የግንኙነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ

“ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ እነሆ መልካም ነው፤ እነሆም ያማረ ነው።” መዝ ፻፴፫:፩

የመንበረ ፓትርያርክ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የግንኙነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሰንበት ት/ቤት ሁለገብ  አገልግሎት ተቋማዊ በኾነ አሠራር ይበልጥ እንዲጠናከር እና በመላው ዓለም ወጥነት ባለው መልኩ ተደራሽ እንዲኾን ዘመኑን የዋጀ የግንኙነት መረብ በመዘርጋት በሰ/ት/ቤቶች መካከል የተቀናጀ ጠንካራ የአገልግሎት ትሥሥር እንዲሁም ክርስቲያናዊ ኅብረት እንዲፈጠር እና የሰ/ት/ቤት አባላት በሚኖሩበት ማኅበረሰብ ውስጥ አዎንታዊ ተጽዕኖ መፍጠር እንዲችሉ ለማድረግ ይተጋል። ለዚህም አገልግሎት በመላው ዓለም ከመንበረ ፓትርያርክ የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ እስከ አጥቢያ ሰ/ት/ቤት ድረስ በተዘረጋው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች መዋቅራዊ አደረጃጀት ውስጥ በየአቅጣጫው ያለውን የመረጃ ፍሰት በመቆጣጠር እና በማስተባበር በመላው ዓለም የሚገኙ ሰ/ት/ቤቶች በአንዲት ቤተ ክርስቲያን ጥላ ሥር ተሰባስበው ለአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ተልእኮ እና የሰ/ት/ቤት ራእይ መሳካት እንዲፋጠኑ እና የሰ/ት/ቤቶችን መልካም ገጽታ እንዲገነቡ ያስተባብራል፣ ያግዛል።

በፌስቡክ ያግኙን