ልማትና ራስን ማስቻል ቋሚ ኮሚቴ

“የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፥ እኛም ባሪያዎቹ ተነሥተን እንሠራለን፤” (ነህ ፪ ፥ ፳)

ሰንበት ት/ቤቶች የሚሰጧቸው ሃይማኖታዊ አገልግሎቶች እና ልዩ ልዩ ክርስቲያናዊ ትሩፋቶች ቀጣይነት ባለው መልኩ እንዲተገበሩ እና በሁሉም የማኅበረሰብ ክፍል ዘንድ ያላቸውን ተደራሽነት ለማስፋፋት እንዲችሉ መርሐ ግብሮቻቸውን የሚያስፈጽሙበት አስተማማኝ የገቢ ምንጭ ያስፈልጋቸዋል። የመንበረ ፓትርያርክ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት የልማት እና ራስን የማስቻል ቋሚ ኮሚቴ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በመሪ ዕቅድ የምታስቀምጣቸውን ሁለንተናዊ የልማት አቅጣጫዎች በመከተል የሰ/ት/ቤት አባላትም ሆኑ በጎ አድራጊ ምዕመናን በሙያቸው በጉልበታቸው በጊዜያቸው እና በገንዘባቸው ቤተ ክርስቲያንን እና ኅብረተሰቡን በማገልገል እንዲሳተፉ በመላው ዓለም ከመንበረ ፓትርያርክ የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ እስከ አጥቢያ ሰ/ት/ቤት ድረስ በተዘረጋው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች መዋቅራዊ አደረጃጀት ውስጥ በልማት እና ራስን በማስቻል ዘርፍ ልዩ ልዩ አገልግሎቶችን በዕቅድ ያዘጋጃል፣ ተፈጻሚነታቸውንም ይከታተላል።

የሰንበት ት/ቤት አባላትም እንደየዕድሜ ደረጃቸው በሚመጥኗቸው የልማት እንቅስቃሴዎች እየተሳተፉ የተለያዩ ሙያዊ ክህሎቶችን ማዳበር የሚችሉባቸውን እና የነገዋን ቤተ ክርስቲያን የሚረከቡ፣ ሀገርን በቅንነት የሚያስተዳድሩ አርአያነት ያላቸው ክርስቲያኖች እንዲኾኑ ልምምድ የሚያገኙባቸውን ዕድሎች ያመቻቻል።

በፌስቡክ ያግኙን