ፍኖተ-ጎርጎርዮስ

ፍኖተ-ጎርጎርዮስ

ሕዝበ ክርስቲያኑ የቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙን ትምህርቱን ሰምተው ግብሩን ዐይተው ሲወዱት ኖረዋል፡፡ ወላጆቹን በተለይ በእርግና ዘመን ላይ የነበረ አባቱን ጠይቆ ለመመለስ ወደ ወላጆቹ በሔደበት አጋጣሚ በሕዝቡ ግፊት ሥልጣነ ክህነት እንዲቀበል ተደረገ፡፡ እርሱ ግን ገዳማዊ ሕይወትን እጅግ ወድዶ ነበርና በብሕትውና ወደሚኖርበት ገዳም ሔዶ ተደበቀ፡፡ የቃልም የሕይወትም መምህር ነበር፤ በአንዲት በዓት ረጅም ጊዜ በጾም በጸሎት በመወሰን የሚታወቅ ገዳማዊ አባት፡፡ በትምህርትም ዓለማዊውን ትምህርት ከቂሣሪያ እስከ አቴና በመጓዝ በግሪክ ፍልስፍና የተራቀቀ፣ በመንፈሳዊው ትምህርትም ከሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ በኋላ ነባቤ መለኮት (ታኦሎጎስ) እስከ መባል የደረሰ የነገረ መለኮት ሊቅ ነበር፡፡

ሄሮድያዳ ዛሬም የዮሐንስን አንገት ለማስቀላት እየተዋጋች ነው።

ሄሮድያዳ ዛሬም የዮሐንስን አንገት ለማስቀላት እየተዋጋች ነው

ሄሮድያዳ ዛሬም የዮሐንስን አንገት ለማስቀላት እየተዋጋች ነው።

ሄሮድያዳ ዛሬም የዮሐንስን አንገት ለማስቀላት እየተዋጋች ነው።

ቍስጥንጥንያ አዲሲቷ ሮም በሚል ስያሜ የምሥራቅ ሮማ ግዛት ዋና ማዕከል ነበረች፡፡ ከአራተኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ላይ ያለፈቃዱ ቢሆንም ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ፓትርያርክ ሆኖ ተሾሞላታል፡፡ የቅዱሱን ሹመት ተከትሎ የቁስጥንጥንያ መንበረ ፓትርያርክ እና ካህናቱ ከቅምጥል የአኗኗር ዘይቤ ጋር ተለያይተዋል፡፡ መንበረ መንግሥቱ ደግሞ በንጉሠ ነገሥት አርቃድዮስ (አርቃዲዎስ) እጅ ሲሆን ንግሥቲቷ አውዶክስያ ነበረች፡፡

Read more

“ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁ” ገላ. ፪፡፲፬

“ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁ” ገላ. ፪፡፲፬

“ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁ” ገላ. ፪፡፲፬

“ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁ” ገላ. ፪፡፲፬

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የተጠመቅን ሁላችን ክርስቶስን እንደለበስን፣ በክርስቶስ አንድ እንደሆንን፣ ከዚህ አንድነት መውጣት ከክርቶስ አካልነት ከቤተ ክርስቲያን ኅብረት መለየት መሆኑን ደጋግሞ ነግሮናል። ለዚህም ነው ለገላትያ ክርስቲያኖች “አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፤ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፤ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና” በማለት የነገራቸው። የክርስቶስ አካልነት በዘር፣ በጎሣ፣ በቋንቋ ወይም በፆታ የሚገኝ ሳይሆን መንፈሳዊ ሰው ለመሆን በመሠራት ገንዘብ የሚደረግ ነው። ቤተ ክርስቲያንም አካለ ክርስቶስ እንደመሆኗ በቋንቋና በዘውግ የምትወሰን አይደለችም። እንዲያውም ቤተ ክርስቲያንን በእነዚህ ምድራዊ አሳቦች መወሰን በመንፈስ ቅዱስ ላይ ትልቅ ጽርፈት ነው። አምላካዊውንም ሕግ በሰብአዊ ሕግ ለመተካት መሞከር ነው። ቅዱስ ዮስጢኖስ ፖፖቪች የተባለ አባት ስለዚህ ጉዳይ ሲናገር እንዲህ ብሏል። Read more

ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ

የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት በኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ሂደት ላይ ያለውን ጥያቄ በደብዳቤ አሳወቀ

ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ

ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ

የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት በኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ሂደት ላይ ያለውን ጥያቄ ለአስመራጭ ኮሚቴው በደብዳቤ አሳውቋል። የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት፤ በቀኖና ቤተ ክርስቲያን አግባብ የኢጲስ ቆጶሳት ምልመላ፣ መስፈርት እና ሂደት ለሕዝብ ይፋ ሆኖ በግልፅ መከናወን እንደሚኖርበት በደብዳቤው አጽእኖት ሰጥቷል። በተጨማሪም፤ እስካሁን በተኼደበት መንገድ ከተቀጠለ፤ የሕግና የቀኖና ጥሰት፣ እንዲሁም ይሁንታ የማጣት ጉዳይ ሊከሰት እንደሚችል አሳስቧል። ደብዳቤውን የተረከቡት የአስመራጭ ኮሚቴው ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ፣ ደብዳቤውን ለኮሚቴው አቅርበው እንደሚመክሩበት አሳውቀዋል።
በሌላ በኩል፤ ከቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው፤ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ በግቦት 14 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የወሰነውን የአዳዲስ ኢጲስ ቆጶሳት ሢመት በተመለከተ በምልዓተ ጉባኤው የተሰየሙት የአስመራጭ ኮሜቴ አባላት ሥራቸውን ያጠናቀቁ መሆኑን በመግለጽ ኮሚቴው አዘጋጅቶ በሚያቀረበው እጩ ኢጲስ ቆጶሳት ምርጫ ዙርያ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ለማስተላለፍ ይቻል ዘንድ በሚል ለሰኔ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. ምልዓተ ጉባኤ ጠርቷል። ከዚህ ጋር በተያያዘ፤ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ለአስመራጭ ኮሚቴው በደብዳቤ ያሳወቃቸው ጥያቄዎች ከተጠራው ምልዓተ ጉባኤ መስየም እና የመጨረሻ ውሳኔ በፊት ታይተው የተዛቡ አካሄዶች ይስተካከላሉ የሚል እምነት አሳድሯል።

እርሱን የምሾመው ለመንበሩ ክብር እንዲሰጠው ነው

እርሱን የምሾመው ለመንበሩ ክብር እንዲሰጠው ነው

እርሱን የምሾመው ለመንበሩ ክብር እንዲሰጠው ነው

እርሱን የምሾመው ለመንበሩ ክብር እንዲሰጠው ነው

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “አሁንም በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። ከእኔ በኋላ ለመንጋዪቱ የማይራሩ ነጣቂዎች ተኵላዎች እንደሚመጡ እኔ አውቃለሁ። ደቀ መዛሙርትንም ወደ እነርሱ ይመልሱ ዘንድ ጠማማ ትምህርትን የሚያስተምሩ ሰዎች ከእናንተ መካከል ይነሣሉ። ስለዚህም ትጉ፤ እኔ ሁላችሁንም ሳስተምር ሦስት ዓመት ሙሉ ሌትም፣ ቀንም እንባዬ እንዳልተገታ አስቡ። አሁንም ለእግዚአብሔርና ሊያነጻችሁ በቅዱሳንም ሁሉ መካከል ርስትን ሊሰጣችሁ ለሚችለው ለጸጋው ቃል አደራ ሰጥቻችኋለሁ” (ሐዋ. ፳÷ ፳፰-፴፪)¹ በማለት ያስተማረው ትምህርት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ኤጲስ ቆጶሳትን ስትመርጥ በጣም እንድትጠነቀቅ የሚያሳስብ ቃል ነው። Read more

ኤጲስ ቆጶስ ለመሾም የሚያገለግለው መስፈርት

ኤጲስ ቆጶስ ለመሾም የሚያገለግለው መስፈርት

ኤጲስ ቆጶስ ለመሾም የሚያገለግለው መስፈርት

ኤጲስ ቆጶስ ለመሾም የሚያገለግለው መስፈርት

ኤጲስ ቆጶሳት የአህጉረ ስብከታቸውን ክርስቲያኖች በአባትነት የሚጠብቁ፣ በመምከር ችግራቸውን የሚያቃልሉ፣ በማንኛውም ነገር አርአያ የሚሆኑ ናቸው። በዓመት ሁለት ጊዜ በሚደረገው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ በመሳተፍ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሚጠቅሙ ውሳኔዎች እንዲተላለፉም የድርሻውን ይወጣሉ። ይህም የአገልግሎቱን ከባድነት ሲያመለክት ለከባድ አገልግሎት የሚታጨው አባትም ኃላፊነቱን በመደንብ መወጣት የሚችል መሆኑን ይገባዋል። Read more

‹‹በበጎነት ላይ ዕውቀትን ጨምሩ›› (፪ኛ ጴጥ. ፩፥፭-፯)

‹‹በበጎነት ላይ ዕውቀትን ጨምሩ›› ፪ኛ ጴጥ. ፩፥፭-፯

‹‹በበጎነት ላይ ዕውቀትን ጨምሩ››(፪ኛ ጴጥ. ፩፥፭-፯)

‹‹በበጎነት ላይ ዕውቀትን ጨምሩ››
(፪ኛ ጴጥ. ፩፥፭-፯)

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን አምነው ከተከተሉት መካከል ጥቂቶችን መረጦ ሐዋርያትን ሾመ፡፡ እስከ ዛሬ ድረስ በእረኛውና በመንጋው መካከል ላለው መስተጋብር መሠረት አስቀመጠ፡፡ የዛሬዎቹ አበው ጳጳሳት እና ካህናት የዚህ ሐዋርያዊ ውርስ ተቀባዮች ናቸው፡፡ በሐዋርያነት የተሾሙት ለተጠሩበት ሐዋርያዊ አገልግሎት ስኬት የሚያስፈልጋቸውን ሥነ ምግባርና ዕውቀት ከጌታ በነቢብም በገቢርም ተምረዋል፡፡ ዛሬም ድረስ ለተጠሩበት አገልግሎት የሚመጥን ሥነ ምግባር እና ትምህርት (ዕውቀት) የሢመተ ጵጵስና ሁለት ምሰሶዎች ናቸው፡፡ Read more

ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳትና የምእመናን ሱታፌ

ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳትና የምእመናን ሱታፌ

ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳትና የምእመናን ሱታፌ

ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳትና የምእመናን ሱታፌ

የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ምእመናንን ማእከል ያደረገ ነው። ጌታችን አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያትን የሰጣቸው ዋናው ትእዛዝ “አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸውና ያዘዝኋችሁን ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርቴ አድርጓቸው” (ማቴ. 28፡19-20) የሚል ነው። ስለሆነም ሐዋርያትና በሐዋርያት እግር የተተኩት ሐዋርያውያን አበው፣ ዐቃብያነ እምነት፣ ሊቃውንት በአጠቃላይ በየዘመኑ የተነሡ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ዋና ግብራቸው ይህን ታላቁን ተልእኮ መፈጸም ነበር። ጌታችን ከሙታን ተለይቶ ከተነሣ በኋላ ለሐዋርያት ለሦስተኛ ጊዜ በተገለጠላቸው ወቅት ስምዖን ጴጥሮስን ሦስት ጊዜ ትወደኛለህን? ብሎ እየጠየቀ የሰጠው ትእዛዝም በተመሳሳይ “ግልገሎቼን አሰማራ፣ ጠቦቶቼን ጠብቅ፣ በጎቼን አሰማራ” (ዮሐ. 21፡15-17) የሚል ነው። Read more

እንኳን ደስ አለዎ ወይስ እግዚአብሔር ያስችልዎ?

እንኳን ደስ አለዎ ወይስ እግዚአብሔር ያስችልዎ?

እንኳን ደስ አለዎ ወይስ እግዚአብሔር ያስችልዎ?

እንኳን ደስ አለዎ ወይስ እግዚአብሔር ያስችልዎ?

ኤጲስ ቆጶስነት ምቾትን አብዝቶ ለሚሻው፣ አድልኦንና ወገንተኝነት ለሚስማማው ለሥጋ ጠባይ የሚመች ሓላፊነት አይደለም፡፡ ሰዋዊ ባሕርይን ገርተው የነፍስ ባሕርይን ገንዘብ ወደሚያደርጉበት ማዕርግ የሚሰግሩበት ራስን በመካድ መሠረት ላይ የቆመ የእግዚአብሔር ጥሪ ነው፡፡ ክህነት ትሑት ሰብዕናን የሚሻ የአገልግሎት ሥልጣን ነው፡፡ አንዱን ከሌላው አስበልጠው ለመጥቀም፣ ያልተደሰቱበትን ደግሞ ከሌላው በታች አድርገው ለመጉዳት ለቂም መወጫነት ዐስበው የሚሹት በትረ ሥልጣን አይደለም፡፡ የቂም በትር ወይም የድሎት መወጣጫ እርካብ ላድርግህ ቢሉት ባለቤቱ እውነተኛው ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስ (ዕብ. ፯፥፳፰) መክሊቱን የጠየቀ ዕለት መሸሸጊያ ጥግ ይጠፋል፡፡ እናም ኤጲስ ቆጶሳት አገልግሎታቸውን የሚፈጽሙት እውነተኛ ዳኝነት የባሕርይው በሆነ በእግዚአብሔር ፊት መሆኑን ለአፍታ መዘንጋት እንደሌለባቸው ቤተ ክርስቲያን አበክራ ታስገነዝባለች፡፡

Read more

አክሊል የሆነችው ሢመት መርጣ የምታርፍባቸው አባቶች

አክሊል የሆነችው ሢመት መርጣ የምታርፍባቸው አባቶች

አክሊል የሆነችው ሢመት መርጣ የምታርፍባቸው አባቶች

አክሊል የሆነችው ሢመት መርጣ የምታርፍባቸው አባቶች

ባለፉት ሁለት ተከታታይ ጽሑፎች ቤተ ክርስቲያን ያለችበትን የአመራር ሁኔታና የሚያስፈልጋትን አመራር ተመልክተናል። በዚህ ክፍል ደግሞ የሚፈለገውን አመራር ለመስጠት የሚችለው ምን መስፈርቶችን የሚያሟላ አባት ነው የሚለውን እንመለከታለን። የኤጲስ ቆጶስነት ሢመት ለሚገባው አባት አክሊል ስትሆን ለማይገባው ደግሞ እሾህ እንደምትሆንበት ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ሲከሠት የኖረ እውነት ነው። መንፈሳዊት ሢመት አክሊል የምትሆነው ኖላዊነታቸውን አምነው የተጣለባቸውን አደራ ለመወጣት ለሚተጉ አባቶች ሲሆን እሾህ የምትሆነው ደግሞ ሳይገባቸው ሰማያዊውን ምሥጢር ጊዜያዊ ጥቅም ለማግኘት ለሚሞክሩ ሲሞናውያን ነው። ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ኤጲስ ቆጶሳትን የምትሾመው ምእመናንን ከአውሬ እንዲጠብቁ ለኖላዊነት ነው። ኖላዊደግሞ በበር የሚገባ ጠባቂ፣ ነፍሱን ስለበጎቹ አሳልፎ የሚሰጥ ዋስ፣ “ደጃፍ የመለሰውን፣ ማጀት የጎረሰውን” ለልጆቹ እንደሚያወርስ አባት ነው። መንፈሳዊ አባት ተብሎ የሽፍታ ተግባር የሚፈጽም፣ ኖላዊነቱን ዘንግቶ ምንደኛ የሚሆን፣ ሰማያዊውን ሢመት በጊዜያዊ ጥምቅ የሚለውጥ፣ አምላካዊውን አደራ ዘንግቶ ፈቃደ መንግሥትን ለመፈጸም የሚደክም ከሆነ ሢመት አክሊል መሆኗ ቀርቶ እሾህ ትሆናበታለች። Read more