበህየ ፍጹመ ተፈሥሐ (፪)

(ትርጉም)

ጌታውን መራና ከዮርዳኖስ አደረሰው (፪)

በዚህም ዮሐንስ (፪) በፍጹም  ደስ አለው (፪)

(ቅዱስ ያሬድ)

ውስተ ማኀፀነ ድንግል ኀደረ ማኀፀነ ድንግል (፪)

ሰማይ ወምድር ዘኢያገምሮ (፪) በማይ ተጠምቀ (፪)

(ቅዱስ ያሬድ)

ክርስቶስ ተወልደ ክርስቶስ ተጠምቀ ክርስቶስ ተወልደ (፪)

ወለደነ ዳግመ ወለደነ ዳግመ እመንፈስ ቅዱስ ወማይ (፪)

(ቅዱስ ያሬድ)

የዓለምን በደል የሰውን ግፍ አይቶ

ዘጠና ዘጠኙን መላእክትን ትቶ

ጽድቅን ለመፈጸም በደልን አጥፍቶ

የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ

አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለኛ

የሰማዮች ሰማይ የማይችለው ንጉሥ

ተወልዶ ሲጠመቅ እኛን ለመቀደስ

ተራሮች ደንግጠው ዘለሉ እንደ ፈረስ

አዝ•••

ባሕር ተጨነቀች ጠበባት መሬቱ

ዮርዳኖስም ሸሸ አልቆመም ከፊቱ

እንደ ተናገረው ዳዊት በትንቢቱ

አዝ•••

ልጁ በዮርዳኖስ ጽድቅን ሲመሠርት

መጣ በደመና ሰማያዊው አባት

እየመሰከረ የልጁን ጌትነት

አዝ•••

እንደምናነበው በወንጌል ተጽፎ

መንፈሰ ቅዱስ ታየ በራሱ ላይ ዓርፎ

በርግብ ምሳሌ ክንፉን አሠይፎ

አዝ•••

ባሕር ስትጨነቅ ተራራው ሲዘምር

ሰማዩ ሲከፈት ደመናው ሲናገር

ዓለም በዛሬው ቀን አየች ታላቅ ምሥጢር

(መልአከ ታቦር ተሾመ ዘርይሁን )

አምላክ ከዮርዳኖስ (፪) ተጠምቆ ሲወጣ (፪)

ሰማያት ተከፍተው (፪) ከሰማይ ቃል መጣ

ቃሉም አንዲህ ነበር (፪) እንደሚከተለው (፪)

የምወደው ልጄ (፫) ይህ ነው የሚል ነው

ዘጠና ዘጠኙን (፪) መላዕክቱን ትቶ (፪)

አምላክ ተጠመቀ (፫) በዮርዳኖስ ገብቶ

ዕፁብ ድንቅ ነው (፪) ይገርማል በውኑ (፪)

ሰማያዊ አምላክ (፫) ምድራዊ መሆኑ

አብ የነገረለት (፪) በደመና ወርዶ (፪)

ተጠምቆ አዳነን (፫) ከድንግል ተወልዶ

(ብርሃኑ ውድነህ)

ጥምቀተ ባሕር ዮርዳኖስ ነያ (፪)

ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ

ጌታችን ሲጠመቅ ባሕር ምን አለች

አልችለውም ብላ ወደ  ኋላ ሸሸች

ብርሃነ መለኮት በወንዙ ሲመላ

ዮርዳኖስም ሸሸ ኼደ ወደ ኋላ

አዝ •••

አብ በመጣ ጊዜ ደመናውን ጭኖ

መንፈስ ቅዱስ ታየ በርግብ አምሳል ሆኖ

ለልጁ ምስክር ሊሆን ፈለገና

ቃሉን ተናገረ ሆኖ በደመና

አዝ•••

ጌታችን ሲጠመቅ በሠላሳ ዓመት

ባሕር ኮበለለች ግኡዟ ፍጥረት

ሰማይ ተከፈተ ሆነልን ፀዓዳ

ምሥጢረ ሥላሴ ታወቀ ተረዳ

አዝ•••

ዕዕልል በይ ዮርዳኖስ የጥምቀት መገኛ

የጽድቅ መሰላል የድኀነት መዋኛ

ቀላያተ አብርሕት ብዙዎቸ እያሉ

እንደምን ተመረጥሽ ዮርዳኖስ ከሁሉ

በዛሬው ጥምቀቱ ተነግሮ አዋጅ

ነፃነት አገኘን በእግዚአብሔር አብ ልጅ

እሰይ እሰይ ተወለደ (፪)

ከሰማየ ሰማያት ወረደ (፪)

በቅዱስ ዮሐንስ ተጠመቀ (፪)

አብ መሰከረለት በደመና ሳለ

የምወደው ልጄ ይኼ ነው እያለ

አዝ•••

ጌታ በዮሐንስ ሊጠመቅ ሲል ገና

ወደ ኋላ ሸሸ ዮርዳኖስ ፈራና

አዝ•••

እንደ አንበሳ ደቦል ተራሮች ዘለሉ

ዕፁብ ነው ድንቅ ነው ግሩም ነው እያሉ

(መዝሙረ ስብሐት)