በትሕትና የሚሸሹት በፍቅር የሚሸከሙት

በትሕትና የሚሸሹት በፍቅር የሚሸከሙት

በትሕትና የሚሸሹት በፍቅር የሚሸከሙት

የክርስትናን ቀደምት ዘመናት ታሪክ ስናገላብጥ የአበው እና እማት የኑራቸው ፍሬዎች፣ የተጋድሏቸው ምስክሮች የሆኑ ድንቅ ድንቅ ታሪኮች ተመዝግበው እናገኛለን፡፡ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ ብሎ ያዘዛቸውን አምላክ ቃል ሲተገብሩት እናያለን፡፡ ማስተዋል ለቻለ ትእዛዙን ጠብቀው፣ በፍጹም ልባቸው ፈጣሪያቸውን በማመን፣ በትሕትና፣ በመታዘዝ፣ ወንድማቸውን እንደ ራስ በመውደድ ቅድስናን ገንዘብ ሊያድርጓት ያለ መታከት የተጋደሉበት ፍኖት ትልቅ የወንጌል መዓድ ነው፡፡ ቢያነቧቸው ትምህርት የሚሆኑ፣ ቢተገብሯቸው በረከት የሚያሰጡ አስደማሚ የቅዱሳን ገድል ተከትበውባቸዋልና፡፡ ዛሬ አንዱን ቅዱስከድርሳንቀድተን እንዘክራለን፡፡ Read more

ለክፉዎች መድኃኒት የሚሆን የጵጵስና አገልግሎት

ለክፉዎች መድኃኒት የሚሆንየጵጵስና አገልግሎት

ለክፉዎች መድኃኒት የሚሆን የጵጵስና አገልግሎት

በቤተ ክርስቲያን ታሪክ በክፋቱ በሚታወቀው ዲዮቅልጥያኖስ ዘመነ መንግሥት ብፁዕ አባ ጢሞቴዎስ የሚባሉ በሀገረ ግብፅ የእንስና ወይም እንዴናው ሀገረ ስብከት ኤጲስ ቆጶስ ነበሩ። የወንጌል ገበሬ ስለነበሩ በሀገረ ስብከታቸው እየዞሩ ወንጌለ መንግሥትን ለሰው ልጅ ሁሉ ያስተምሩ የነበረው ሳይታክቱ ነበር። የኤጲስ ቆጶሱ ዞረው ወንጌልን ማስተማራቸው የጠቅላይ ግዛቱን ገዥ ዕለት ዕለት ያበሳጨው ነበር። ሀገረ ገዥውም ስለተበሳጨ አስጠርቶ “በክርስቶስ ማመንህንና ወንጌልን ዞረህ ማስተማርህን ተው” በማለት አስጠነቀቃቸው (መጽሐፈ ስንክሳር ኅዳር ፲፫ የሚነበበው)። Read more

የመንግሥት ጣልቃገብነት ከሕገ ወጡ ቡድን ድጋፍ እስከ ጳጳሳት ምርጫ

የመንግሥት ጣልቃገብነት ከሕገ ወጡ ቡድን ድጋፍ እስከ ጳጳሳት ምርጫ

የመንግሥት ጣልቃገብነት ከሕገ ወጡ ቡድን ድጋፍ እስከ ጳጳሳት ምርጫ

የሃይማኖትና የመንግሥት ግንኙነትን በተመለከተ አገራት የየራሳቸውን ሥርዓት ይከተላሉ። መንግሥት ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮም በተለያዩ ዘመናት ሃይማኖትና መንግሥት የተለያዩ የግንኙነት መርሖችን አልፈዋል። ሃይማኖት ከመንግሥት በላይ የሆነበት ጊዜ የነበረውን ያህል መንግሥትም ከሃይማኖት በላይ ተደርጎ የተወሰደበት ዘመን እንደነበር የዘርፉ ምሁራን ይገልጻሉ። ባለንበት ዘመን አብዛኛዎቹ አገራት የሚመሩት መንግሥትና ሃይማኖት የተለያዩ ናቸው በሚለው መርሕ ነው። ይህም ሆኖ ዓለማዊ መንግሥት ኖሯቸው፣ አንድን ሃይማኖት ብሔራዊ ሃይማኖት አድርገው ያወጁ አገራት አሉ። እንግሊዝ እና ግብጽ ለዚህ ተጠቃሽ ምሳሌዎች ናቸው።[1] ወደ አገራችን ኢትዮጵያ ስንመጣ እስከ ፲፱፻፷፮ ዓ.ም ድረስ ኦርቶዶክስ ክርስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ ቆይቷል። በተለይም በ፲፱፻፹፯ ዓ.ም የወጣው የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት ስለ ሃይማኖትና መንግሥት መለያየት ግልጽ ድንጋጌ አስቀምጧል። የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ፲፩ መንግሥትና ሃይማኖት የተለያዩ እንደሆኑ፣ መንግሥታዊ ሃይማኖት እንደማይኖርና መንግሥት በሃይማኖት ጉዳዮች፣ ሃይማኖትም በመንግሥት ጉዳዮች ጣልቃ እንደማይገቡ ይደነግጋል። ሆኖም ግን መንግሥት ላወጣው ሕግ ተገዥ ባለመሆን በሃይማኖታዊ ጉዳዮች ጣልቃ ሲገባ ይስተዋላል። Read more

የኤጲስ ቆጶሳት አስመራጭ ኮሚቴ ያከናወናቸው ተግባራትና ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገባቸው ጉዳዮች

የኤጲስ ቆጶሳት አስመራጭ ኮሚቴ ያከናወናቸው ተግባራትና ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገባቸው ጉዳዮች

የኤጲስ ቆጶሳት አስመራጭ ኮሚቴ ያከናወናቸው ተግባራትና ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገባቸው ጉዳዮች

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በግንቦት ፳፻፲፭ ዓ.ም በነበረው የርክበ ካህናት መደበኛ ጉባኤው ዘጠኝ አዲስ ኤጲስ ቆጶሳትን ለመሾም ሰባት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ያሉበት አስመራጭ ኮሚቴ መሠየሙ ይታወቃል። አዲስ ኤጲስ ቆጶሳት የሚመደብባቸው ዘጠኙ አህጉረ ስብከትም ምዕራብ ወለጋ፣ ምሥራቅ ወለጋ፣ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ፣ ምዕራብ አርሲ (ሻሸመኔ)፣ ድሬ ዳዋ፣ ምሥራቅ ሐረርጌ፣ ቡኖ በደሌ፣ ጌዴኦ፣ ቡርጂና አማሮ እንዲሁም ዳውሮ ኮንታ አህጉረ ስብከት ናቸው። የአስመራጭ ኮሚቴው አባላት ደግሞ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ፣ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ፣ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ፣ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ፣ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል፣ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስና ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል ሲሆኑ አስመራጭ ኮሚቴው ግንቦት ፳፫ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ሥራውን በይፋ የጀመረ መሆኑን የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሕዝብ ግንኙነት አገልግሎት አሳውቋል። Read more

ተሿሚዎችን ለምእመናን አለማሳወቅ የሚያስከትለው መዘዝ

ተሿሚዎችን ለምእመናን አለማሳወቅ የሚያስከትለው መዘዝ

ተሿሚዎችን ለምእመናን አለማሳወቅ የሚያስከትለው መዘዝ

በዘመናችን ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን ውጭ የሚፈጸሙ ጉዳዮች በርክተዋል። አባቶች የሠሩትን ቀኖና እያፈረሱ የቤተ ክርስቲያንን ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ አስጠብቃለሁ ብሎ መናገር አይቻልም። ከእግዚአብሔር ይልቅ ቄሳርን ለማስደሰት የሚደረገው ሙከራ በእግዚአብሔር የሚያስጠይቅ በታሪክም የሚያስወቅስ ነው። ቤተ ክርስቲያን ጉባኤ ከለባት ብላ በምትጠራው የኬልቄዶን ጉባኤ እነ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ንጉሥ ለማስደሰት ብለው እንደ ሌሎቹ መለካውያን ቢሆኑ ኖሮ ርትዕት የሆነችው ሃይማኖት ከዘመናችን ባልደረሰች ነበር። Read more

ፍኖተ-ጎርጎርዮስ

ሕዝበ ክርስቲያኑ የቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙን ትምህርቱን ሰምተው ግብሩን ዐይተው ሲወዱት ኖረዋል፡፡ ወላጆቹን በተለይ በእርግና ዘመን ላይ የነበረ አባቱን ጠይቆ ለመመለስ ወደ ወላጆቹ በሔደበት አጋጣሚ በሕዝቡ ግፊት ሥልጣነ ክህነት እንዲቀበል ተደረገ፡፡ እርሱ ግን ገዳማዊ ሕይወትን እጅግ ወድዶ ነበርና በብሕትውና ወደሚኖርበት ገዳም ሔዶ ተደበቀ፡፡ የቃልም የሕይወትም መምህር ነበር፤ በአንዲት በዓት ረጅም ጊዜ በጾም በጸሎት በመወሰን የሚታወቅ ገዳማዊ አባት፡፡ በትምህርትም ዓለማዊውን ትምህርት ከቂሣሪያ እስከ አቴና በመጓዝ በግሪክ ፍልስፍና የተራቀቀ፣ በመንፈሳዊው ትምህርትም ከሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ በኋላ ነባቤ መለኮት (ታኦሎጎስ) እስከ መባል የደረሰ የነገረ መለኮት ሊቅ ነበር፡፡

ሄሮድያዳ ዛሬም የዮሐንስን አንገት ለማስቀላት እየተዋጋች ነው

ሄሮድያዳ ዛሬም የዮሐንስን አንገት ለማስቀላት እየተዋጋች ነው።

ሄሮድያዳ ዛሬም የዮሐንስን አንገት ለማስቀላት እየተዋጋች ነው።

ቍስጥንጥንያ አዲሲቷ ሮም በሚል ስያሜ የምሥራቅ ሮማ ግዛት ዋና ማዕከል ነበረች፡፡ ከአራተኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ላይ ያለፈቃዱ ቢሆንም ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ፓትርያርክ ሆኖ ተሾሞላታል፡፡ የቅዱሱን ሹመት ተከትሎ የቁስጥንጥንያ መንበረ ፓትርያርክ እና ካህናቱ ከቅምጥል የአኗኗር ዘይቤ ጋር ተለያይተዋል፡፡ መንበረ መንግሥቱ ደግሞ በንጉሠ ነገሥት አርቃድዮስ (አርቃዲዎስ) እጅ ሲሆን ንግሥቲቷ አውዶክስያ ነበረች፡፡

Read more

“ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁ” ገላ. ፪፡፲፬

“ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁ” ገላ. ፪፡፲፬

“ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁ” ገላ. ፪፡፲፬

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የተጠመቅን ሁላችን ክርስቶስን እንደለበስን፣ በክርስቶስ አንድ እንደሆንን፣ ከዚህ አንድነት መውጣት ከክርቶስ አካልነት ከቤተ ክርስቲያን ኅብረት መለየት መሆኑን ደጋግሞ ነግሮናል። ለዚህም ነው ለገላትያ ክርስቲያኖች “አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፤ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፤ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና” በማለት የነገራቸው። የክርስቶስ አካልነት በዘር፣ በጎሣ፣ በቋንቋ ወይም በፆታ የሚገኝ ሳይሆን መንፈሳዊ ሰው ለመሆን በመሠራት ገንዘብ የሚደረግ ነው። ቤተ ክርስቲያንም አካለ ክርስቶስ እንደመሆኗ በቋንቋና በዘውግ የምትወሰን አይደለችም። እንዲያውም ቤተ ክርስቲያንን በእነዚህ ምድራዊ አሳቦች መወሰን በመንፈስ ቅዱስ ላይ ትልቅ ጽርፈት ነው። አምላካዊውንም ሕግ በሰብአዊ ሕግ ለመተካት መሞከር ነው። ቅዱስ ዮስጢኖስ ፖፖቪች የተባለ አባት ስለዚህ ጉዳይ ሲናገር እንዲህ ብሏል። Read more

የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት በኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ሂደት ላይ ያለውን ጥያቄ በደብዳቤ አሳወቀ

ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ

ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ

የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት በኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ሂደት ላይ ያለውን ጥያቄ ለአስመራጭ ኮሚቴው በደብዳቤ አሳውቋል። የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት፤ በቀኖና ቤተ ክርስቲያን አግባብ የኢጲስ ቆጶሳት ምልመላ፣ መስፈርት እና ሂደት ለሕዝብ ይፋ ሆኖ በግልፅ መከናወን እንደሚኖርበት በደብዳቤው አጽእኖት ሰጥቷል። በተጨማሪም፤ እስካሁን በተኼደበት መንገድ ከተቀጠለ፤ የሕግና የቀኖና ጥሰት፣ እንዲሁም ይሁንታ የማጣት ጉዳይ ሊከሰት እንደሚችል አሳስቧል። ደብዳቤውን የተረከቡት የአስመራጭ ኮሚቴው ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ፣ ደብዳቤውን ለኮሚቴው አቅርበው እንደሚመክሩበት አሳውቀዋል።
በሌላ በኩል፤ ከቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው፤ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ በግቦት 14 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የወሰነውን የአዳዲስ ኢጲስ ቆጶሳት ሢመት በተመለከተ በምልዓተ ጉባኤው የተሰየሙት የአስመራጭ ኮሜቴ አባላት ሥራቸውን ያጠናቀቁ መሆኑን በመግለጽ ኮሚቴው አዘጋጅቶ በሚያቀረበው እጩ ኢጲስ ቆጶሳት ምርጫ ዙርያ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ለማስተላለፍ ይቻል ዘንድ በሚል ለሰኔ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. ምልዓተ ጉባኤ ጠርቷል። ከዚህ ጋር በተያያዘ፤ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ለአስመራጭ ኮሚቴው በደብዳቤ ያሳወቃቸው ጥያቄዎች ከተጠራው ምልዓተ ጉባኤ መስየም እና የመጨረሻ ውሳኔ በፊት ታይተው የተዛቡ አካሄዶች ይስተካከላሉ የሚል እምነት አሳድሯል።

እርሱን የምሾመው ለመንበሩ ክብር እንዲሰጠው ነው

እርሱን የምሾመው ለመንበሩ ክብር እንዲሰጠው ነው

እርሱን የምሾመው ለመንበሩ ክብር እንዲሰጠው ነው

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “አሁንም በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። ከእኔ በኋላ ለመንጋዪቱ የማይራሩ ነጣቂዎች ተኵላዎች እንደሚመጡ እኔ አውቃለሁ። ደቀ መዛሙርትንም ወደ እነርሱ ይመልሱ ዘንድ ጠማማ ትምህርትን የሚያስተምሩ ሰዎች ከእናንተ መካከል ይነሣሉ። ስለዚህም ትጉ፤ እኔ ሁላችሁንም ሳስተምር ሦስት ዓመት ሙሉ ሌትም፣ ቀንም እንባዬ እንዳልተገታ አስቡ። አሁንም ለእግዚአብሔርና ሊያነጻችሁ በቅዱሳንም ሁሉ መካከል ርስትን ሊሰጣችሁ ለሚችለው ለጸጋው ቃል አደራ ሰጥቻችኋለሁ” (ሐዋ. ፳÷ ፳፰-፴፪)¹ በማለት ያስተማረው ትምህርት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ኤጲስ ቆጶሳትን ስትመርጥ በጣም እንድትጠነቀቅ የሚያሳስብ ቃል ነው። Read more