ራስን በራስ መሾም በቤተ ክርስቲያን ላይ ያስከተለው መዘዝ

ራስን በራስ መሾም በቤተ ክርስቲያን ላይ ያስከተለው መዘዝ

ራስን በራስ መሾም በቤተ ክርስቲያን ላይ ያስከተለው መዘዝ

ራስን በራስ መሾም በቤተ ክርስቲያን ላይ ያስከተለው መዘዝ

ከቤተ ክርስቲያን ታሪክ የተማርነው አባቶቻችን “ኤጲስ ቆጶስ ሆናችሁ ሕዝበ ክርስቲያኑን ምሩ” ሲባሉ አደገኛ አውሬ እንዳየ የቤት እንስሳ ሸሽተው ይደበቁ ነበር። አባቶች ሢመቱን ይሸሹት የነበረው አንድም በትሕትና ሁለትም በራስ ኃጢአት ብቻ ሳይሆን በሌሎች ጥፋት መጠየቅ ስላለበት ነው። በዘመናችን የኤጲስ ቆጶስነት ግብሩ የተለየ እስከሚመስል ድረስ ራስን በራስ እስከመሾም ተደርሷል። ከዚያ መንፈሳዊ ልዕልና ወርደን ለዚህ ውድቀት የተዳረግነው የኤጲስ ቆጶስነት ዓላማውና ግብሩ በመለወጡ ነው። ቤተ ክርስቲያ ለመከራ የተዳረገችውም ምእመናንን የሚጠብቁ ሳይሆኑ ምእመናንን ለኃላፊው ነገር መጠቀሚያ የሚያደርጉ ሰዎች አባት መሆን ሳይችሉ አባት ለመሆን መጣራቸው ነው። የኤጲስ ቆጶስ ተግባርና ኃላፊነት የሚያስገነዝበው “ኤጲስ ቆጶስ ማለት የምእመናን ላዕላዊ ጠባቂ ወይም አውራ ጠባቂ ማለት ነው፤ ይህም ማለት በተመደበበት ሀገረ ስብከት የመጨረሻው የምእመናን ጠባቂ እረኛ ማለት ነው ፤ ኤጲስ ቆጶስ በሚሊዮን በሚቈጠሩ ምእመናን ላይ በመንፈሳዊ የጥበቃ አገልግሎት የተሾመ ነው። Read more

ለቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊው ለውጥ መቼ?

ለቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊው ለውጥ መቼ?

ለቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊው ለውጥ መቼ?

ለቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊው ለውጥ መቼ?

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ያልተበረዘ ክርስቶሳዊ ትምህርት ምንጭ ናት፡፡ ነቅ አልባ አስተምህሮዋ መቼም ቢሆን ለድርድር አይቀርብም፡፡ ከጥንትም መሥሯቿ ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና ፍጽምት አድርጎ ነው የሠራት። መንገድ እና ሕይወት እኔ ነኝ ያለው ጌታ የመሠረታት ሕይወት የሚገኝባት መንገድ ናት ተዋሕዶ፡፡ ሐቁ ከእርሷ የተሻለ መንገድ የለም ሳይሆን ከእርሷ ሌላ የሕይወት መንገድ የለም ነው። አስተዳደራዊ ሥርዐትን በተመለከተ ግን ነገሮች የሚከወኑበት ሁልጊዜም ከዘመን ዘመን የተሻሻለ መንገድ ይመጣል።

ሐዋርያት መጀመሪያ የክርስቲያኖች ቁጥር አነስተኛ በነበረበት ሰዓት የዘረጉትን የአስተዳደር ሥርዓት የአማኙ ቁጥር እየጨመረ ሲመጣ ቀይረውታል። ‹‹ማዕድን እናገለግል ዘንድ የሚገባ ነገር አይደለም፤›› ብለው ሁኔታውን ያገናዘበ አስተዳደራዊ ለውጥ አደረጉ። ውሳኔው የምእመናንን ሱታፌ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ከፍ ያደረገ፣ አዳዲስ የወንጌል መልእክተኞችን ወደ አገልግሎቱ የሳበ የለውጥ ውሳኔ ነበር፡፡ የክርስትናን ፋና ወጊ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስን ያስገኘ እና አገልግሎቱን ያሰፋ አስተዳደራዊ ለውጥ ነበር፡፡ Read more

ብፁዕ አቡነ አብርሃም ከትግራይ ክልል ጋር ተያይዞ ባለው ወቅታዊ ጉዳይ የሰላምና የአንድነት መልዕክት አቀረቡ

ብፁዕ አቡነ አብርሃም ከትግራይ ክልል ጋር ተያይዞ ባለው ወቅታዊ ጉዳይ የሰላምና የአንድነት መልዕክት አቀረቡ

 

ብፁዕ አቡነ አብርሃም ከትግራይ ክልል ጋር ተያይዞ ባለው ወቅታዊ ጉዳይ የሰላምና የአንድነት መልዕክት አቀረቡ

ብፁዕ አቡነ አብርሃም ከትግራይ ክልል ጋር ተያይዞ ባለው ወቅታዊ ጉዳይ የሰላምና የአንድነት መልዕክት አቀረቡ

አርብ ሐምሌ 14 ቀን 2015፤ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ችግሮች በተለይም በትግራይ ክልል ባሉ አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳትና ሊቃውንት ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን እና ከሕግ ውጭ በሆነ መልኩ ” ኤጲስ ቆጶሳትን ” እንሾማለን በማለት  እየተደረገ ያለው ዝግጅት አስመልክቶ እንዲቆምና  የውይይት መድረኮች ተመቻችተው  ችግሮችን በሰላማዊና የቤተ ክርስቲያንን አንድነት  በጠበቀ መልኩ ለመፍታት በቦታው ካሉ ሊቃነ ጳጳሳት ጀምሮ ለሊቃውንት ኦቶዶክሳውያንና ለሌሎች እምነት ተከታዮች እንዲሁም ለፌደራልና ለክልሉ መንግሥት የሰላምና የአንድነት ጥሪ ሐሙስ ሐምሌ 13 ቀን 2015 በሰጡት መግለጫ አቅርበዋል።

ብፁዕ አቡነ አብርሃም  በመገለጫቸው ጉዳዮቹን ለማጥራትና  ሁሉም አካል ወደልቡ እንዲመለስ ያለመ መሆኑን በመግለጽ  መልእክታቸውን ማስተላለፍ የቀጠሉ ሲሆን በሰሜኑ ኢትዮጵያ በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት በሞቱ  የተጎዱና ከቀያቸው በተፈናቀሉ በአጠቃላይ በደረሰው መከራና ሞት እጅግ ማዘናቸው ገልጸዋል።  ይሁን እንጂ  ጉዳዮች እዚህ ከመድረሳቸው  በፊት በሰዓቱ  አባቶች ከግል ጀምሮ እስከ ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ድረስ  የተደረጉ ሰላማዊ  ተግባራት እንደነበሩ አብራርተዋል። Read more

ይቅርታና ክረምት

ይቅርታና ክረምት

ይቅርታና ክረምት

ይቅርታና ክረምት

በወርሐ ክረምት ከሚታሰቡ እና ከሚናፈቁ ነገሮች አንዱ አዲሱን ዓመት መቀበል፣ ስለ አዲሱ ዓመት ማሰብ ፣አዲስ ተስፋ፣ አዲስ ምኞትና በአዲሱ ዓመት ስለ ሚሠሩ ሥራዎች፣ ስለምናሳካቸው ተግባራት እቅድ ማቀድ ነው።

አብዛኞቻችን ከማናስበው ነገር አንዱ አሮጌውንስ ዓመት እንዴት እንሸኘው የሚለውን ነው:: ሁሌም ይሄ ሲታሰብ ወደ አእምሮ ከሚመጡ ነገሮች ዉስጥ ጾመ ፍልሠታ አንዱ ነው። በተለይም ደግሞ ከአዲስ ዓመት በፊት መምጣቱ አሮጌውን ዓመት ለመሸኘት ጥሩ አጋጣሚ ነው። በፍልሰታ ሁሉም ኦርቶዶክሳዊ ምዕመን በመሚባል ደረጃ ከሕፃን እስከ አዋቂ የሚጾምበት የሚያስቀድስበት ወቅት ነው። ግን ምን ያህሎቻችን ነን ቅዳሴ ስንሄድ የካህኑን “በልቦናው ቂምን ያዘለ ክፋትን ያሰበ ቢኖር እዚህ አይቁም” የሚለውን ቃል ልብ የምንል የሚለው ሌላ ጥያቄ ነው።

ጾም ጸሎታችን ቅዳሴያችን ምጽዎታችን ሳይቀር ያለ ይቅርታ በረከት ማናገኝበት እንደሆነ የምናስበው። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ (ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና) በማቴ 5÷23-24 ባለው ኃይለ ቃል፤ “እንግዲህ መባህን በመሰዊያው ላይ ብታቀርብ፣ በዚያም ወንድምህ አንዳች አንተ ላይ እንዳለው ብታስብ፣ በዚያ በመሰዊያው ፊት መባህን ትተህ ሂድ፤ አስቀድመክም ከወንድምክ ጋር ታረቅ፤ በኋላም መጥተክ መባክን አቅርብ።” ያለውን አምላካዊ ቃል አስበን አሮጌው ዓመታችንን በይቅርታ ለመሸኘት የተዘጋጀን መሆን ይገባናል። በዘዉትር ጸሎት ላይ፤ “በደላችንን ይቅር በለን፣ እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል” እንላለን። ታድያ፤ ይቅርታ ምንድነው? ለምንስ ነው ይቅርታ ማደርገው? ደሞስ ለማ? የሉትን ጥያቄዎች በመመለስ አሮጌውን ዓመታችንን በይቅርታ ለመሸኘት እንዘጋጅ።

ከእግዚአብሔር ጋር መታገል

ከእግዚአብሔር ጋር መታገል

ከእግዚአብሔር ጋር መታገል

ከእግዚአብሔር ጋር መታገል

ንስሐ ገብተህ ኃጢያትን ለማስወገድ ትፈልጋለህ? አንድ ነገር አስታውስ። ኃጥያትን ለማሸነፍ የሚደረገው ትግል በሰው ጉልበት ብቻ ውጤታማ ሊሆን አይችልም። ኃጥያት ጠንካራ በመሆኗ “ወግታ የጣለቻቸው ብዙዎች ናቸው። እርሷም የገደለቻቸው ብዙዎች ናቸው” ምሳሌ(7፥26) ተብሎ ተጽፏል።

 

ይህ አዳምን፣ ሶምሶምን፣ ዳዊትና ሰለሞንን ወግቶ የጣለ ኃጢያት ያለ እግዚአሔር አጋዥነት አንተ ብቻዬን እወጣዋለው ብለህ ታስባለህ? አስቀድመህ የወደቅህበት ኃጢያት ያለ እግዚአብሔር እርዳታና ድጋፍ አንተን እንደሚቆጣጠርህ አትጠራጠር። ውጊያው ውጫዊ የሆነ ጦርነት ብቻ አይደለም። በተለይ የኃጢያት ዝንባሌ የምታሳይ ከሆነ ውጊያው እጥፍ ነው የሚሆነው። የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ እንዲህ ይላል። “እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ ጠባቂ በከንቱ ይተጋል”(መዝሙር 127፥1)። ጌታ እራሱ “ያለ እኔ አንዳች ነገር ማድረግ አይቻላችሁም”(የሐዋ 15፥5) ይላል። እግዚአብሔርን ሳትይዝ የምታደርገው ትግል ፍጻሜው ውድቀት መሆኑን አትጠራጠር። ውጊያውን ማሸነፍ ቢቻልህ እንኳን በከንቱ ውዳሴ ተጠልፈህ መውደቅ መቻልህን አትዘንጋ። ምክንያቱም በራስህ ኃይል ታግለህ እንዳሸነፍከው ይሰማኻልና። Read more

ቤተ ክርስቲያን ለምን ለውጥ ያስፈልጋል?

ቤተ ክርስቲያን ለምን ለውጥ ያስፈልጋል?

ቤተ ክርስቲያን ለምን ለውጥ ያስፈልጋል?

ቤተ ክርስቲያን ለምን ለውጥ ያስፈልጋል?

በዘመናችን ቤተ ክርስቲያን እጅግ በከፋ መንፈሳዊ ጉድለትና አስተዳደራዊ ግድፈት እየታመሰች ነው። ይህን ሐቅ በአገልግሎት ቀጥተኛ ሱታፌ ላላቸው ካህናትና ምእመናንን መንገር የዓዋጁን በጆሮ ይሆናል፡፡ ሀብተ ውልድ ያላቸው ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች ከቤተ ክርስቲያን ጋር ያላቸው ትሥሥር የላላ ነው ተብለው ለሚታሰቡት ክርስቲያኖች እንኳ ግድፈቱ ክሡት ነው፡፡ ይህ የተገለጸ እውነት ቤተ ክርስቲያን ለውጥ ያስፈልጋታል የሚለው ሐሳብ አከራካሪ እንዳይሆን ያደርገዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚነሣ አንዳች የማያከራክር መሠረታዊ እውነት አለ፤ እርሱም ምን ዓይነት ለውጥ ለሚለው ጥያቄ የሚሰጥ መልስ ይሆናል፤ አስተዳደራዊ ለውጥ፡፡

የቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ሥሪት በጥሩ መሠረት ላይ የቆመ ነው። የዘመነ ሰማዕታትን የመከራ ማዕበል መሻገር የቻለችው መሠረቷ፣ ራስ ጉልላቷ ክርስቶስ ኢየሱስ ስለሆነላት ነው። ሐዋርያት፣ ሐዋርያውያን አበው እና በየጊዜው የተነሡት ሊቃውንቱ በጽኑ መሠረት ላይ የቆሙ ዓምዶቿ ስለነበሩ በደም በተከፈለ መሥዋዕትነት መከራውን የተሻገረ ክርስትና ዛሬም ድረስ እንዲኖረን አድርገዋል። እንከን የለሽ ክርስቶሳዊው አስተምህሮዋን ለመቀሰጥ የተደረገባትን ሙከራ ሁሉ ተቋቁማ እዚህ የመድረሷ ዋነኛው ምክንያት እውነት ላይ የቆመች የእውነት ምስክር በመሆኗ ነው፡፡ ይህ እውነቷ ዘላለማዊ ነውና ለውጥም መሻሻልም አያስፈልገውም፡፡ ይህን ተልእኮዋን የምታስፈጽምበት አስተዳደራዊ ሥርዓት ግን ዘመኑን በዋጀ መንገድ ለውጥን ይሻል፡፡

ከላይ በገለጽነው እውነት መሠረት በዚህ ጽሑፍ የምንዳስሰው ለውጥ ለምን ያስፈልጋል፣ የሚለውን ነጥብ ነው፡፡ ለውጥ የሚያስፈልግበትን በርካታ ጥናታዊ ሐሳቦችን መጋቤ ምሥጢር ስማቸው ንጋቱ «የለውጥ አመራር ለቤተ ክርስቲያን» በሚለው መጽሐፋቸው ይዘረዝራሉ (ገጽ ፪፻)። ለዛሬ ሁለቱ ላይ እናተኩር።

1ኛ. ለውስጥ ግፊት (internal pressure) ምላሽ ለመስጠት፤ ለውጥ የሚያስፈልግበት አንደኛው ምክንያት ለውስጥ ግፊት ምላሽ ለመስጠት እንደሆነ መጋቤ ምሥጢር በመጽሐፋቸው ይገልጻሉ። እውነት ነው ከቤተ ክርስቲያን ውስጥ አስተዳደራዊ ለውጥን እንዲመጣ የሚጠይቅ(ግፊት የሚያደርግ) ኃይል አለ። ይህኛው ግፊት የወዳጅ ግፊት ነው። ቤተ ክርስቲያኑን እናቴ ብሎ የተጠጋ ብቻ ሳይሆን ህልውናውን ከህልውናዋ ጋር ያስተሣሠረው ምእመን የሚያነሣው የለውጥ ጥያቄ ነው።

ቤተ ክርስቲያኑ ሁሌም ህልው ሁና ማየት የሚሻ፣ ሁሌም  የመንፈሳዊ ልዕልና ማዕከል እንደ ሆነች፣ ዓለምን እየዋጀች፣ ስብራቱን እየጠገነች ዕለት ዕለት እንድታድግ የሚሻ ለውጥ ፈላጊ ኃይል ነው። ለውጡን የሚፈልገው በፍጥነት እየተለወጠ ባለው ዓለም በአስተዳደራዊ ዕሳቤ ሳይለወጡ መኖር የሚያመጣውን ወደ ዳር የመገፋት፣ የመገዝገዝ እና የመገንደስ ሥጋት ስለሚያውቅ ነው። ማንኛውም ተቋም በተለወጠ ከባቢ ያልተለወጠ የአእምሮ ውቅር ይዞ መቀጠል ይከብደዋል። ይህ ኃይል ጳጳሳቱን አባቶቼ ብሎ በእግዚአብሔር እንደራሴነት የተቀበለ፣ ለቡራኬያቸው በፊታቸው የሚንበረከክ ነው።

በዚህ ለውጥ ፈላጊ የቤተ ክርስቲያኗ አካል ውስጥ ኦርቶዶክሳዊው ምእመን፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችና አገልጋይ ካህናት ይገኛሉ፡፡ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ጥንቱ ፈቃደ ሥጋቸውን ያሸነፉ፣ ለመለኮታዊው ፈቃድ የተገዙ ጳጳሳት እጅ ማየት ይሻል፡፡ ለፍትሕ ቆሞ ድሃ ተበደለ፣ ፍርድ ተጓደለ የሚል አባት፣ ስለ ቤተ ክርስቲያን ክብርና ስለ ወንጌል አገልግሎት ራሱን ለመስጠት ቁርጠኝነቱ ያላቸው አባቶች መንፈሳዊውን አገልግሎት ሲመሩት ማየት ይፈልጋል፡፡ በመንጋው ላይ የሚሾሙ እረኞች የሥልጣን ፆር ያሸነፋቸው ሳይሆኑ፣ የእግዚአብሔር ጥሪ የደረሳቸው፣ ለመንጋው የሚጠነቀቁ፣ በጎችም በመንፈሳዊ ብቃትና ንጽሕናቸው የሚተማመኑባቸው፣ በኖላዊነታቸው በመንጋው የሚታወቁ እንዲሆኑ የሚጠይቅ ለውጥ ፈላጊ ነው፡፡ በአድልኦ አልባ መርሕ አገልጋዮቿን ማለትም ካህናትን እና ምእመናንን የምታስተናግድ ቤተ ክርስቲያን እንድትኖረው ይሻል።

በውስጥ ያለው የለውጥ ፍላጎት ግፊት ዓላማው መንፈሳዊና አስታዳደራዊ ግድፈቶች ታርመው ማየት ነው፡፡ ፈሪሐ እግዚአብሔር የሰፈነበት፣ ከጉቦኝነት፣ ከዘውገኝነት የጸዳ ለዓለም አሠራር አርአያ የሆነ አስተዳደርን ማንበር ይፈልጋል፡፡ አድልዎን የምታወግዝ ቤተ ክርስቲያን በአድሏዊ አሠራር ስትታወክ ማየት አይሻም፡፡ የሥነ ምግባርና ሞራል ትምህርት  ምንጭ የሆነች ቤተ ክርስቲያን የሥነ ምግባር መምህሮቿ በሥልጣን ሽኩቻ ሲራኮቱ ማየትና መስማትን አይወድም፡፡ አባቶች በሀገረ ስብከታቸው እና በሚያስተዳድሯቸው አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት የሌብነት፣ የግቦና የወገንተኝነት ተግባር መበራከቱ በውስጥ ላለው ለውጥ ፈላጊ ኃይል ሕመም ነው፡፡ ከዚህ ሕመም የተፈወሰች ቤተ ክርስቲያንን ለማየት አስተዳደራዊ ለውጥን መተግበር የሕክምናው አንዱ መንገድ እንደሆነ በጽኑ ያምናል፡፡

የሰፈነው አስተዳደራዊ ግድፈት መንፈሳዊነትና ሙያዊ ብቃት ያላቸውን አገልጋዮች ከዐጸደ ቤተ ክርስቲያን ገፍቶ እያስወጣ ነው፡፡ በበርካታ ምእመናንን ሕይወት ላይም አሉታዊ ተጽእኖው ከብዷል፡፡ በጎችን ከቤተ ክርስቲያን አስበርግጎ እያስወጣ እና ለነጣቂዎች ሲሳይ እያዳረገ ነው፡፡ በውስጥ የተነሣው የለውጥ ግፊት እነዚህን ሁሉ ሥጋቶች ሊቀርፍ የሚችል አስተዳደራዊ ለውጥ እንዲተገበር የሚሻ ነው፡፡ ለውጡ የምእመናንን መንፈሳዊ ሕይወት በሚያጎለምስ መልኩ መቃኘት አለበት፡፡ ክብረ ክህነት የተጠበቀበት፣ በምእመናን እና በእረኞች መካከል መተማመን የሰፈነበት ከአድልኦ የጸዳ ሥርዓትን ማስፈን አንዱና ዋነኛ ዓላማው ነው።

አስተዳደራዊ ብልሹነት ከመገንገኑ የተነሣ ካህናት ቀድሰው ወጥተው ዕጣን ዕጣን ብቻ አይደለም የሚሸቱት፣ ከምርፋቅ እስከ መኖሪያ ቤታቸው ብሶት ብሶት የሚሸቱ ድምፆችንም ያሰማሉ። ዕድሜ ልክ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ጠንቅቀው ተምረው ዕድሜ ልክ ደጅ ጠኝ የሆኑ አገልጋዮች ዕንባ በማኅሌቱ ድምፅ ተውጦ ሊጠፋ አልቻለም እኮ። አስቀድሰው ወደ ቤታቸው ከሚመመለሱ ክርስቲያኖች መካከል ለሕይወት የሚበጅ ስንቅ ከሰነቁት ይልቅ የልመና መድረክ በሚመስለው ዐውደ ምሕረት የተሰማቸውን መሰላቸት ይዘው የሚመለሱት እየበዙ ነው፡፡ በዕረፍተ ሥጋ የተለያቸውን ዘመድ አዝማድ ቀብረው ወደ ቤታቸው ከሚመለሱ መካከል በአገልግሎት አሰጣጥ በሚታይ መድልዎ በኀዘን ላይ ኀዘን የሚደርቡ ምእመናን ብዙ ናቸው።

የውስጥ ለውጥ ፈላጊ ግፊት ውጤት የሆነው ብዙኃኑ አገልጋይና ምእመናን የተዛባውን አስተዳደር ሥርዐት ታርሞ ማየት ብቻ ሳይሆን በማረም ሒደቱም ተሳታፊ የመሆን ዓቅሙም ፍላጎቱም አለው። ቤተ ክርስቲያንን ፍትሕ እና ርትዕ የሰፈነባት ደጀ ሰላም ሆና ማየትን ያልማል። ያንዣበበው አደጋ ገብቷቸው፣ ህልሙን ህልም አድርገው፣ የለውጥ መሪ ለመሆን ራሳቸውን ያዘጋጁአባቶች ቢጠሩት አቤት፣ ቢልኩት ወዴት ለማለት የተዘጋጀና በቤተ ክርስቲያን ዕቅፍ ውስጥ ያለ ኃይል ነው፡፡ ይህን በልጅነት መንፈስ የተነሣሣ በጎ የለውጥ ግፊት ተቀብሎ በአግባቡ ለማስተናጋድ ያልተከፈተ የቤተ ክህነት ደጃፍ መዶሻና ጅራፍ ከያዘ የለውጥ ኃይል ጋር መፋጠጡ አይቀሬ ነው፡፡

  1. ተፎካካሪ ለሆኑ ግፊቶች(Competitive pressure) ምላሽ ለስጠት፤ ሁለተኛው ለውጥ የሚያስፈልግበት ምክንያት ተፎካካሪ ለሆኑ ግፊቶች(Competitive pressure) ምላሽ ለመስጠት ነው።

በፉክክር መርሕ የምትመራ ዓለም ነው የምንኖረው፡፡ በዓለም ሳለን ይህን የፉክክር መድረክ የመጋፈጥ ግዴታ አለብን፡፡  መጋቤ ምሥጢር ስማቸው የፖለቲካውን እና የኢኮኖሚውን ዓለም የፉክክር አድማስ ይገልጹና የመንፈሳዊውን ዐለም ፉክክር እንዲህ ያስረዳሉ፤ ‹‹መንፈሳዊው ዓለም ደግሞ በነገረ መለኮት ዕውቀት፣ በሥርዓት፣ በቀኖና፣ በስብከት ዘዴ፣ በማኅበራዊ አገልግሎት፣ አባላትን በማብዛትና አንዱ የሌላውን በመንጠቅ ይወዳደራል፡፡ እኛ ሁል ጊዜ አስነጣቂ ሌላው ነጣቂ የሆነበት ግንኙነት እየተፈጠረ ነው፡፡›› (ገጽ ፪፻፩)

ከዚህ የሁል ጊዜ ተነጣቂነት ቦታ ለመውጣት ለውጥ ያስፈልጋል፡፡ ለውጡ በአግባቡ ከተመራ ቤተ ክርስቲያን ከተፈጥሯዊ ዕድገቷ ማለትም ከክርስቲያን ቤተሰብ በሚወለዱ ሕፃናት ያገኘቻቸውን ነፍሳት ብቻ አይሆንም ለሰማያዊ ክብር የምታበቃው፡፡ በወንጌል መረብነት በደጅ ያሉትን አጥምዳ የሰማያዊ ሕይወት ተካፋይ በማድረግ እየሰፋች እንድትሔድ ያስችላታል፡፡ ለውጡ ቸል ከተባለ ደግሞ የራሷን ልጆች ጠብቃ በዐጸዷ ለማቆየትም ከባድ ይሆንባታል፡፡

ከውጭ በኩል የለውጥ ግፊት የሚፈጥረው አካል ለውጡን የሚፈልገው ከውስጣዊው ግፊት በተቃርኖ ቆሞ እና ከራሱ ዓላማና ግብ አንፃር አስልቶ ነው፡፡ በእርሱ አስተሳሰብ የተቃኘች ለፍላጎቱ የተገዛች ቤተ ክርስቲያንን ለመፍጠር ነው። በዚህ ተፎካካሪ ውጫዊ ገፊ ኃይል የተቃኘች ቤተ ክርስቲያን ደግሞ ርትእት ኦርቶዶክሳዊት ልትሆን አትችልም፡፡ ምክንያቱም ፈቃዱን ፈጻሚ ለማድረግ ባለው ፍላጎት አስተምህሮዋን ይቆነጽላል፣ መንፈሳዊ ዕሴቶቿን ያራክሳል፡፡ በዚህ ብቻ አይቆምም፤ ለራሱ ጥቅም ሲል የቤተ ክርስቲያንን ህልውና ለማክሰም እንቅልፍ የለውም፡፡

ይህን ሁሉ ነባራዊ ሐቅ ተረድቶ እና የሁነት ትንተና ሠርቶ በረድኤተ እግዚአብሔር በመደገፍ መጭውን ጊዜ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ምቹ ማድረግ የሚችል ቤተ ክህነት ግን ያለን አይመስልም፡፡ ለውጡ መጀመር ያለበት እዚህ ላይ ነው፤ ቤተ ክህነቱ ዐይነ ልቡናውን እንዲገልጥ ከማድረግ፡፡ ነባራዊውን ሒደት እንዲያይ፣ ውስጣዊውን የለውጥ ግፊት በአዎንታ እንዲቀበል መጫን ግድ የሚልበት ጊዜ ላይ ነን፡፡ ቤተ ክርስቲያን ለውጡን የማስፈጽም ዓቅም ያላቸውን በዕውቀት የደረጁ፣ በልምድም የበለጸጉ ምእመናንን ልጆቿን አበርክቶት የምትጠቀምበትን መንገድ ማመቻቸት ለነገ የማይባል ሓላፊነት ነው፡፡ ሕዝበ ክርስቲያኑ በተደጋጋሚ እንደታየው ለሚወዳት እና ሳይሳሳ ነፍሱን ለሚሰጥላት ቤተ ክርስቲያን ህልውና ሲል ቤተ ክህነቱ አስተዳደሩን ከአፍ በተሻገረ ሁኔታ ግልጸኝነት እና ተጠያቂነት አሠራር በማስፈን እንዲያዘምን በተለያየ መንገድ ግፊት ማድረግ አለበት፡፡

በሰማይ የሀሉ ልብክሙ - ልቡናችሁ በሰማይ ይኑር ቅዳሴ እግዚእ

በሰማይ የሀሉ ልብክሙ – ልቡናችሁ በሰማይ ይኑር ቅዳሴ እግዚእ

በሰማይ የሀሉ ልብክሙ - ልቡናችሁ በሰማይ ይኑርቅዳሴ እግዚእ

በሰማይ የሀሉ ልብክሙ – ልቡናችሁ በሰማይ ይኑር
ቅዳሴ እግዚእ

በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንም ሆነ በአኃት አብያተ ክርስቲያን ጸሎተ ቅዳሴ የሚጀመረው ካህኑ ከምእመናን ጋር በሚያደርገው ተዋሥዖ (ምልልስ) ነው፡፡ ብሔራውያን ሊቃውንት ከመጽሐፈ ኪዳን የወሰዱትን አኮቴተ ቁርባን ቅዳሴ እግዚእ (የጌታ ቅዳሴ) ብለው ሰይመውታል፡፡[1] የዚህ ቅዳሴ አውስኦ የሚጀምረው በዲያቆኑ ‹‹በሰማይ የሀሉ ልብክሙ-ልባችሁ በሰማይ ይኑር›› በሚል ቃል ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከትንሣኤው በኋላ ከሐዋርያት ጋር ለዐርባ ቀናት ያህል ሲቆይ ያስተማራቸው እና ከሰባቱ ኪዳናት አንዱ ነው፡፡ ሊቃውንቱ ይህ ቃል ጌታ አስቀድሞ በጸሎተ ሐሙስ ሕብስቱን ያከበረበት በለሆሳስ የደገመው ቃል መሆኑን ይነግሩናል፡፡ ይህንኑ ቃል ከትንሣኤው በኋላ ለሐዋርያት እንዳስተማራቸውም ያስረዳሉ፡፡[2] Read more

በሕገ ወጥ ሹመት የተሳተፉ አባቶችን ዕጩ አድርጎ ማቅረብ ያለው ዳፋ

በሕገ ወጥ ሹመት የተሳተፉ አባቶችን ዕጩ አድርጎ ማቅረብ ያለው ዳፋ

በሕገ ወጥ ሹመት የተሳተፉ አባቶችን ዕጩ አድርጎ ማቅረብ ያለው ዳፋ

በሕገ ወጥ ሹመት የተሳተፉ አባቶችን ዕጩ አድርጎ ማቅረብ ያለው ዳፋ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በግንቦት ፳፻፲፭ ዓ.ም በነበረው የርክበ ካህናት መደበኛ ጉባኤው አዲስ ኤጲስ ቆጶሳትን ለመሾም አስመራጭ ኮሚቴ መሠየሙ ይታወቃል።ኮሚቴው ዕጩ ኤጲስ ቆጶሳትን እንዲያቀርብ ከመሠየም ውጪ ቅዱስ ሲኖዶስ ጉዳዩን በምሥጢር እንዲያከናውን የሰጠው ትእዛዝ የለም። የተሠየመው አስመራጭ ኮሚቴ ግን ሥራውን በድብቅ ሠርቶ ለቋሚ ሰኖዶስ ሪፖርት አድርጓል። ቋሚ ሲኖዶሱም የሥራውን መጠናቀቅ በመግለጽ ለብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ለቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት እንዲገኙ ጥሪ አስተላልፏል። የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤም ኮሚቴው በዘጠኙ አህጉረ ስብከት የሚመደቡ ዘጠኝ ተሿሚዎችን ለመለየት የመጨረሻዎቹን ፲፰ ዕጩዎች ማቅረቡን በመግለጽ ሪፖርት ሲያደርግ በምርጫ ዘጠኙን በመለየት ሹመታቸው ሐምሌ ፱ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም እንደሚፈጸም ውሳኔውን ይፋ አድርጓል። ኮሚቴው ካቀረባቸው ዕጩዎች ውስጥ ሰባቱ ጥር ፬ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም በሕገ ወጡ ሢመት ተሳታፊ የነበሩ ናቸው። ከእነዚህ ውስጥ ሦስቱ በቅዱስ ሲኖዶስ ተመርጠዋል። የእነዚህ አካላት በዕጩነት መቅረብ እጅግ ብዙ ውስብስብ ችግሮችን የሚፈጥር መሆኑ አያጠራጥርም። ለማሳያ ያህል የተወሰኑትን እንመልከት። Read more

ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይን አስመልክቶ ከሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የተሰጠ መግለጫ!

ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይን አስመልክቶ ከሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የተሰጠ መግለጫ!

ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይን አስመልክቶ ከሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የተሰጠ መግለጫ!

ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይን አስመልክቶ ከሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የተሰጠ መግለጫ!

በሰሜኑ የአገራችን ክፍል ከተፈጠረ ጦርነት ጋር ተያይዞ በቤተ ክርስቲያን የበላይ መዋቅርና በትግራይ ክልል በሚገኙ አህጉረ ስብከት መካከል የነበረው አስተዳደራዊ መዋቅር ተቋርጦ መቆየቱ ይታወቃል። የተፈጠረው አለመግባባት በውይይት ተፈቶ መዋቅራዊ አንድነቱ ተጠናክሮ እንዲቀጠል ሀገራዊ የሰላም እርቁ ከተፈጸመበት ማግስት ጀምሮ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፊርማ በተደጋጋሚ በደብዳቤ ሲጠየቅ መቆየቱም ይታወሳል፡፡

በትግራይ ክልል በሚገኙ አህጉረ ስብከት ያሉ አራቱ ሊቃነ ጳጳሳት ግን የሰላም ጥያቄውን በመግፋት መዋቅራዊ አደረጃጀቱን በመጣስ መንበረ ሰላማ የትግራይ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት መሥርተናል በማለት ተገቢነት የሌለው መግለጫ ከመስጠት አልፈው ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት ለመፈጸም ለሐምሌ 9 ቀን 2015 ዓ.ም. ቀጠሮ መያዛቸውን በተለያዩ መገናኛ ብዙኀን እየገለጹ ይገኛሉ። የተከሰተውን የቤተ ክህነት አስተዳደር ክፍተት በማስፋት ወደ ቀኖና ጥሰት ለመውሰድ የሚደረገው ሒደት በእግዚአብሔርና በታሪክ ፊት ተጠያቂነትን ያስከትላል። በሊቃነ ጳጳሳቱ በቤተ ክርስቲያን ደረሰብን በሚል የሚጠቀሱ ጉዳዮች አግባብነት የሌላቸው ከመሆናቸውም በላይ በግለሰብ ደረጃ ተነገሩ የተባሉ ንግግሮችንም በመውሰድ ቤተ ክርስቲያንን በምልዓት እንደ ጥፋተኛ መቁጠሩ ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም። ይልቁንም አሁን ያለውን ችግር የበለጠ የሚያወሳስብ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡

ተከስቶ ከነበረው ችግር ጋር ተያይዞ ፈጥኖ ለመፍትሔ አለመዘጋጀትና ሰላም እና አንድነት ለማምጣት መዘግየት እንደነበረ ባይካድም በስተመጨረሻ ቅዱስ ሲኖዶስ ችግሩ የመጨረሻ እልባት እንዲያገኝ  በይፋ ይቅርታ ከመጠየቅ ጀምሮ በቅዱስ ፓትርያርኩ የተመራ የሰላም ልዑክ በመላክ አንድነቱን ለማምጣት የተሔደበት ርቀት የሚደነቅ ነው። ይሁን እንጂ አራቱ ሊቃነ ጳጳሳት የሰላም ልዑካኑን የአንድነትና የእርቅ ጥያቄ በመግፋት፣ ቤተ መቅደስ እስከ መዝጋት የደረሰ ፈጽሞ የማይገባ አሳዛኝ ድርጊት ፈጽመዋል። እንዲሁም  ቤተ ክርስቲያንን ለማዳከም፣ ለመክፈል ብሎም ለማጥፋት በሚሠሩ አጽራረ ቤተ ክርስቲያን እና የዘውግ ፖለቲካ አቀንቃኞች ድጋፍና ጫና ኢቀኖናዊ በሆነ መንገድ አዲስ አደረጃጀት ለመፍጠርና ኤጲስ ቆጶሳትን ለመሾም ዝግጅት መደረጉን ከሚወጡት መረጃዎች ተረድተናል።

በመሆኑም ይህን ኢቀኖናዊ ሕገ ወጥ አካሄድና አጠቃላይ ቅዱስ ፓትርያርኩ ከሚመሩት የሰላም ልዑክ ጋር የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ከነበረው ሱታፌና ተጨባጭ ምልከታ አንጻር የሚከተለውን የአቋም መግለጫ አውጥቷል።

1ኛ. ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ እና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጥር ፲፬ ፳፻፲፭ ዓ.ም በተፈጸመው የቀኖና ቤተ ክርስቲያን ጥሰት ወቅት በቁርጠኝነት ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ለማስከበር በተሔደበት ርቀት ልክ አሁን ላይ የቤተ ክርስቲያንን መዋቅራዊ አደረጃጀት በመክፈል፣ ሕገ ወጥ የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ለመፈፀም የተወጠነውን እኩይ ሴራ ለማስቆም በመንፈስ ቅዱስ መሪነት እንደ ከዚህ ቀደሙ በጥብዓት፣ በታላቅ ጥበብና በአንድነት በመቆም ታሪካዊ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ እንጠይቃለን።

2ኛ. በትግራይ ክልል የምትገኙ ብፁዓን አባቶች፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ካህናት፣ ምእመናን፣ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት እና ልዩ ልዩ መንፈሳዊ ማኅበራት ይህ ፈተና የውጫዊ አካላት ጫና ያለበትና ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን ለማዳከም የታለመ ሴራ መሆኑን  በመረዳት፣ የቤተክርስቲያንን አንድነት በማስቀደም እየተፈጸመ ያለውን ኢቀኖናዊ ጥሰት በማስቆም የኦርቶዶክሳውያን አንድነት እንዳይከፈል የበኩላችሁን መንፈሳዊ ኃላፊነት  እንድትወጡ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

3ኛ. ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጀምሮ እስከ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን በአገልግሎት ላይ ያላችሁ አንዳንድ አገልጋዮች የሰላምና የአንድነቱ አካል ከመሆን ይልቅ ችግሩን በማባባስ በመጠመዳችሁ ከዚህ እኩይ ተግባር በመቆጠብ አንድነት እና ሰላም እንዲሰፍን ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ እና የመፍትሔው አካል እንድትሆኑ በአጽንዖት እናሳሰባለን።

4ኛ. በቅዱስ ፓትርያርኩ ዙሪያ ሆናችሁ የዚህ ታሪካዊ ስሕተት ደጋፊ የሆናችሁ እና የቤተ ክርስቲያንን ታሪክ ለማበላሸት  የተሰለፋችሁ  አካላት ከአፍራሽ አካሔዳችሁ እንድትቆጠቡ እየጠየቅን በስሑት አካሔዳችሁ ምክንያት የሚነሣው እሳት ወላፈኑ መጀመሪያ የሚያገኘው እናንተን መሆኑን በመረዳት ከዚህ ግብራችሁ እንድትታቀቡ በጥብቅ እናሳስባለን።

በመጨረሻም  ቤተ ክርስቲያንን  ለመጠበቅ እንዲሁም ሕግ እና ሥርዓት  ለማስከበር በሚደረገው ሒደት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት በአስፈላጊ ጉዳዮች ሁሉ  ቅዱስ ሲኖዶስን በመታዘዝ የልጅነት ድርሻውን ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን ያረጋግጣል።

ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት
ሐምሌ ፯ ፳፻፲፭

የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ልዩ ልዩ ብዙኃን መገናኛዎች

የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ልዩ ልዩ ብዙኃን መገናኛዎች

የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ልዩ ልዩ ብዙኃን መገናኛዎች

የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ልዩ ልዩ ብዙኃን መገናኛዎች

በያዝነው ዓመት ሊደረግ የታሰበው የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ የእምነቱን ተከታዮች በሁለት ከፍሎ ደጋፊና ተቃዋሚ አድርጎ እያነታረከ ነው። ጉዳዮን ማኅበራዊና ብዙኃን መገናኛዎች እየዘገቡት ያለው በሚከተለው መልኩ ነው። Read more