የአስተዳደርና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ

“የአስተዋይ ልብ እውቀትን ያገኛል፥ የጠቢባንም ጆሮ እውቀትን ትፈልጋለች።” – ምሳሌ ፲፰ ፥ ፲፭

 

ሰ/ት/ቤቶች በቃለ ዓዋዲው የተደነገገላቸውን ሐዋርያዊ ተልእኮ በብቃት እንዲወጡ የመልካም አስተዳደር ክርስቲያናዊ መርሖዎችን መከተል ይጠበቅባቸዋል። በመልካም አስተዳደር እና በክርስቲያናዊ የአመራር ሥነ ምግባር የተቃኙ አስተዳደራዊ መመሪያዎችን ከማዘጋጀት ጀምሮ ከየሰንበት ት/ቤቱ የተውጣጡ በጎ ፈቃደኛ አገልጋዮችንም ሆነ የሙሉ ጊዜ ተቀጣሪ አገልጋዮችን መመልመል እና አስፈላጊውን ሥልጠና መስጠት፣ የሥራ ዝርዝር መመሪያ ቀርጾ በየሥራ ዘርፉ መደልደል፣ አስፈላጊውን የገንዘብ እና ቁሳዊ ግብዓቶችን ማደራጀት ማስተባበር እና ማስተዳደር፣ አፈጻጸማቸውን መገምገም የመሳሰሉት አስተዳደራዊ ሥራዎች የመንበረ ፓትርያርክ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ የአስተዳደር እና የፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሜቴ ከሚያከናውናቸው ዋና ዋና ተግባራት መካከል ይጠቀሳሉ።

ይህ ክፍል እነዚህን እና ተያያዥነት ያላቸውን አገልግሎቶች በመላው ዓለም ከመንበረ ፓትርያርክ የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ እስከ አጥቢያ ሰ/ት/ቤት ድረስ በተዘረጋው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች መዋቅራዊ አደረጃጀት ውስጥ በማስፈጸም የሰ/ት/ቤት አባላት በሰ/ት/ቤት ቆይታቸው የመልካም አስተዳደር እና የመሪነትን ክህሎት እየቀሰሙ የሚያድጉበትን የአገልግሎት ዕድል ለማመቻቸት ይጥራል።

በፌስቡክ ያግኙን