ቤተ ክርስቲያን ምን ዓይነት አመራር ያስፈልጋታል?

ቤተ ክርስቲያን ምን ዓይነት አመራር ያስፈልጋታል?

 

ቤተ ክርስቲያን ትውልዱን ለእግዚአብሔር መንግሥት የማዘጋጀት ሰማያዊ ተልእኮዋን በአግባቡ ለመወጣት እና የነገውን ትውልድ ሰብእና በመቅረፅ ረገድ የሰብአዊ ምሕንድስና ሥራዋን ለመፈጸም ዘመኑን የዋጀ አመራርና አሠራር ያስፈልጋታል። ይህም መሻት በብዙ ኦርቶዶክሳውያን ልብ ውስጥ አለ፡፡ ይህ ዕውን ይኾን ዘንድ ዛሬም ኾነ ነገ ቤተ ክርስቲያን ስንዱ እመቤት የሚያሰኛትን የነገረ ሃይማኖት ጥንቃቄ በአስተዳደርና በአመራርም መድገም ስትችል ነው። ቤተ ክርስቲያን በምድር ያለች የእግዚአብሔር መንግሥት ናትና መሠረታዊ መገለጫዎቿ ተጠብቀው ብቻ በምትሰጣቸው የአመራርነት ሚናዋ ተገልጠው ሊታዩ ይገባል። ይህን ዕውን ማድረግም በየዘመኑ የሚነሡ ኖላውያን እና ምእመናን የሁል ጊዜ ሓላፊነት ነው፡፡

በተለይም ቤተ ክርስቲያን ከውጭና ከውስጥ ተገዳዳሪዎች ጋር በተፋጠጠችበት እና እንደ ኢዮብ በፈተና በተከበበችበት በዚህ ዘመን የአሳዳጆቿን በትር መቋቋም የምትችለው በምትሰጠው ውጤታማ አመራር ነው። ፈተናውን ከባድ የሚያደርገው ከውጪው ተጽእኖ በላይ በውስጥ ያለው መንፈሳዊነት መዳከም እና ብልሹ የአስተዳደር ሥርዐት መስፈን ነው፡፡ ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን በጥንቱ መንፈሳዊ ልዕልናዋ ጸንታ እንድትቆም ማስቻል እና በዘመኑ የአስተዳደር ጥበብ የተዋጀ አሠራር የሰፈነባት መንፈሳዊ ተቋም ማድረግ በሁለቱ ተገዳዳሪዎቿ የተሴረባትን ሴራዎች ማምከኛ መንትያ መንገዶች ናቸው፡፡

Read more

“የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸውማል።” መዝ 33:7

👉 ይህን ኃይለ ቃል የተናገረው ልበ አምላክ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ነው። በግልጽ እንደነገረን የእግዚአብሔር የሆኑት ቅዱሳን መላእክት የሚያድኑ አዳኞች ናቸው። እነርሱን ከሚፈሯቸውና ከሚያምኗቸው ሰዎች አይለዩም። ከሚደርስባቸው መከራ እና ችግር ፈተና ሁሉ ያድኗቸዋል ይታደጓቸዋል። ቅዱሳን መላእክት የሰው ልጆችን የሚያድኑ አዳኞች መሆናቸውን ቅዱስ ያዕቆብ ዮሴፍንና ልጆቹን በባረከ ጊዜም እንዲህ ሲል መስክሯል። “ከታናሽነቴ ጀምሮ እኔን የመገበኝ እግዚአብሔር ከክፉ ነገር ሁሉ #ያዳነኝ_መልአክ እነዚህን ብላቴኖች ይባርክ።” ዘፍ 48:15

Read more

፲፪ኛው የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ የአቋም መግለጫ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ የሰ/ት/ቤቶች ማ/መምሪያ የዓለም አቀፍ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ፲፪ኛው ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ከግንቦት 26-27 ቀን 2015 ዓ.ም ተከናውኖ
በቀረቡ ሪፖርቶች፣ ጥናታዊ ሰነዶች፣ ከሁሉም አካባቢዎች ከቀረቡ የውይይት ግብዓቶች በመነሳት ባለ አስራ አንድ ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል።

1.  በ12ኛው ጠቅላላ ጉባኤ የቀረበውን ሪፖርትና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ተቀብለን አጽድቀናል ለትግበራው በጋራ እንሰራለን፡፡
2.  ከጠቅላይ ቤተክህነት ሰ/ት/ቤቶች ማደራጃና መምሪያ ሀገር አቀፍ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት እስከ አጥቢያ ሰ/ት/ቤት የቀረበውን የአደረጃጀት መዋቅር በጥልቀት ገምግመናል፡፡በጉባኤው የተሰጡ ማስተካከያዎችን በማካተት ወደ ስራ እንዲገባ ወስነናል፡፡
3.  የሥርዓተ ትምህርት መጻሕፍትን ለማሳተም የበጀት እጥረት እንዳለ ተገንዝበናል፡፡ይህንን ከቅዱስ ሲኖዶስ እስከ ሀገረ ስብከት ያሉ የቤተክርስቲያን መሪዎች በመገንዘብ ለሕትመቱ ተዘዋዋሪ በጀት/Revolving budget/ እንዲፈቀድና የተዘጋጁ መጻሕፍት ወደ ሕትመት እንዲገቡ በየደረጃው ለሚመለከታቸው አካላት ጥያቄ እንዲቀርብና ክትትል እንዲደረግ በአጽንዖት እንጠይቃለን፡፡
4.  ሀገሪቱ ላይ በሚከሰቱ የተለያዩ አለመግባባቶች ምክንያት ያለ እዳዋ እዳ የተሸከመችው ቅድስት ቤተክርስቲያናችንን በአቢያተ ክርስቲያኗ ላይ የሚደርሰው መቃጠልና መዘረፍ በምእመናን እንዲሁም በሰንበት ት/ቤት ወጣቶቻችን ላይ የሚደርስ የህይወት መጥፋት፣ የአካል መጉደልና መሳደድ እንዲቆም የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ እንጠይቃለን፡፡
5.  በተለያ ምክንያት የቤተ ክርስቲያንን መምህራንና አገልጋዮችን ማሰር እንዲቆም የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ እንጠይቃለን፡፡
6.  የቤተክርስቲያናችን አንድነት ተጠብቆ ምዕመናን ከመደናገር ወጥተው ሥርዓተ አምልኮ በነጻነት መፈጸም ይችሉ ዘንድ ይቅርታና ሰላምን ሲያስተምሩ የኖሩ የትግራይ አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳትና የአስተዳደር አካላት ለቤተክርስቲያ አንድነትና ለምዕመናን ሲሉ ወደ ውይይትና ይቅርታ እንዲመለሱና ቅዱስ ሲኖዶስ ያቀረበውን የሰላም ጥሪ እንዲቀበሉ በልጅነት መንፈስ እየጠየቅን ቅዱስ ሲኖዶስና በአንጻራዊ ሰላም ውስጥ ያለው የቤተ ክርስቲያን መዋቅር በትግራይ በተፈጠረው ጦርነት ለተፈጠረው ችግር ተገቢውን ድጋፍ ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራ እንጠይቃለን፡፡
7.  በቃለ አዋዲ የተደነገገው የሰበካ አስተዳደር ጉባኤ አደረጃጀት ከአጥቢያ ቤተክርስቲያን በቀር እየተተገበረ አለመሆኑ በቤተክርስቲያን አስተዳደራዊ ሂደት ላይ ክፍተት እንደፈጠረ በጉባኤው በጥልቀት ተነስቷል፡፡ስለሆነም ከወረዳ ቤተክህነት እስከ ጠቅላይ ቤተክህነት ድረስ በቃለ አዋዲው መሰረት የካህናት፣የምዕመናን እና የሰንበት ት/ቤት አባላት ተሳትፎ እንዲከበር በታላቅ አጽንዖት እንጠይቃለን፡፡
8.  ሥርዓተ አምልኮ ለመፈጸም፣ልጆች ወልዶ ለማሳደግና ተተኪ ትውልድ ለማፍራት ሀገር ያስፈልጋል፡፡በሀገር ውስጥም ሰላም ከሌለ ምንም ማከናወን አይቻልምና በመላው ሀገሪቱ በተቃርኖ የሚገኙ አካላት በሚያርጉት ጦርነትና የእርስ በእርስ ግጭት ምክንያት ንጹሀን ዜጎች ሕጻናት፣ሴቶችና ካህናት ላይ የሚደርስ እንግልትና ጉዳት እየከፋ መምጣቱን በመገንዘብ ልዩነታቸውን በውይይትና በድርድር ብቻ እንዲፈቱ እንጠይቃለን፡፡
9.  ከሲመተ ኤጲስ ቆጶሳት ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ ችግሮች በፍጹም ቅድስት ቤተክርስቲያናችንን የሚመጥኑ ሆነው አላገኘናቸውም፡፡በመሆኑም ሲመቱ ሕገ ቤተክርስቲያንን፣ፍትሐነገሥትንና ቃለ አዋዲን ባከበረና ባከበረ መልኩ ብቻ እንዲደረግ በልጅነት መንፈስ እንጠይቃለን፡፡
10.  በቤተክርስቲያናችን የሚስተዋሉ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት በተለያዩ የቤተ ክርስቲያን አካላት ተጠንተው የሚቀርቡ የመፍትሔ ሀሳቦችን ቅዱስ ሲኖዶስ በምክረ ሃሳብነት እንዲቀበላቸውና በማዳበር እንዲተገበሩ አቅጣጫ እንዲሰጥ ከጠቅላይ ቤተክህነት ጀምሮ ያሉ የቤተ ክርስቲያን መዋቅር አካላት የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ ያለምንም መሸራረፍ ተግባራዊ እንዲያደርግ በአጽንዖት እናሳስባለን፡፡
11.  በቤተክርስቲያናችን ውስጥ የሚስተዋሉ የአስተዳደር ችግሮች እንዲፈቱ በሚያስችሉ ሥራዎች ላይ ሁሉ በመሳተፍና እንደ ቤተክርስቲያን ተተኪ ልጅነታችን የበኩላችንን ኃላፊነት በባለቤትነት መንፈስ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት እስከ አጥቢያ ባለዉ መዋቅር ትኩረት ሰጥተን የምንሠራ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ግንቦት 27 ቀን 2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ

ዕርገተ ክርስቶስ

“እያዩት ከፍ ከፍ አለ፤ ደመናም ከዓይናቸው ሰውራ ተቀበለችው” ሐዋ. 1÷9

ዕርገት ማለት ወደላይ ከፍ ከፍ ማለት ሲሆን የመሬትን የስበት ኃይል የሚያሸንፍ ከፍታ ነው፡፡ ክርስቶስ ወደ ሰማይ ያረገው የመሬት የስበት ኃይልሳይገድበው ነው፡፡ የክርስቶስ ዕርገት ቀድሞ በትንቢት የተነገረ፤ በሚያምኑት ዘንድ በናፍቆት ሲጠበቅ የቆየ እና በራሱ በጌታችን የተሰበከ ነው፡፡

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለ፴፫ ዓመታት ከሦስት ወራት በምድር ኖሯል፡፡ በ፴ ዓመቱ ተጠመቀ ለ፫ ዓመታት አስተማረ፣ ስለ ኃጢአታችን በመስቀል ላይ ቤዛ ሆነልን፡፡ በሦስተኛውም ቀን ከሙታንተለይቶ ተነሣ፤ ለደቀ መዛሙርቱም ተገለጠላቸው፡፡ Read more

ቤተ ክርስትያን እና አመራሮቿ

ቤተ ክርስቲያን በምን ዓይነት የአመራር ሁኔታ ውስጥ ትገኛለች?

አመራር ሲባል የአንድን አካል እሴት፣ እምነት፣ በጎ አስተሳሰብና ጠባይ በተመሪዎች ውስጥ በማሳደር አርአያ በሚሆን አግባብ በጎ ተጽእኖ ማሳረፍ ማለት ነው። ወደ ቤተ ክርስቲያን በቀረበ መልኩ ሲተረጎም ደግሞ መልካም አርአያነት ባለው ሕይወትና በዕውቀት ምእመናን መመገብና ለሰማያዊ ሕይወት ማብቃት ማለት ነው። የሚያሠራና ተደራሽ መዋቅር መዘርጋት፣ አቅም ያለው የሰው ኃይል ማፍራት፣ አገልጋይና አገልግሎትን ማገናኘት፣ የተማከለ የፋይናንስ ሥርዓት መዘርጋት፣ አሳታፊነት እና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ተባብሮ መሥራት የመልካም አመራር መገለጫዎች ናቸው። Read more

የቅዱስ ፓትርያርኩ የግንቦት ፳፻፲፭ ዓ.ም ርክበ ካህናት ጉባኤ መክፈቻ ንግግር

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ፣

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና በሰሜን አሜሪካ የኒዮርክ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ፣

ብፁዕ አቡነ ሔኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ

ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፣ Read more

ቤተ ክርስቲያን የአንድ አካል ብቻ አይደለችም፤ የካህናት፣የምእመናን እና የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት ጭምር እንጂ!

ከሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የተላለፈ ወቅታዊ መልእክት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ዋና ተግባሩ የሆነውን ሐዋርያዊ ተልእኮ በትጋት እና በስፋት ከማስፈጸም ይቅል በሥጋ ሐሳብ ተቀፍድዶ ጥንታዊቷን እና አማናዊቷን ቤተ ክርስቲያን በማይመጥን ደረጃ ላይ መገኘቱን የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ተገንዝቧል። በተለይ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን፣ አደረጃጀቱን ለማዘመን እና የሥራ አፈጻጸም ስልትን ከዘመኑ ጋር ለማጣጣም እንዲያስችል በተለየዩ ጊዜያት በባለሙያዎች ተጠንተው የተዘጋጁ መፍትሔ አመላካች ሰነዶች ልዩ ልዩ ምክንያት እየተለጠፈባቸው ተገፍተው መወገዳቸውን ታዝበናል። ስለሆነም አስተዳደራዊ ክፍተቱ በከፍተኛ ደረጃ የወለደው ችግር የአደባባይ ምሥጢር ሆኖ ተገልጧል:: Read more

ከቅዱስ ሲኖዶስ ለ ፫ ቀናት የታወጀውን የነነዌ ፆም እና ምሕላ መጠናቀቅን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

በስመ አብ፤ ወወልድ፤ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!
በትንቢተ ዮናስ በሰፊው እንደተጠቀሰው የነነዌ ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት ላይ ስለአመጹ እና ግብራቸውም በእግዚአብሔር ፊት አጸያፊ በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር ዮናስን “ተነስተህ ወደዚያች ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ ክፋታቸውም ወደ ፊቴ ወጥቷልና በእርስዋ ላይ ስበክ” በማለት አዘዘው፡፡ ትንቢተ ዮናስ ምዕ ፩ ቁጥር ፪ ዮናስም ድምፁን ከፍ አድርጎ ለነነዌ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል ሲሰብክ “የነነዌ ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ፤ ለጾም አዋጅ ነገሩ፤ ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ፡፡ ወሬውም ወደ ነነዌ ንጉሥ ደረሰ፤ እርሱም ከዙፋኑ ተነስቶ መጎናጸፊያውን አወለቀ ማቅም ለበሰ፤ በአመድም ላይ ተቀመጠ፡፡ አዋጅም አስነገረ፤ በነነዌ ውስጥ የንጉሡንና የመኳንንቱን ትእዛዝ አሳወጀ፤ እንዲህም አለ ሰዎችና እንስሶች፤ ላሞችና በጎች አንዳችን አይቅመሱ፣ አይሰማሩ፣ ውኃንም አይጠጡ፤ ሰዎችና እንስሶችም በማቅ ይከደኑ፣ ወደ እግዚአብሔርም በብርቱ ጩኸት ይጩኹ፤ ሰዎችም ሁሉ ከክፉ መንገዳቸውና በእጃቸው ካለው ግፍ ይመለሱ፡፡ እኛ እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ተመልሶ ይጸጸት እንደሆነ ማን ያውቃል፡፡ እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደተመለሱ ሥራቸውንም አየ፤ እግዚአብሔርም ያደርግባቸው ዘንድ በተናገረው ክፉ ነገር ተጸጽቶ አላደረገውም” ትንቢተ ዮናስ ፫፡ ፭-፲

Read more

ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ ከቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!
በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረገው ምልዓተ ጉባኤ ጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሶዶ ደሙ ወረዳ ሀሮ በዓለወልድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተፈጸመውን ኢ-ሲኖዶሳዊ የሆነ የሃይማኖት፣ የቀኖናና የአስተዳደር ጥሰት አስመልክቶ በሰፊው ተወያይቶ ከቤተ ክርስቲያኒቱ የሃይማኖት ልዩ ልዩ ሕግጋት ውጭ ጳጳስ ሾመናል ባሉ አካላት እና ተሹመናል በሚሉት አካላት ላይ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕግጋት በሚፈቅድለት መሠረት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አውግዞ ከቤተ ክርስቲያን የተሰጣቸው ከዲቁና ጀምሮ ያለው ሙሉ ሥልጣነ ክህነት በመሻር አውግዞ የለያቸው ሲሆን፣ በዕለቱ ይኸው ውግዘት በመላው ዓለም ለሚገኙ የዕምነቱ ተከታዮች ማኅበረ ካህናትና ማኅበረ ምዕመናን ውግዘቱን እንዲያውቁት መንግሥትም በዚህ ጉዳይ የሚፈጠር ችግር እንዳይኖር ሰላም እንዲያስከብር ዓለም በዚህ ጉዳይ ላይ ግልጽ መረጃ ኖሮት ቤተ ክርስቲያን ለወሰነችውም ውሳኔ ግንዛቤ እንዲወስድ በመግለጫ ማሳወቃችን ይታወሳል፡፡

Read more

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በፍትሕ መንፈሳዊ እንዲሁም በሕገ ቤተክርስቲያን አንቀጽ 19 ንዑስ ቁጥር 3 አስቸኳይና ድንገተኛ ጉዳይ ሲያጋጥም ምልዓተ ጉባኤ እንደሚያደርግ በተደነገገው መሠረት ጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም. ባካሄደው አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያኒቷ ላይ በተፈጠረው ወቅታዊ የሃይማኖት፣ የቀኖና እና የአስተዳደራዊ ጥሰቶችን አስመልክቶ ውሳኔዎች አሳልፏል፡፡

Read more