ከደቂቀ እስጢፋኖስ እስከ መንበረ ሰላማ

ከደቂቀ እስጢፋኖስ እስከ መንበረ ሰላማ

ከደቂቀ እስጢፋኖስ እስከ መንበረ ሰላማ

ከደቂቀ እስጢፋኖስ እስከ መንበረ ሰላማ

የተከበራችሁ አንባብያን የዚህን ጽሑፍ የመጀመሪያ የሆነውን እና አቡነ ተክለ ሃይማኖትን በተመለከተ ተሐድሶ መናፍቃን እና ተስፈንጣሪ ፖለቲከኞች የሚያነሷቸውን የፈጠራ ድርሰቶች መነሻ ምክንያት የሚያስነብበውን ጽሑፍ ለንባብ ማብቃታችን የሚታወቅ ነው። ቀጣዩን ክፍል ደግሞ እንደሚከተለው አቅርበነዋል። መልካም ንባብ፡-

ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ

በመካከለኛው ዘመን ለቤተ ክርስቲያን መልካም ካደረጉ ነገሥታት አንዱ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ነው። ንጉሡ አገሪቱን ለሁለት ሊከፍል ጫፍ ደርሶ የነበረውን የቤተ ተክለ ሃይማኖት እና የቤተ ኤዎስጣቴዎስ ጉዳይ መፍትሔ በመስጠት ሰላም እንዲወርድ አድርጓል። ጉዳዩ እንዲህ ነው። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርሰቲያን በሐዋርያዊ አገልግሎታቸው የሚታወቁት የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም መነኰሳት እና የአባ ኤዎስጣቴዎስ ተከታዮች ልዩነት ፈጥረው ነበር። የልዩነቱ ምክንያት ቤተ ተክለ ሃይማኖቶች መከበር የሚገባት ሰንበተ ክርስቲያን እንጂ ሰንበተ አይሁድ መከበር የለባትም ሲሉ ኤዎስጣቴዎሳውያን ደግሞ ቅዳሜም፣ እሑድም መከበር አለባቸው የሚል አቋም ያዙ። በዘመኑ የነበሩ ነገሥታት አቡነ ተክለ ሃይማኖትን ያከበርን መስሏቸው የእርሳቸውን ገዳም መነኰሳት አሳብ ደግፈው ቤተ ኤዎስጣቴዎሳውያንን መግፋት በመጀመራቸው ልዩነቱ እየሰፋ ሄደ። Read more

ከደቂቀ እስጢፋኖስ እስከ መንበረ ሰላማ

ከደቂቀ እስጢፋኖስ እስከ መንበረ ሰላማ

ከደቂቀ እስጢፋኖስ እስከ መንበረ ሰላማ

ከደቂቀ እስጢፋኖስ እስከ መንበረ ሰላማ

አባ እስጢፋኖስን እና ተከታዮቹንበተመለከተ ብዙ ይጻፋል፣ ይነገራል። የእርሱ እና የተከታዮቹ ጉዳይ ማንም እንደፈለገ ለመዘወር የተመቸ ነው። ከትግራይ ክልል የተነሡ ተስፈንጣሪ ፖለቲከኞች ባላንጣችን የሚሉትን ሸዋን ለመተቸት ይጠቅሱታል። በክልሉ ኑፋቄያቸውን ለመዝራት ፈልገው ያልተሳካላቸው ተሐድሶ መናፍቃን በዕውቀቱ አቻ የሌለው፣ በአስተምህሮው እንከን የማይገኝበት አስመስለው ያቀርቡታል። ቤተ ክርስቲያኗን በዘር ለመከፋፈል የሚደክሙ አካላት አርአያነቱን እንከተል በማለት የፈጣራ ድርሰት ጽፈው ያነቡለታል። እንደ አባ እስጢፋኖስ ያለ ምግባረ ብልሹ ራሱን ኮፍሶ ሌላውን ስለሚያናንቅ እንዲህ ያለው ምግባር የመናፍቃንመለያ መሆኑን መረዳት ከተደጋጋሚ ጥፋት ይታደጋል። Read more

የትግራይ ቤተ ክህነት እንቅስቃሴ ለተሐድሶ መናፍቃን ሰርግና ምላሽ

የትግራይ ቤተ ክህነት እንቅስቃሴ ለተሐድሶ መናፍቃን ሰርግና ምላሽ

የትግራይ ቤተ ክህነት እንቅስቃሴ ለተሐድሶ መናፍቃን ሰርግና ምላሽ

የትግራይ ቤተ ክህነት እንቅስቃሴ ለተሐድሶ መናፍቃን ሰርግና ምላሽ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለሀገር ካበረክተችው አስተዋጽኦ አንዱ የሀገር አንድነት ምክንያት ሆና መኖሯ ነው። ለዚህም ነው ኢትዮጵያን ማዳከም የሚፈልጉ ኃይሎች ሁሉ መጀመሪያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ማዳከምን ዋና አጀንዳቸው የሚያደርጉት። በተለይም ከ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ሚስዮናውያን ቤተ ክርስቲያንን በማጥፋት ኢትዮጵያን መረከብ አጀንዳቸው ካደረጉ ከአራት መቶ በላይ ዘመናትን አስቈጥረዋል። በዘህ ጊዜ ውስጥ ራሳቸውን ቤተ ክርስቲያንን ለማጥፋት የሚመኙትን ያህል ምናልባትም ከዚያ በላይ ቤተ ክርስቲያንን የሚጠሉ “ኢትዮጵያውያን ፈረንጆችን” ማፍራት ችለዋል። እነዚህ ከውጪ የሚላክላቸውን አጀንዳና ፍርፋሪ ተቀብለው በውስጥ ሆነው ቤተ ክርስቲያንን ያጠቃሉ። Read more

ለአገራችን ኢትዮጵያ ሰላምን ስጣት

ለአገራችን ኢትዮጵያ ሰላምን ስጣት

ለአገራችን ኢትዮጵያ ሰላምን ስጣት

ለአገራችን ኢትዮጵያ ሰላምን ስጣት

ሊቀ ነቢያት ሙሴ እስራኤላውያን ከአሕዛብ ነገሥታት ጋር ጦርነት በሚያደርጉበት ወቅት ወንድሞቻችሁ ወደ ጦርነት ሔደው እናንተ ከቤታችሁ ተቀምጣችኋል ሲላቸው “እኛ ባሪያዎችህ ሁላችን ጋሻ ጦራችንን ይዘን በእግዚአብሔር ፊት ጌታችን እንደተናገረ ወደ ጦርነት እንሔዳለን” (ዘኁ. ፴፪፡፳፯) የሚል መልስ ሰጥተውታል። በዓለም ላይ ሰላም ሲታጣ  አገራት ሰላም አስከባሪ ኃይል በመላክ ሰላምን በፈረስ አንገት፣ በጦር አንደበት ሊያመጧት ይሻሉ። የተከሠተውን የሰላም እጦት ወደ ነበረበት ለመመለስ ጦርነት ያውጃሉ። ሰላምን የሚሹ ሁሉ ለጦርነት እንዲዘጋጁ ዐዋጅ ይነግራሉ። ሰላም የጦርነት አለመኖር ቢሆንም የሚለካው በውጤቱ ነውና የተባለው ሰላም እስከሚመጣ ሕዝቡ በጦርነት ይሳተፋል። ይህ የዕለት ከዕለት የየአገራት አነዋወር መገለጫ ነው። Read more

ጦርነቱን ወደ ሰላም በማሸጋገር ምድሪቱንም፣ ትውልዱንም ማሳረፍ ከሁሉም ወገን ይጠበቃል

ጦርነቱን ወደ ሰላም በማሸጋገር ምድሪቱንም፣ ትውልዱንም ማሳረፍ ከሁሉም ወገን ይጠበቃል

ጦርነቱን ወደ ሰላም በማሸጋገር ምድሪቱንም፣ ትውልዱንም ማሳረፍ ከሁሉም ወገን ይጠበቃል

ጦርነቱን ወደ ሰላም በማሸጋገር ምድሪቱንም፣ ትውልዱንም ማሳረፍ ከሁሉም ወገን ይጠበቃል

የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ተቀዳሚ ተግባር ሐዋርያዊ አገልግሎትን ማከናወን ቢሆንም የአገር ሰላም እንዲሰፍን የመሪነት ሚናስትጫወት ኖራለች። የምንገኝበት ዘመንም ከእስከ አሁኑ የበለጠ የሰላም ሐዋርያ መሆንን የሚጠይቅ ነው። እንኳን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በኢትዮጵያ ጉዳይ ይመለከተኛል የሚል አካል ሁሉ ሰላም የሚሰፍንበትን መንገድ መፈለግ ከሚያስፈልግበት ደረጃ ላይ እንገኛለን። የቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሰላም አምባሳደርነት ለአንድ ወገን ያደላ ሳይሆን የሁሉም እናትነት መሆኗን በተግባር መግለጥ ይገባዋል። Read more

ከአዲስ ተሿሚዎች የሚጠበቅ ተግባርና ኃላፊነት

ከአዲስ ተሿሚዎች የሚጠበቅ ተግባርና ኃላፊነት

ከአዲስ ተሿሚዎች የሚጠበቅ ተግባርና ኃላፊነት

ከአዲስ ተሿሚዎች የሚጠበቅ ተግባርና ኃላፊነት

ሥርዓተ ሲመተ ኤጲስ ቆጶሳት መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ሐምሌ 09 2015 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለመጀመሪያ ጊዜ የራሷ ልጆች ኤጲስ ቆጶስነት እንዲሾሙላት ባደረገች ጊዜ የተፈጸመውን መንፈሳዊ ተግባር በዘመኑ ታትሞ የወጣው ብርሃንና ሰላም ጋዜጣ የዘገበው “አመራረጡ ግን በዕጣ እንዲሆን ምክር ተቈርጦ ስለነበር በዕጣው ላይ ሰባት ቀን ሙሉ በቤተ ክርስቲያን ጸሎት እየተጸለየበት እና ቅዳሴ እየተቀደሰበት ቆይቶ ለአምስቱ መምህራን ዕጣ ወጣላቸው። ስማቸውም መምህር ደስታ፣ መምህር ኃይለ ማርያም፣ መምህር ወልደ ኪዳን፣ መምህር ኃይለ ሚካኤል ናቸው። አምስተኛው ግን ወደ ግብፅ አልወረዱም” በማለት ነበር (ብርሃንና ሰላም ሰኔ 6 ቀን 1921 ዓ.ም፣ ገጽ 189)። Read more