‹‹እንደ ዳኛ ሳይሆን እንደ ጳጳስ አስተዳድር››
ቅዱስ አምብሮስ በቅድስናቸው፣ በተጋድሏቸው ከሚጠቀሱ የምዕራብ ቤተክርስቲያን አባቶች መካከል አንዱ ነው፡፡ ገና ወደ ክርስትና ከመምጣቱ አስቀድሞ በሰሜን ኢጣልያ የምትገኘው ሜሎና የተባለች ግዛት ተሹሞ ነበር፡፡ ሹመቱን የሰማ ከእርሱ የበላይ አስተዳዳሪ የነበረ ሹም ‹‹እንደ ዳኛ ሳይሆን እንደ ጳጳስ አስተዳድር›› በማለት በመልካም ሁኔታ እንዲያስተዳድር መከረው፡፡ የዚህ ሀገረ ገዥ ምክር ገና ከኢጥሙቃን ወገን የነበረውን የአምብሮስን መጻኢ ዕጣ ፈንታ የተናገረ ትንቢት እንደ ነበር ይነገራል፡፡ እርሱም በተሾመበት ቦታ በሚያስገርም ሁኔታ፣ እጅግ በበዛ ቅንነትና ፍትሐዊነት አስተዳደረ፡፡ በሚላኖ መንበር የነበረው አርዮሳዊ ጳጳስ ሲሞት ተተኪውን በመምረጥ ሂደት በሕዝቡ መካከል ከፍተኛ ረብሻ ተነሣ፡፡ አገረ ገዥው አምብሮስ ሁከቱን ለማብረድ ሕዝቡን በሚያረጋጋበት ጊዜ አንድ ሕፃን ልጅ ድንገት ‹‹አምብሮስ ጳጳስ መሆን አለበት!›› በማለት በጩኸት ተናገረ፡፡ ሕዝቡ ተገርሞ የሕፃኑን ድምፅ የእግዚአብሔር መልእክት አድርጎ ተቀበለው፡፡ Read more