ጸሎታቸው የሚጠቅም ውግዘታቸው የሚጎዳ

ጸሎታቸው የሚጠቅም ውግዘታቸው የሚጎዳ

ጸሎታቸው የሚጠቅም ውግዘታቸው የሚጎዳ

ጸሎታቸው የሚጠቅም ውግዘታቸው የሚጎዳ

ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ ከመንፈሳዊ ብቃት ደረጃ ላይ የደረሰ አባት መሆኑን መጻሕፍት ይመሰክሩለታል። መንፈሳዊ ሕይወቱን ሢመት ያላደበዘዘበት፣ በዘመኑ ከተነሣ ኑፋቄ ጋር ሲጋደል የኖረ አባት ነው። በጣም መንፈሳዊ በመሆኑም አምላኩን በጸሎት ጠይቆ ሊሞት ለነበረ አንድ ካህን ዕድሜ እንዲጨምርለት አድርጓል። እንደ ኢያሱ ፀሐይ ከመግባት እንድትዘገይ አድርጓል (ድርሳነ ቄርሎስ ገጽ፣ ፫-፭)። ቅዱስ ቄርሎስ መናፍቃንን ቀጥቅጦ የሚያደቅ መዶሻ መሆኑን የምትመሰክረው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳትሆን ፈላስፎች ጭምር መሆናችን በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የዶግማ መምህር የነበሩት ቀሲስ ዶክተር ዮሴፍ ያዕቆብ ክፍል ውስጥ ደጋግመው ይናገሩ ነበር።
በፎክሎርና ሥነ ጽሑፍ ትምህርት ክፍል “ዘመን አይሽሬ የግእዝ ሥነ ጽሑፍ” የተሰኘውን ትምህርት ለማስተርስ ተማሪዎች ያስተምሩ የነበሩት ዶክተር ዮናስ አድማሱ የቅዱሱን ድርሰት ለማስተማሪያ እንዲሆን አባዝተው ለተማሪዎቻቸው ይሰጧቸው ነበር። ቅዱስ ቄርሎስን ያሳደገው የእናቱ ወንድም አጎቱ ቅዱስ ቴዎፍሎስ ዘእስክንድርያ ነው። መንፈሳዊ ትምህርትን ከተግባራዊ ክርስትና ጋር እየተማረ ያደገው በእስክንድርያ መንበረ ፕትርክና ውስጥ ነው። አጎቱ ቅዱስ ቴዎፍሎስ ከዚህ ዓለም ድካም ሲያርፍ በየሀገረ ስብከቱ የነበሩ ጳጳሳትና የእስክንድርያ ክርስቲያኖች ፓትርያርክ እንዲሆን መርጠው አሾሙት።
ቅዱሱ አባት መንፈሳዊ ዕውቀት፣ ከጽኑ መንፈሳዊ ተጋድሎ ጋር የሠመረለት፣ ሃይማኖት ከምግባር ጋር የተዋሐደለት ነበር። እርሱ የእስክንድርያ ፓትርያርክ በሆነበት ዘመን ንስጥሮስም በቍስጥንጥንያ መንበር ላይ ፓትርያርክ ሆኖ ተሾመ። መናፍቃን ሹመት ሲያገኙ ደብቀውት የኖሩትን ኑፋቄ ማውጣት መገለጫቸው በመሆኑ ንስጥሮስም ሲሾም በድርያድርስ ተጽፎ ዕቃ ቤት የነበረን ጽሑፍ አግኝቶ በማንበብ “ደግ ሃይማኖት ነው” ብሎ በውስጡ ደብቆት የኖረውን ኑፋቄ በገሀድ ማስተማር ጀመረ። መናፍቃን ሹመት ሲያገኙ ደብቀውት የኖሩትን ኑፋቄ የሚያወጡት አንድም ሥልጣን ስለያዝን ማን ይነካናል በማለት ሲሆን ሁለትም እነርሱን ያህል አባቶች ጥቅም ባያገኙበት ኖሮ ሃይማኖታቸውን በቀላሉ አይቀይሩም ነበር በማለት የዋሃን እንዲከተሏቸው በማሰብ ነው።
የንስጥሮስን ድርጊት የሰማው ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ ድርጊቱን የፈጸመው ራሱ ንስጥሮስ መሆኑን ዕያወቀ ሌላ ሰው የፈጸመው አስመስሎ እንዲህ ያለ ክሕደት የሚያስተምር ሰው በሀገረ ስብከትህ አለና መርምር ብሎ ይልክበታል። ንስጥሮስም በሀገረ ስብከቴ አንተ ያልከውን አይነት ኑፋቄ የሚያስተምር ሰው የለም ብሎ መልሶ ይልክበታል። ትንሽ ቆይቶ እንደ ገና እንዲህ ያለ ኑፋቄ የሚያስተምር ሰው በሀገረ ስብከትህ አለና አጣራ ብሎ ይልክበታል። እርሱ ግን የለም ብሎ መልስ ሰጥቶ ኑፋቄውን በዐደባባይ ማስተማሩን ይቀጥላል።
ሦስተኛም ሲልክበት ከእርሱ ኑፋቄ ይከፋል ብሎ ያሰባቸውን መናፍቃን ስም ጠርቶ እኔ እንደ እነርሱ አላስተማርኩም። አንተ የጠቀስከውን አይነት ትምህርት ባስተምር ምንድን ነው ጥፋቴ አይነት መልስ ይሰጠዋል። ቅዱሱ አባት እንደ ገና በዘመኑ የምሥራቅ ሮማ ግዛት ንጉሥ ወደ ነበረው ወደ ታናሹ ወይም ዳግማዊ ቴዎዶስዮስ እንዲህ ያለ ኑፋቄ የሚያስተምር ሰው በግዛትህ አለና አጣራ ብሎ ይልክበታል። መልእክቱንም ለንጉሡ ብቻ ሳይሆን በንጉሡ ላይ ጫና እንዲያሳድሩ ለንጉሡ እኅትና ለልጁ ይልክላቸዋል።
ጉዳዩን አጣርቶ የደረሰበት ዳግማዊ ቴዎዶስዮስም ቅዱስ ቄርሎስን አባቴ ያልከው ትክክል ነው። ንስጥሮስ የጠቀስኸውን ኑፋቄ በማስተማር ላይ ነው ብሎ ነገረው። በመቀጠልም አባቴ ጉባኤ ልጥራልህና ተከራከሩ አለው። ቅዱሱ አባትም በንጉሡ አሳብ ተስማማ። በዚህ ምክንያት በ፬፴፩ በቍስጥንጥን ጉባኤ ተደረገ። ቅዱስ ቄርሎስ ጉባኤ ወደ ተጠራበት ቍስጥንጥንያ ሲሄድ ጳጳሳትን ብቻ ሳይሆን የገዳም አባቶችን ጭምር ይዞ ነበር የሄደው። ቅዱሱ እንዲህ ያደረገበት ምክንያት በበረሃ በተጋድሎ የሚኖሩ አባቶች በጸሎት እንዲያግረዙት ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም ከመካከላቸው ለፓትርያርክነትም ሆነ ለጵጵስና የሚያበቃቸው አባቶች ቢኖሩ በጉባኤ መልስ መስጠት እንዲማሩ በማሰብ ነበር።
ቅዱስ ቄርሎስ ይዟቸው ከሄዳቸው ገዳማውያን አባቶች አንዱ ከመንፈሳዊ ብቃቱ የተነሣ ደመና ጠቅሶ ይጓዝ እንደ ነበር ከመጋቢት እስከ ጷግሜን የሚነበበው መጽሐፈ ስንክሳር ያስነብበናል። የቅዱሱ አባት መንፈሳዊ ብቃትም ከጉባኤ ቍስጥንጥንያ በኋላ ተፈጽሞ ታይቷል። ይኸውም ጉባኤው ተጠናቆ ሁሉም ወደየመጣበት ሲመለስ ቅዱሱ አባት ለብሶት የነበረው በጣም የተበጣተሰ ልብስ መሆኑን የተመለከቱ መርከበኞች ቆሻሻ ልብስ ለብሰህ ከታላላቅ አባቶች ጋር መሄድ አትችልም ብለው በመርከብ ከመሳፈር አስቀሩት። መርከበኞቹ የፈጸሙትን ድርጊት ቅዱስ ቄርሎስ አላወቀም ነበር። ፓትርያርኩ የተሳፈረባት መርከብ ከባሕሩ መሐል ስትደርስ በመርከብ እንዳይሳፈር የተከለከለው አባት በደመና ተጭኖ በመርከቧ አናት ላይ ሲያልፍ የተመለከተው ቅዱስ ቄርሎስ አባቴ በጸሎት አስበኝ በማለት ተማጸነው። በሌላ በኩል ማለፍ ሲችል እግዚአብሔር ይህን ያደረገው መርከበኞቹ እንዲያምኑ ነበር። ያም አባት ዕለቱን ከገዳሙ ገብቶ ከመነኰሳት ጋር በጸሎት ተሳትፏል።
በንጉሡ አሳብ አቅራቢነት ለተጠራው ጉባኤ ሊቀ መንበሩ ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ ነበር። ቅዱሱ አባት ንስጥሮስን መልስ አሳጥቶ ከረታው በኋላ ወደ አማናዊቷ ሃይማኖት እንዲመለስ አባቶች ቢለምኑትም ንስጥሮስ ግን ፈቃደኛ ሳይሆን ቀረ። በዚህ ምክንያትም ንስጥሮስ ወደ ላዕላይ ግብፅ ተጋዘ (ድርሳነ ቄርሎስ በሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስ፣ ገጽ ፫-፭)። መናፍቁ ንስጥሮስ በላዕላይ ግብፅ ከተጋዘ በኋላም ቢሆን ቅዱስ ቄርሎስ ደጋግሞ “እመቤታችንን ወላዲተ አምላክ፣ ጌታችንን መድኃኒታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ደግሞ አምላክ ወሰብእ” ብሎ እንዲያምን ከልመና ጋር መልእክት ይልክበት ነበር። ንስጥሮስ ግን “የያዝኩት ተስማምቶኛል አልመለስም” ብሎ በክሕደቱ ቀጠለ።
ቅዱስ ቄርሎስ ንስጥሮስን ብዙ ጊዜ ለምኖት ለመመለስ ፈቃደኛ ባለመሆኑ “እመቤታችንን ወላዲተ አምላክ፣ ጌታችንን መድኃኒታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ደግሞ አምላክ ወሰብእ” ብላ ለማመን ፈቃደኛ ያልሆነች ምላስህ አትታዘዝልህ በማለት ረገመው። ወዲያውም የንስጥሮስ ምላስ ተጎልጉሎ ደምና መግል ይወጣው ጀመር። በዚህ ሁኔታ ሲሠቃይ ኖሮ ንስጥሮስ ይህን ዓለም ተሰናበተ። በደዌ በመሠቃየቱ ይህን ዓለም፣ ከአምላኩ በመለየቱት የወዲያኛውን ዓለም አጣ። የመንፈሳውያን አባቶች ጸሎታቸው እንደሚጠቅም ሁሉ ውግዘታቸው ቆርጦ የሚጥል ሰይፍ መሆኑን ከቅዱስ ቄርሎስና ከንስጥሮስ ታሪክ እንረዳለን።
በዘመናችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን የሚመሩ አባቶችም እንደ ቅዱስ ቄርሎስ ቢሆኑ አገር ትጠቀማለች። በዚህ ዘመን ፈልጋ መሾም የሚገባትም እንደ እርሱ ያሉትን አባቶች ነው። ቅዱስ ቄርሎስን የመሰሉ አባቶችን ማግኘት የሚቻለው ከልሂቅ እስከ ደቂቅ ክርስቲያኖች ሁሉ ጸሎት በመያዝ አምላካቸውን እንዲማጸኑ በማድረግ ነው። እኛ ከለመንነው “ለምኑ ይሰጣችኋል” ብሎ ቃል የገባልን አምላክ የፈቀድነውን ሊሰጠን የታመነ ነው።

“ልባችሁ በጸጋ ቢጸና መልካም ነው እንጂ በመብል አይደለም” ዕብ. ፲፫፡፱

“ልባችሁ በጸጋ ቢጸና መልካም ነው እንጂ በመብል አይደለም” ዕብ. ፲፫፡፱

“ልባችሁ በጸጋ ቢጸና መልካም ነው እንጂ በመብል አይደለም” ዕብ. ፲፫፡፱

“ልባችሁ በጸጋ ቢጸና መልካም ነው እንጂ በመብል አይደለም” ዕብ. ፲፫፡፱

በቅርቡ የመስኖ ፕሮጀክት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ጉዳዩ ጋር ግንኙነት የሌለውን ጥናት በመጥቀስ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው የሚከተለውን ጽሑፍ አጋርተዋል።

በግርድፉ ወደ አማርኛ ሲመለስ “ጤናማ አመጋገብ፣ የምግብ ብዝኀነት እና የምግብ ዋስትና ማኅበራዊ ጤናን፣ የሥራ ምርታማነትን፣ ጤናማ ሰብአዊ ግንኙነትን፣ ሰላምና የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማምጣት ቁልፍ ሒደቶች ናቸው። የኢትዮጵያ አመጋገብ ባህል (በተለይም የሰሜን ኢትዮጵያ) በሃይማኖት ተጽፅኖ ሥር የወደቀ ስለሆነ ጤናማ ላልሆነ አመጋገብ አጋላጭ ነው። እነዚህ ችግሮች ካልተፈቱ ወደ ብልጽግና፣ ሰላም እና መረጋጋት የሚደረገው ጉዞ ዘላቂነት አይኖረውም። ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ የሚያቃውሰው የግለሰብ ጤናን ብቻ አይደለም። ኃይልን ያዳክማል፤ ፖለቲካዊ ውሳኔዎችን ጨምሮ ውሳኔ መስጠት ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል፣ ከሌሎች ሰዎች ጋር ያለን ግንኙነትን ያዛባል፤ ግጭቶችን ያመጣል” የሚል ነው። ይህ ስም ማጥፋት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ በግልጽ ከተቃጡ የአሳብ ጦርነቶች አንዱ ነው።

በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ አካላት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ የተለያዩ ስም ማጥፋቶችን ሲፈጽሙ ቆይተዋል። አንዳንዶቹ በዓላትን በማብዛት ለብሔራዊ ድኅነት ተጠያቂ ያደርጓታል፤ ሌሎች ለቅዱሳን ዝክር፣ ለሙታን ተዝካር ሀብት ንብረት በማባከን ይወቅሷታል፤ እነዚህ ደግሞ ጾም በማብዛት ሰዎች ጤናቸው እና የማሰብ ችሎታቸው እንዲቀንስ እንዳደረገች እየከሰሷት ይገኛሉ። ቤተ ክርስቲያን ግን ከእነዚህ ሁሉ ክሶች ነፃ ናት። ሆድን የፈጠረ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ምግብ እንደሚስፈልገው፣ እንዳዘጋጀለትም ታምናለች፣ ታውቃለች፤ ታስተምርማለች። ምግብ መብላትንም አትቃወምም። ነገር ግን “ሁሉ በአግባብና በሥርዓት ይሁን” በሚለው ክርስቲያናዊ አስተምህሮዋ ልጆቿ ለመኖር እንዲመገቡ እንጂ ለመብላት እንዲኖሩ አትፈቅድም። እንዲህ ያለው መፈክር ለመብል ብቻ ለተፈጠርን ለሚመስላቸው ነው። ምግብ ለሰው ልጅ ኑሮ አስፈላጊ ቢሆንም ሰው የተፈጠረው ከመብልና ከመጠጥ ላለፈ ዓላማ መሆኑን ዕለት ዕለት ትሰብካለች። የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ ሳይንስ ስለደገፈው እውነት፣ ስላልደገፈው ደግሞ ሐሰት የሚባል አለመሆኑን መረዳት ይገባል።  ተመራማሪዎች ጾም አስፈላጊ ስለመሆኑ፣ የሚጾሙ ሰዎች ከማይጾሙ ሰዎች ይልቅ የተረጋጉ፣ የልብና የስኳር መጠናቸውን በመጠበቅ የተሻለ ጤና ያላቸው ስለመሆናቸውና ረጅም ዕድሜ የሚኖሩ እንደሆኑ በጥናት ማረጋገጣቸውን እየመሰከሩ ባለበት ወቅት ሥልጣንን መከታ አድርጎ ጥላቻን መዝራት ተገቢ አለመሆኑን ማስገንዘብ እንወዳለን። የሰሞነኛ ክስ ምንጩ ሰበብ እየፈለጉ ኦርቶዶክሳውያንን እና ለሆዳቸው አለመፈጠራቸውን የሚያምኑትን ማሸማቀቅ ነው።

ምኞታቸውን በማኅበራዊ ብዙኃን መገናኛ ያካፈሉት ባለሥልጣን ከልጥፉ ጋር አንድ ጥናት ያያያዙ ቢሆንም ጥናቱ እርሳቸው ስለሚሉት ጉዳይ የሚጠቅሰው ነገር የለም። ጥናቱ የተሠራው በራሳቸው እና  በሌሎች ሁለት ግለሰቦች የተደረገው ጥናት “Smallholder milk market participation, dietary diversity and nutritional status among young children in Ethiopia” የሚል፣ ትኩረቱም በወተት ተጠቃሚዎች ላይ ነው። እርሳቸው ያለ ዐውዱ ቢጠቅሱትም ከተባለው ጉዳይ ጋር ፈጽሞ ግንኙነት የለውም። ደግሞስ ጾም የሚጾሙ በአብዛኛው ከዐሥር ዐመት በላይ የሆኑ ሰዎች ናቸው። ሕፃናት ከእንስሳት ተዋጽዖ አይከለከሉም። የተመጣጠነ ምግብ መመገብም በሃይማኖት የተከለከለ አይደለም። ስለሆነም አቅርቦቱ በሌለበት፣ ብዙዎቹ ከእጅ ወደ አፍ ኑሮ እየገፉ የሚበሉት አትተው በሚሰቃዩበት አገር የተመጣጠነ ምግብ የማይመገቡት በሃይማኖቱ እንሌመገቡ ስለተከለከሉ ነው የሚል አሳብ ማቅረብ ሃይማኖቱን መጥላት፤ ሕዝብንም መናቅ ነው። ባለሥልጣኑ ሃይማኖትን ለመንቀፍና ቤተ ክርስቲያንን ለመውቀስ ብቻ የራስን አሳብ ያለ ማስረጃና ማረጋገጫ እንደ ተጨባጭ እውነት ማቅረባቸው በእጅጉ የሚያስነቅፍ ነው።

በቅዱሳን መጻሕፍት ብዙ ቅዱሳን ያለ ምግብ ወይም መናኛ ምግብ በመመገብ አገርንም ቤተ ክርስቲያንንም በሰላም ሲመሩ ኖረዋል። እንዲያውም ክርስትና ከድሎትና ከምቾት ጋር ስምም አይደለም። ከቅዱሳን ሐዋርያት ጀምሮ ሐዋርያውያን አበው፣ ዐቃብያነ እምነት፣ ቅዱሳን ሊቃውንት፣ ቅዱሳን ሰማዕታት እና ቅዱሳን ጻድቃን አልጫን ዐለም በቅድስና ሕይወታቸው ያጣፈጡት የላመ የጣመ እየበሉ አይደለም። በብሉይ ኪዳንም በ፳፯ አገሮች ላይ የተሾመው ነቢዩ ዳንኤል ይህን የመሪነት ሥራውን ያከናውን የነበረው “ሐሰተኛ ምሁራን” እንደሚሉት የተመጣጠነ ምግብ እየተመገበ ሳይሆን የንጉሡ ምግብ እንዳያረክሰው በማሰብ ቆሎ እየቆረጠመ ነበር። ለዐሥር ቀን ቆሎ እየቀመሱ የሰነበቱት ሠለስቱ ደቂቅ ንጉሡ እንዲመገቡ ካዘዘው  ይመገቡ ከነበሩት አምሮባቸውም፣ በአእምሮ ልቀውም መገኘታቸው ጤና የሚጠበቀው በምግብ ሳይሆን ምግብን በፈጠረ እግዚአብሔር መሆኑን የሚያስገነዝብ ነው።

ጌታችን አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገዳመ ቆሮንቶስ ከቆመበት ሳያርፍ፣ ከዘረጋበት ሳያጥፍ ለአርባ ቀናት መጾሙ፣ ስንጾምም እንዴት መጾም እንዳለብን ማስተማሩ ጾም ለሰው ልጆች አስፈላጊ መሆኑን መግለጹ ነው። በኦርቶዶክሳውያን ዘንድ የጾም አስፈላጊነት ክርክር የማይነሣበት ዶግማ ነው። የሰይጣንን ፈተና ድል ለመንሣትም ዋና መሣሪያችን መሆኑን ሁልጊዜ ስለ ምግብ እንድናስብ በማድረግ፣ በመብል ሊጥለን የሚፈልግ ዲያብሎስ የመብል ፈተና ሲያቀርብለት “ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም፤ ተብሎ ተጽፏል” (ማቴ. ፬፡፬) በማለት አሳፍሮ አሳይቶናል። ስለሆነም ስለ ምግብና ስለ ሆድ ማሰብ ሞት ነው። እንዲያውም ሆድ በሞላ ቁጥር አእምሮ የማሰብ አቅሙ እየቀነሰ ይሔዳል። አብዛኛዎቹ የዐለም ፈጠራዎች ችግርና ማጣት የወለዳቸው ናቸው። ሰው ሁሉም ነገር ከተሟላለት የማሰብም ሆነ የመሥራት ፍላጎት አይኖረውም።

የኢትዮጵያ አብዛኛው ሕዝብ ባለሥልጣናቱ እንደሚያወሩት የተመጣጣነ ምግብ የሚያውቅ፣ በቀን ሦስት ጊዜ የሚመገብ አይደለም። ነገር ግን ከሌሎች ጋር ተሳስቦና ተግባብቶ የመኖር ችግር የለበትም። የማሰብም ሆነ ውሳኔ የመስጠት ጉድለት የለበትም። እንዲያውም በተቃራኒው መርጠው የሚመገቡትና በተመጣጠነ ምግብ ሰበብ መብልን ሥራቸው ያደረጉ ሹማምንት የሚሰጡት ውሳኔ ነው አገር ሲያጠፋ የሚታየው። የሚመሩትን ሕዝብ ማወቅ፣ ያለበትንም የኑሮ ደረጃ መገንዘብ ብዙ ከመሳት ይጠብቃል። የአገር ዕድገት በመሪዎች ሀብትና ቅንጡ አኗኗር አይመዘንም። በኢትዮጵያ የተመጣጠነ ምግብ ያለው ትምህርት ቤት ከመምህራን አፍ፣ በቴሌቪዥን መስኮት ከዝግጅት አቅራቢዎች እና በዐደባባይ ከባለሥልጣናት ንግግር ብቻ ነው። በገጠሩ የሚኖረው ማኅበረሰብ ባለማግኘት፣ ያለውም ቢሆን ከመብል ጋር ያለው አስተሳሰብ ከመኖር ጋር ብቻ የተያያዘ ስለሆነ ስለ ተመጣጠነ ምግብ ጉዳዩ አድርጎ አያስብም፤ አይበላምም። ይህ የተሠራበት እሴት በሕይወቱ ላይ ያመጣበት ችግር የለም። ጾሙንም እንደ ጫና ሳይሆን እንደ በረከት የሚቆጥረው ተረድቶት ነው። ቤተ ክርስቲያን ያለ ጥናት እንደሚናገሩት አካላት የተመጣጣነ ምግብ መመገብን አትከለክልም። ማግበስበስን ግን ትጸየፋለች።

ይህን የምታስተምረው ደግሞ እንደ እንግዳ ደራሽ፣ እንደ ውኃ ፈሳሽ መሠረት የሌለው ሳይሆን ከአምላኳ የተቀበለችው፣ ከሐዋርያት የተረከበችው ነው። ጌታችን በወንጌል “ለሚጠፋ መብል አትሥሩ፤ ነገር ግን ለዘላለም ሕይወት ለሚኖር መብል የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ሥሩ” (ዮሐ. ፮፡፳፯) በማለት ሰው ሊሠራ የሚገባው አላፊ ለሆነው ዐለም ምግብ ብቻ ሳይሆን የዘላለም ሕይወቱን እያሰበ እንዲኖር ነው። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም “መብል ለሆድ ነው፤ ሆድም ለመብል ነው፤ እግዚአብሔር ግን ይህንም ያንም ያጠፋቸዋል” (፩ኛ ቆሮ. ፰፡፰) በማለት ሆድም መብልም እንደሚጠፉ ነግሮናል። አብዝቶ መብላት መጠጣት ወደ ጥጋብና እግዚአብሔርን ወደ መርሳት ያደርሳል። “ይሹሩ ወፈረ፣ ረገጠ፤ ወፈረ፣ ደነደነ፣ ሰባ፤ የፈጠረውንም እግዚአብሔር ተወ፤ የመድኀኒቱንም አምላክ ናቀ” (ዘዳ. ፴፪፡፲፭) የሚለው የመጽሐፍ ቃል የሚያስረዳን ይህኑ ነው። ስለሆነም ስለ ሥጋ ማሰብ፣ ስለ መብልና መጠጥ ብቻ ማስብ “ሊበሉና ሊጠጡ ተቀመጡ፣ ሊዘፍኑ ተነሡ” (፩ኛ ቆሮ. ፲፡፯) ተብሎ እንደተጻፈ እግዚአብሔርን መርሳትና ሞት ነው።

በመንፈስ ቅዱስ የተቃኙ አባቶች

በመንፈስ ቅዱስ የተቃኙ አባቶች

በመንፈስ ቅዱስ የተቃኙ አባቶች

በመንፈስ ቅዱስ የተቃኙ አባቶች

የመንፈስ ቅዱስ መሰንቆ የቃኛቸው አባቶች በመንፈሳዊ ሥልጣን ላይ ሲቀመጡ ራሳቸውንም ሌሎችንም ይጠቅማሉ። በመንፈስ ቅዱስ የተቃኙ አባቶች በፈቃደ እግዚአብሔር ስለሚመሩ ክርስቲያኖች ሁሉ እግዚአብሔር በሚፈቅደው መንገድ እንዲጓዙ ያደርጋሉ። እንዲህ ማድረጋቸው ሃይማኖት እንዲጸና ቀኖና ቤተ ክርስቲያን እንዲጠበቅ ሳይታክቱ ይሠራሉ። መሥራት ብቻ ሳይሆን ራሳቸው አርአያ ሆነው ፈጽመው ያሳያሉ። Read more

የነገረ ሰብእ ትምህርት ጉድለት የወለደው አገራዊ ቀውስ

ከወርቃማው ሕግ አትንሸራተቱ (የነገረ ሰብእ ትምህርት ጉድለት የወለደው አገራዊ ቀውስ ክፍል ሁለት)

የነገረ ሰብእ ትምህርት ጉድለት የወለደው አገራዊ ቀውስ

የነገረ ሰብእ ትምህርት ጉድለት የወለደው አገራዊ ቀውስ

የተከበራችሁ የማኅበራዊ ሚዲያችን ተከታታዮች አስቀድምን ባስነበብነው የዚህ ጽሑፍ የመጀመሪያ ክፍል ሰው በእግዚአብሔር አርአያ እና ምሳሌ የተፈጠረ የፍጥረታት ንጉሥ፣ ከሌሎች ፍጥረታት ተለይቶ ዐዋቂ እና ሕያውነት ያለው፣ በፍጥረታት ላይ የሠለጠነ ባለጸጋ ፍጡር መሆኑን አቅርበን ነበር። በዚህም ምክንያት ሰው ነጻ ፈቃዱን ተጠቅሞ ሲጠፋ ከሦስቱ አካላት አንዱ ወልድ “እስመ በፈቃዱ፣ ወበሥምረተ አቡሁ ወመንፈስ ቅዱስ መጽዐ አድኀነነ” እንደ ተባለው ሰው ሆኖ ሰውን ከውድቀት አነሣው። ዘጠና ዘጠኙን ነገደ መላእክት ትቶ አንዱን ነገድ ሰውን ለመፈለግ ሰው የሆነው ለሰው ካለው ጽኑ ፍቅር የተነሣ ነው። Read more

ብሔር ተኮር ሃይማኖታዊ ስብከት

ብሔር ተኮር ሃይማኖታዊ ስብከት

ብሔር ተኮር ሃይማኖታዊ ስብከት

ብሔር ተኮር ሃይማኖታዊ ስብከት

ቤተ ክህነቱ ታሟል

ጎሣን መሠረት ያደረገው የሀገራችን ፖለቲካ ኢትዮጵያዊነት ዕሴቶችን በማፈራረስ ሀገር የቆመበትን መሠረት ለመናድ መዶሻውን ካነሣ ምእተ ዓመት ሊያስቆጥር የመጨረሻው ሩብ ክፍለ ዘመን ብቻ ቀርቶታል፡፡ በሀገረ ምሥረታው ሒደት ምትክ የለሽ ሚና የተጫወተችውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጥፋቱ ሰለባ የሆነችው ገና ከጅምሩ ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን አሐቲነት አደጋ ላይ የወደቀበት እና በከፋ የፈተና ማዕበል እየተናጠች የምትገኝበት ዘመን ላይ መሆናችን ፀሐይ የሞቀው እውነት ነው፡፡ Read more

የአዲስ አበባ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት በ2015 ዓ.ም በ4 በ6ና በ10ኛ ክፍል ያስተማራቸውን ከ4500 በላይ ተማሪዎች አስመረቀ

ጥቅምት 04 2016 ዓ.ም (የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት)

የአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት በ2015 ዓ.ም በ4 በ6 እና በ10ኛ ክፍል በተዘጋጀው ሥርዓተ ትምህርት ያስተማራቸውን ተማሪዎች በዛሬው ዕለት በደብረ ምጥማቅ ሰዓሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም እና ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ካቴድራል አስመረቀ። በመርሐ ግብሩ ላይም ብጹዕ አቡነ አብርሃም የባህርዳር ሀገረስብከት ሊቀጳጳስና የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ የሰሜን አሜሪካ የኒውዮርክ ሀገረስብከት ሊቀጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብጹዕ አቡነ ቀለሜንጦስ የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከትና የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ሊቃነ ጳጳሳት የጠቅላይ ቤተክህነት መምሪያ ኃላፊዎች የጠቅላይ ቤተክህነት የየመሪያው ኃላፊዎች ፤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት እና የክፍለ ከተማ ቤተክህነት የየክፍሉ ኃላፊዎች የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ አመራሮች ተመራቂ ተማሪዎችና ወላጆቻቸው በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ውሏል።

የምርቃት መርሐ ግብሩ ልጅህን በሚሄድበት መንገድ ምራው በሸመገለም ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም በሚል መሪ ቃል የተከበረ ሲሆን በመጀመሪያ በብጹዕ አቡነ ቀለሜንጦስ መሪነት በጸሎተ ወንጌል ተከፍቷል። በመቀጠልም በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ሰብሳቢ ላዕከ ኄራን መንክር ግርማ የመግቢያ ንግግር የተደረገ ሲሆን በንግግራቸውም በአዲስ አበባ ከሚገኙ 250 አድባራት 157 የሚሆኑት በ2015 ዓ.ም ሥርዓተ ትምህርቱን መተግበራቸውንና በዛሬው ዕለት ግን 77 የሚሆኑ አድባራት በአንድ ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ እርከኖች ተማሪዎቻቸውን ማስመዘናቸውን ገልጸዋል። በዚህም ከተፈተኑት 4500 ተማሪዎች ውስጥ 4030 የሚሆኑት ወደ ቀጣይ ክፍል መዘዋወራቸውን አብስረዋል። በ2016 ዓ.ም በ205 ደብራት 72,000 በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት እንዲማሩ እንደ እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

የዕለቱን ወንጌል የሰንበት ትምህርት ቤት ፍሬ የሆኑት ዲያቆን ህሊና በለጠ “እኔ የሳሮን ጽጌሬዳ የቆላም አበባ ነኝ” መኃ 2:1 በሚል ቃል መነሻነት ቃለ እግዚአብሔር አስተላልፈዋል። በመቀጠልም ብጹዕ አቡነ አብርሃም ለተመራቂ ተማሪዎችና ለወላጆች የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል። በመልዕክታቸውም “የሳንቲም ውርስ ልጆችን ያጋጫል የሃይማኖት የእውቀት የምግባር ውርስ ግን እስከ መጨረሻው ለወላጆች የሚጠቅሙ ሀገርን ሀገር የሚያሰኙ የነገዋን ቤተክርስቲያንን የሚገነቡ ተስፋዎች ያደርጋችዋል። ስለዚህም ቤተክርስቲያንን እንጠብቃት እንታዘዛት አገልግሎታችሁ ከጥቅማ ጥቅም የተነሳ ሳይሆን በነጻ የምታገለግሉበት ነውና ብዙ ጸጋና ሀብትን ይሰጣችኋል በዚህም ቤተክርስቲያናችሁ እጅግ ትደሰታለች።” ሲሉ አባታዊ ቡራኬያቸውን ሰጥተዋል።

በመጨረሻም የሽልማትና የምስጋና መርሐግብር የተካሄደ ሲሆን ከ77 አድባራት በብዙ የተማሪዎች ቁጥር ያስፈተኑንና ከተፈተኑት ውስጥ የደረጃ ተማሪዎች የነበሩትን ከብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት እጅ የማበረታቻ ሽልማት ተሰቷቸዋል። በብጹዕ አቡነ ቀለሜንጦስ የመጨረሻ አባታዊ ቡራኬ እና መልእክት የመርሐ ግብሩ ፍጻሜ ሆኗል።

(የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት)

✍️YouTube 👇
https://www.youtube.com/@eotc-gssu
✍️ FaceBook 👇
https://www.facebook.com/EOTC.GSSU
✍️Telegram 👇
https://t.me/EOTCNSSU
✍️Website👇

✍️Tiktok👇

@sundayschoolunion

 

የነገረ ሰብእ ትምህርት ጉድለት የወለደው አገራዊ ቀውስ

የነገረ ሰብእ ትምህርት ጉድለት የወለደው አገራዊ ቀውስ

የነገረ ሰብእ ትምህርት ጉድለት የወለደው አገራዊ ቀውስ

የነገረ ሰብእ ትምህርት ጉድለት የወለደው አገራዊ ቀውስ

በቤተ ክርስቲያን ትምህርት ነገረ ሰብእ (አንትሮፖሎጂ) አንደኛው የጥናት ዘርፍ ነው። ይህ የጥናት ዘርፍ ስለ ሰው አፈጣጠርና ክብር የሚናገር ነው። ስለ ፍጥረት አመጣጥ የሚናገረው የመጽሐፍ ቅዱስ የመጀመሪያው መጽሐፍ ኦሪት ዘፍጥረት ሰው በእግዚአብሔር አርአያና ምሳሌ የተፈጠረ ክቡር ፍጡር መሆኑን ይነግረናል። ሊቀ ነቢያት ሙሴ ስለ አፈጣጠሩ ሲተርክልንም “እግዚአብሔርም አለ፤ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፣ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፣ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ፡ እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው” (ዘፍ. ፩፡፳፮-፳፯) ይለናል። የሚወዱትን እንግዳ ሁሉን አዘጋጅቶ እንደሚጠሩት እግዚአብሔርም ለሰው የሚያስፈልገውን ሁሉ አስቀድሞ ካዘጋጀ በኋላ ሰውን የፍጥረት መደምደሚያና መካተቻ አድርጎ ፈጥሮታል። እግዚአብሔር ሌሎች ፍጥረታትን በኀልዮ (በማሰብ) እና በነቢብ (በመናገር) ሲፈጥራቸው ሰውን ግን በእጁ ሠርቶታል። “እግዚአብሔር አምላክ ሰውን ከምድር አፈር አበጀው፤ በፊቱም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ” (ዘፍ. ፪፡፯) የተባለው ለዚህ ነው። ስለሆነም ሰው ክብሩና ልእልናው ከፍ ያለ ነው። Read more

የዩክሬን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ዮናታን እስር

የዩክሬን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ዮናታን እስር

የዩክሬን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ዮናታን እስር

የዩክሬን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ዮናታን እስር

ሊቀ ጳጳስ ዮናታን በዩክሬን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የተልኪና ብራስላቭ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ናቸው። የሀገሪቱ መንግሥት ዩክሬን የምትመራበትን ወንጀለኛ መቅጫ ሕግ አንቀጽ 109፣ 110፣ 161 እና 436 (2) በመጥቀስ በአራት ወንጀሎች ጠርጥሬያቸዋለሁ በማለት ክስ ይመሠርትባቸዋል። ጉዳዩን በአግባቡ ለመረዳት ሊቀ ጳጳሱ የተከሰሱባቸው የወንጀል ሕጉ ድንጋጌዎች ምን ምን እንደሚሉ አስቀድመን እንመለከታለን።

  • አንቀጽ 109 በዐመጽ ለውጥ ለማምጣት ወይም ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለማስወገድ ወይም በኃይል ሥልጣን ለመያዝ የሚፈጸሙ ተግባራት
  • አንቀጽ 110 – የዩክሬንን ሉዓላዊ የግዛት ወሰን ማለፍ ወይም ዳር ድንበሯን ለመለወጥ አስቦ መሥራት
  • አንቀጽ 161 – ዘርን፣ ሃይማኖትን እና ዜግነትን መሠረት በማድረግ ልዩነት መፍጠር
  • አንቀጽ 463 (2) – የጦርነት ፕሮፖጋንዳ መንዛት (ሩሲያ በዩክሬን ላይ የፈጸመችውን የኃይል ወረራ አይቀበሉም፣ ለሕጋዊነቱ ዕውቅና ሰጥተዋል፤ የሩሲያ ወታደሮችን አድንቀዋል) የሚሉ ናቸው።

Read more

“ክርስቲያኖች መተት አደረጉብን”

“ክርስቲያኖች መተት አደረጉብን”

“ክርስቲያኖች መተት አደረጉብን”

“ክርስቲያኖች መተት አደረጉብን”

መቼም በየዘመኑ የማይሰማ ጉድ የለም። ከመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን አንሥቶ በየሀገሩ ይኖሩ የነበሩ አረማውያን እና አሕዛብ ክርስቲያኖችን ተከራክረው ማሸነፍ እንደማይቻላቸው ሲረዱ አንድ መላ ዘይደው ነበር። ይኸውም “ክርስቲያኖች የሰው ሥጋ ይበላሉ” ብለው በማስወራት ስለክርስትና የማያውቁ የሰው ልጆች እንዲርቁ በሌላ በኩልም ሃይማኖቱ ሕገ ወጥ ተብሎ ከምድረ ገጽ እንዲጠፋ ማስደረግ ነበር። ይህም ሐዋርያት ወንጌልን ለመላው ዓለም ለማዳረስ በሚሰማሩባቸው ቦታዎች ሁሉ እንደ በግ እንዲታረዱ የሱ ምክንያት ነበረው። የአረማውያኑ አሳብ መከራውን ተሰቅቀው ሌሎች እንዲሸሿቸው ማድረግ ቢሆንም ውጤቱ ግን በተቃራኒው ነበር። Read more

እነርሱ እያቃጠሉ እኛ ስንሠራ አንኖርም

እነርሱ እያቃጠሉ እኛ ስንሠራ አንኖርም

ዘመናችን “መታዘዝ እንደ ድካም፣ ትሕትና እንደ ውርደት፣ ራስን መግዛት ራስን እንደ መጨቈን፣ በሥርዓት ማደር እንደ ኋላ ቀርነት፣ ክህነታዊ ተዋረድን የጠበቀ አገልግሎት ዘመን እንዳለፈበት የጭቆና መሣሪያ፣ ሃይማኖተኛነት እንደ ተራ ወግ አጥባቂነት ተፈርጆ ይዘመትበታል፡፡ ነባር ሃይማኖትን መቃወምን እንደ ሃይማኖት የያዘ መስተጻርርነት አየሩን ሞልቶታል” በማለት በአማን ነጸረ የጻፈው በተግባር ተገልጦ የሚታይበት ነው። ፀረ -ኦርቶዶክሶችም ይባል አክራሪዎች በኦርቶዶክሳውያን እንደሚሸነፉ ሲረዱ እግር ላይ ወድቀው የሚለምኑት በኦርቶዶክሳውያን መልካም ዕሴት ላይ ተሸጋግረው አዘናግተው ለማጥቃት ወይም ጊዜ ለመግዛት እንጂ በሚልኩት ሽምግልናም ሆነ በሚያቀርቡት ተማጽኖ አምነውበት አይደለም።
የአክራሪዎች መርሕ ራስ ብቻ ደኅና የሚል ነው። የራሳቸው ደኅንነት ከሌላው ደኅንነት ጭምር እንደሚመነጭ አመዛዝነው መረዳት የሚችሉበት አእምሮ የተነሣቸው ናቸው። መደጋገፍ የሚባለው አብሮ የመኖር ባህል፣ መከባበር የሚሉት መልካም ዕሴት አይገባቸውም። ሁሉ ነገር የእኛ፣ ሁሉን እኛ ይዘነው ሌላው ከገጸ ምድር ይጠፋ የሚል ነው። ለቀጣይ ትውልድ ማሰብ የሚባል ነገር አያውቁም። ሌላው የለፋበትን ነጥቆ መውሰድ ወይም ማውደም ሃይማኖት ብለው የያዙት እኩይ ድርጊት ነው። እግዚአብሔር የፈጠረውን ትውልድ በማጥፋት “የፈጠርከውን አጠፋንልህ” ብለው ለባለቤቱ ሪፖርት የሚያቅርቡ ናቸው። እንዲህ ያለው መረን የለቀቀ አስተሳሰብ ክቡር የሆነውን ፍጡር ከእንስሳ ተራ የሚያስመድብ ነው። Read more