የበዓል ዝግጅት ቋሚ ኮሚቴ

“እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህቺ ናት፤ ሐሴትን እናድርግ በእርሷም ደስ ይበለን” – መዝ ፻፲፯ ፥ ፳፬

 

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካሏት ትውፊቶች መካከል የአደባባይ በዓላቷ ይጠቀሳሉ። የበዓል ዝግጅት ቋሚ ኮሚቴ ሰ/ት/ቤቶች በጋራ የሚያከብሯቸውን እንደ መስቀል እና ጥምቀት የመሳሰሉ የአደባባይ በዓላት እንዲሁም ሰንበት ት/ቤቶች የልምድ ልውውጥ የሚያደርጉባቸው መደረኮች በመላው ዓለም ከመንበረ ፓትርያርክ የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ እስከ አጥቢያ ሰ/ት/ቤት ድረስ በተዘረጋው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች መዋቅራዊ አደረጃጀት ውስጥ በደማቅ ሁኔታ እና ወጥነት ባለው አሠራር እንዲዘጋጁ ለማድረግ ይጥራል። ዓመታዊ የሰ/ት/ቤቶች ቀን ዝግጅትንም በሙሉ ኀላፊነት ያስተባብራል።

በፌስቡክ ያግኙን