የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት - በኢ/ኦ/ተ/ቤ የመንበረ ፓትርያርክ ሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ አንድነቱ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ተቋማዊ ራእይ፣ ተልእኮ
      • መዋቅራዊ አደረጃጀት
      • የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ተቋማዊ አደረጃጀት
      • የሰንበት ት/ቤቶች የሥራ አመራር ምርጫ ማስፈጸሚያ
    • ስልታዊ እቅድ 2018 – 2021 ዓ/ም
  • ሥርዓተ ትምህርት
    • መሠረታዊ መረጃዎች
    • የሰንበት ት/ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት አደረጃጀት መመሪያ
    • የሥርዓተ ትምህርቱ መመማሪያ መጻሕፍት ይዘት
      • የአንደኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
      • የኹለተኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
      • የሦስተኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
    • የሥርዓተ ትምህርቱ ዓመታዊ የጊዜ ሰሌዳ /ካሌንደር
    • የመምህራን ሥልጠና እና መልእክቶች
    • መጻሕፍቱን ለማግኘት እና ተጨማሪ መረጃ
    • ልዩ ልዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች
  • ፕሮጀክቶች
  • መዝሙረ ማኅሌት
    • የመስከረም ወር መዝሙሮች
      • የዮሐንስ መዝሙር
      • የመስቀል መዝሙሮች
      • የብዙኃን ማርያም መዝሙር (መስከረም ፳፩ )
      • የዘመነ ጽጌ መዝሙር
    • የጥቅምት ወር መዝሙሮች
      • የአብርሃ ወአጽብሐ መዝሙር (ጥቅምት 4 ቀን)
    • የኅዳር ወር መዝሙሮች
      • የቅዱስ ሚካኤል መዝሙር (ኅዳር 12 ቀን)
    • የጥር ወር መዝሙሮች
      • የዘመነ ጥምቀት መዝሙር
      • የቃና ዘገሊላ መዝሙር (ጥር 12 ቀን)
    • የመጋቢት ወር መዝሙሮች
      • የወርኃ ጾም መዝሙሮች
      • የሆሣዕና መዝሙራት
      • የሰሙነ ሕማማት መዝሙሮች
  • ዜና
    • አጫጭር ዜናዎች
    • ዝርዝር ዜናዎች
    • ወቅታዊ መረጃዎች
    • ማስታወቂያ
      • የሰንበት ትምህርት ቤቶች መጻሕፍት እንግሊዝኛ ትርጉም ሥራ ተሳትፎ ጥሪ
  • ያግኙን
  • ቋንቋ
    • ትግርኛ
    • Afaanoromo
  • Menu Menu

የአዲስ አበባ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት በ2015 ዓ.ም በ4 በ6ና በ10ኛ ክፍል ያስተማራቸውን ከ4500 በላይ ተማሪዎች አስመረቀ

ጥቅምት 04 2016 ዓ.ም (የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት)

የአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት በ2015 ዓ.ም በ4 በ6 እና በ10ኛ ክፍል በተዘጋጀው ሥርዓተ ትምህርት ያስተማራቸውን ተማሪዎች በዛሬው ዕለት በደብረ ምጥማቅ ሰዓሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም እና ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ካቴድራል አስመረቀ። በመርሐ ግብሩ ላይም ብጹዕ አቡነ አብርሃም የባህርዳር ሀገረስብከት ሊቀጳጳስና የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ የሰሜን አሜሪካ የኒውዮርክ ሀገረስብከት ሊቀጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብጹዕ አቡነ ቀለሜንጦስ የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከትና የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ሊቃነ ጳጳሳት የጠቅላይ ቤተክህነት መምሪያ ኃላፊዎች የጠቅላይ ቤተክህነት የየመሪያው ኃላፊዎች ፤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት እና የክፍለ ከተማ ቤተክህነት የየክፍሉ ኃላፊዎች የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ አመራሮች ተመራቂ ተማሪዎችና ወላጆቻቸው በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ውሏል።

የምርቃት መርሐ ግብሩ ልጅህን በሚሄድበት መንገድ ምራው በሸመገለም ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም በሚል መሪ ቃል የተከበረ ሲሆን በመጀመሪያ በብጹዕ አቡነ ቀለሜንጦስ መሪነት በጸሎተ ወንጌል ተከፍቷል። በመቀጠልም በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ሰብሳቢ ላዕከ ኄራን መንክር ግርማ የመግቢያ ንግግር የተደረገ ሲሆን በንግግራቸውም በአዲስ አበባ ከሚገኙ 250 አድባራት 157 የሚሆኑት በ2015 ዓ.ም ሥርዓተ ትምህርቱን መተግበራቸውንና በዛሬው ዕለት ግን 77 የሚሆኑ አድባራት በአንድ ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ እርከኖች ተማሪዎቻቸውን ማስመዘናቸውን ገልጸዋል። በዚህም ከተፈተኑት 4500 ተማሪዎች ውስጥ 4030 የሚሆኑት ወደ ቀጣይ ክፍል መዘዋወራቸውን አብስረዋል። በ2016 ዓ.ም በ205 ደብራት 72,000 በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት እንዲማሩ እንደ እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

የዕለቱን ወንጌል የሰንበት ትምህርት ቤት ፍሬ የሆኑት ዲያቆን ህሊና በለጠ “እኔ የሳሮን ጽጌሬዳ የቆላም አበባ ነኝ” መኃ 2:1 በሚል ቃል መነሻነት ቃለ እግዚአብሔር አስተላልፈዋል። በመቀጠልም ብጹዕ አቡነ አብርሃም ለተመራቂ ተማሪዎችና ለወላጆች የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል። በመልዕክታቸውም “የሳንቲም ውርስ ልጆችን ያጋጫል የሃይማኖት የእውቀት የምግባር ውርስ ግን እስከ መጨረሻው ለወላጆች የሚጠቅሙ ሀገርን ሀገር የሚያሰኙ የነገዋን ቤተክርስቲያንን የሚገነቡ ተስፋዎች ያደርጋችዋል። ስለዚህም ቤተክርስቲያንን እንጠብቃት እንታዘዛት አገልግሎታችሁ ከጥቅማ ጥቅም የተነሳ ሳይሆን በነጻ የምታገለግሉበት ነውና ብዙ ጸጋና ሀብትን ይሰጣችኋል በዚህም ቤተክርስቲያናችሁ እጅግ ትደሰታለች።” ሲሉ አባታዊ ቡራኬያቸውን ሰጥተዋል።

በመጨረሻም የሽልማትና የምስጋና መርሐግብር የተካሄደ ሲሆን ከ77 አድባራት በብዙ የተማሪዎች ቁጥር ያስፈተኑንና ከተፈተኑት ውስጥ የደረጃ ተማሪዎች የነበሩትን ከብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት እጅ የማበረታቻ ሽልማት ተሰቷቸዋል። በብጹዕ አቡነ ቀለሜንጦስ የመጨረሻ አባታዊ ቡራኬ እና መልእክት የመርሐ ግብሩ ፍጻሜ ሆኗል።

(የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት)

✍️YouTube 👇
https://www.youtube.com/@eotc-gssu
✍️ FaceBook 👇
https://www.facebook.com/EOTC.GSSU
✍️Telegram 👇
https://t.me/EOTCNSSU
✍️Website👇

ቀዳሚ ገጽ

✍️Tiktok👇

@sundayschoolunion

 

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on LinkedIn
  • Share on Telegram
  • Share by Mail
https://eotc-gssu.org/a/wp-content/uploads/photo_2_2023-10-15_20-40-09.jpg 881 576 Abenezer Mamushet https://eotc-gssu.org/a/wp-content/uploads/logo-2-1-300x74-1.png Abenezer Mamushet2023-10-15 22:10:552023-10-15 22:14:11የአዲስ አበባ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት በ2015 ዓ.ም በ4 በ6ና በ10ኛ ክፍል ያስተማራቸውን ከ4500 በላይ ተማሪዎች አስመረቀ
Search Search

Recent Posts

  • የሦስተኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
  • የኹለተኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
  • የአንደኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
  • የመስቀል ደመራ በዓል በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ
  • ሦስተኛ ዙር የ፲፪ ክፍል ምርቃት መርሐ ግብር ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ በተገኙበት ተከናወነ።

Archives

  • April 2026
  • September 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • May 2025
  • April 2025
  • October 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • November 2022
  • October 2022
  • September 2022
  • July 2022
  • June 2022
  • April 2022
  • February 2022
  • January 2022
  • October 2021
  • September 2021
© Ethiopian Orthodox Church Global Sunday School Union | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
  • Link to Youtube
  • Link to Telegram
  • Link to TikTok
Link to: የነገረ ሰብእ ትምህርት ጉድለት የወለደው አገራዊ ቀውስ Link to: የነገረ ሰብእ ትምህርት ጉድለት የወለደው አገራዊ ቀውስ የነገረ ሰብእ ትምህርት ጉድለት የወለደው አገራዊ... Link to: ብሔር ተኮር ሃይማኖታዊ ስብከት Link to: ብሔር ተኮር ሃይማኖታዊ ስብከት ብሔር ተኮር ሃይማኖታዊ ስብከት
Scroll to top Scroll to top Scroll to top