የእንግሊዝኛ ትርጉም ሥራዎች ላይ በጎ ፍቃደኞችን ለማሳተፍ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ቅዱስ ሲኖዶስ በወሰነው መሠረት ከሚሠራቸው ሥራዎች መካከል ቀዳሚ የሆነው ወጥ የሆነ የሰንበት ት/ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት (Curriculum) ዝግጅት እና ትግበራ አንዱ ነው፡፡ በዚህም መሠረት የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ከመንበረ ፓትርያርክ እስከ አጥቢያ ባለው መዋቅር አስተባባሪነት ከቅድመ መደበኛ የህጻናት እስከ 12ኛ ክፍል የሰንበት ት/ቤቶች መጻሕፍት በማዘጋጀት ላይ ይገኛል፡፡
አገልግሎቱን በውጭ ዓለም በሚገኙ ሁሉም የቤተ ክርስቲያን መዋቅር ተደራሽ ለማድረግ ይረዳ ዘንድ የእንግሊዘኛ ትርጉም ሥራ አስፈላጊ ነው። በመሆኑም ከዚህ በፊት በእንግሊዘኛ የተዘጋጁ ሥራዎችን በግብዓትነት ለመጠቀም፣ እንዲሁም በተርጓሚነት፣ በአርትዖ እና በማስተባባር በጎ ፍቃደኞችን ለማሳተፍ ይረዳ ዘንድ ይህ መጠይቅ ተዘጋጅቷል። በዚህም መሠረት በሚከተለው አግባብ እንደምታገለግሉበት መዋቅር መረጃውን በአንድ ሳምንት ውስጥ እንድታስገቡ እንጠይቃለን፡፡

እናንተ ጋር ከሚገኙ አገልጋዮች በትርጉምና በአርትዖት ሥራው ቢሳተፉ የምትሏቸው መምህራን ዝርዝር ይጻፉ (ስም፣ ስልክ፣ ኢሜይል)