የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት - በኢ/ኦ/ተ/ቤ የመንበረ ፓትርያርክ ሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ አንድነቱ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ተቋማዊ ራእይ፣ ተልእኮ
      • መዋቅራዊ አደረጃጀት
      • የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ተቋማዊ አደረጃጀት
      • የሰንበት ት/ቤቶች የሥራ አመራር ምርጫ ማስፈጸሚያ
    • ስልታዊ እቅድ 2018 – 2021 ዓ/ም
  • ሥርዓተ ትምህርት
    • መሠረታዊ መረጃዎች
    • የሰንበት ት/ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት አደረጃጀት መመሪያ
    • የሥርዓተ ትምህርቱ መመማሪያ መጻሕፍት ይዘት
      • የአንደኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
      • የኹለተኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
      • የሦስተኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
    • የሥርዓተ ትምህርቱ ዓመታዊ የጊዜ ሰሌዳ /ካሌንደር
    • የመምህራን ሥልጠና እና መልእክቶች
    • መጻሕፍቱን ለማግኘት እና ተጨማሪ መረጃ
    • ልዩ ልዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች
  • ፕሮጀክቶች
  • መዝሙረ ማኅሌት
    • የመስከረም ወር መዝሙሮች
      • የዮሐንስ መዝሙር
      • የመስቀል መዝሙሮች
      • የብዙኃን ማርያም መዝሙር (መስከረም ፳፩ )
      • የዘመነ ጽጌ መዝሙር
    • የጥቅምት ወር መዝሙሮች
      • የአብርሃ ወአጽብሐ መዝሙር (ጥቅምት 4 ቀን)
    • የኅዳር ወር መዝሙሮች
      • የቅዱስ ሚካኤል መዝሙር (ኅዳር 12 ቀን)
    • የጥር ወር መዝሙሮች
      • የዘመነ ጥምቀት መዝሙር
      • የቃና ዘገሊላ መዝሙር (ጥር 12 ቀን)
    • የመጋቢት ወር መዝሙሮች
      • የወርኃ ጾም መዝሙሮች
      • የሆሣዕና መዝሙራት
      • የሰሙነ ሕማማት መዝሙሮች
  • ዜና
    • አጫጭር ዜናዎች
    • ዝርዝር ዜናዎች
    • ወቅታዊ መረጃዎች
    • ማስታወቂያ
      • የሰንበት ትምህርት ቤቶች መጻሕፍት እንግሊዝኛ ትርጉም ሥራ ተሳትፎ ጥሪ
  • ያግኙን
  • ቋንቋ
    • ትግርኛ
    • Afaanoromo
  • Menu Menu

“የመንበረ ሰላማ” እና “የትግራይ ጠቅላይ ቤተ ክህነት” ጉዳይ

 “የመንበረ ሰላማ” እና “የትግራይ ጠቅላይ ቤተ ክህነት” ጉዳይ

“የመንበረ ሰላማ” እና “የትግራይ ጠቅላይ ቤተ ክህነት” ጉዳይ

በትግራይ ክልል የሚገኙ አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት በሰሜኑ የአገራችን ክፍል በተከሠተው  ጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የአስተዳደር ክፍተት በማስተካከል ግንኙነቱ እንዲቀጥል በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ለተጻፉ ደብዳቤዎችም ሆነ በአካል በመሔድ ያቀረቡትን የሰላም ጥያቄ በመግፋት ክልላዊ ሲኖዶስ ለማቋቋም የሚያደርጉትን ሒደት አጠናክረው ቀጥለዋል። መንበረ ሰላማ የሚባል መንበር፣ የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃነ ጳጳሳት ጉባኤ ጽ/ቤት የተሰኘ መዋቅር እንደፈጠሩ በደብዳቤዎቻቸውና በመግለጫዎቻቸው አሳውቀዋል። ከዚህም አልፈው ሐምሌ ፱ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ለአገር ውስጥ አምስት ለውጪ አምስት አህጉረ ስብከት በአጠቃላይ አሥር “ኤጲስ ቆጶሳትን” እንደመረጡ አሳውቀዋል። ጳጳሳቱ በዚህ ሳይገቱ ሐምሌ ፲፮ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም መረጥናቸው ካሏቸው ውስጥ ስድስቱን ሾመዋል። የተፈጸመው ድርጊት ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን ውጭ የሆነ፣ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት የሚፈታተን፣ ሐዋርያዊነቷን የሚያቃልል፣ ቅድስትነቷን የማይቀበል፣ ኵላዊነቷን በጎጥ የከፋፈለ ድርጊት በመሆኑ የማያዳግም መፍትሔ ሊሰጠው ይገባል። በዚህ ጽሑፍ በመጠኑ መዳሰስ የምንፈልገው የትግራይ ቤተ ክህነትን የትመጣ፣ ለጉዳዩ እንደ ገና መቀስቀስ ገፊ ምክንያቶች፣ የእንቅስቃሴው መሪዎችና ግባቸውን በተመለከተ ነው።

የትግራይ ቤተ ክህነት የት መጣ፡– የትግራይ ቤተ ክህነት አንቅስቃሴ ከወቅታዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ተደጋግሞ የሚሰማ ቢሆንም እንቅስቃሴው ግን የቆየና ከደርግ ዘመነ መንግሥት የጀመረ መሆኑ የታወቀ ነው። ከሕወሐት መሥራቾች አንዱ የሆኑት ዶክተር አረጋዊ በርሔ  “የሕወሐት ታሪክ” በሚል ርእስ ለሦስተና ድግሪ ባዘጋጁት የመመረቂያ ጽሑፋቸው ጉዳዩን  በተደጋጋሚ ገልጠውታል። ሕወሐት ከሥሪቱ ጀምሮ የቀድሞውን ዘውዳዊ ሥርዓት በመተቸትና በመንቀፍ የሚታወቅ ከመሆኑ አንጻር የኢትዮጵያ መሪዎች ቅቡልነት የሚመነጨው ደግሞ ከቤተ ክርስቲያን በመሆኑ ምክንያት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጋር የነበረው ግንኙነት የተበላሸ ነበር። ስለሆነም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የነበራትን ተሰሚነት ለማጉደፍ ብዙ ደክሟል። ግእዝ ተናጋሪ ካድሬዎችን ወደ ቤተ ክርስቲያን አስርጎ በማስገባት፣ በአባቶች መካከል መለያየት እንዲፈጠር በማድረግ ምእመናንን ከአባቶች የመነጠል፣ በሕዝብና በመንግሥት መካከል እንደ አማካኝ ተቋም ሆና እንዳትታይ የማድረግ ተግባር ሲያከናውን ኖሯል። አባቶች በምእመናን ላይ የነበራቸው ቅቡልነት እንዲቀንስ የፈጸመው ድርጊትም  ውጤቱ በተግባር እየታየ ነው።[1]

የቤተ ክርስቲያንን ተጽዕኖ ለመቀነስ ሕወሐት ከወሰዳቸው ርምጃዎች አንዱና ዋናው ቀሳውስትን የድርጅቱ ርእዮተ ዓለም አስፈጻሚ ለማድረግ በተከታታይ ሥልጠናዎችን ይሰጥ እንደ ነበር ዶ/ር አረጋዊ ገልጠዋል። የሥልጠናው ዓላማም የትግራይን ቤተ ክርስቲያን ከዋናው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ነጥሎ ከፓርቲው ስትራቴጂካዊ ግብ ማስማማት ነበር። ይህም የትግራይ ብሔርተኝነትን ኮትኩቶ ለማሳደግ ተጠቅሞበታል።  ለካህናቱ ሥልጠና ይሰጡ የነበሩ ካድሬዎችን፣ የቤተ ክርስቲያንን እንቅስቃሴ የሚከታተሉ ደኅንነቶችንና ተመሳስለው የገቡ ሰላዮችን በመጠቀም በፓርቲው መሪዎች የሚንቀሳቀሱ ጽ/ቤቶች እስከ ማቋቋም ተደርሶ ነበር። የፓርቲው መሥራች ከነበሩት ግለሰብ ጽሑፍ የምንረዳው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የመክፈልና ለማዳከም ስልት ተነድፎለትና ሥርዓት ተዘርግቶለት የሚሠራ የፓርቲው አንድ ፕሮግራም እንደ ነበር ነው። ለዚህም መነሻው በፓርቲው የሚቀነቀነው የዘውግ ፖለቲካ ነው።

ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ቤተ ክርስቲያን በውስጥ ኩፋሌ መንበር ገጥሟት የቆየ ሲሆን ቀድሞ የነበራትን ተሰሚነት፣ ክብርና ልዕልና ለማሳጣትም ብዙ ውጪያዊ ተግዳሮቶች ተፈራርቀውባታል። ከሃይማኖት ጋር ግንኙነት የሌላቸውን ጉዳዮች ሳይቀር ምክንያት በማድረግ ቤተ ክርስቲያን ላይ ጥቃት መፈጸም፣ ኦርቶዶክሳውያንን ስልታዊ በሆነ መንገድ ከሥልጣንና ከመንግሥት ኃላፊነት ማግለል፣ አስተምህሮዋን ለማጠልሸት የሚሠሩ ተሐድሶ መናፍቃንን በእጅ አዙር መደገፍ ድርጅቱ ሲፈጽማቸው የኖራቸው የጥፋት ተግባራት ናቸው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በተለይም በያዝነው ዓመት የጎሣ ቤተ ክህነትና የጎሣ ሲኖዶስ ማቋቋም በዐዲስ መልክ እንደ አትራፊ ንግድ በብዙዎች እየተተገበረ ያለ አጀንዳ ሆኗል። እነ አባ ሳዊሮስ “የኦሮሚያ ቤተ ክህነት” እና “የኦሮሚያና ብሔር ብሔረሰቦች ሲኖዶስ” በሚል ከቅዱስ ሲኖዶስና ዕውቅና እና ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን ውጪ “ኤጲስ ቆጶሳትን ሾመናል” ብለው እንደነበር  በተመሳሳይ በትግራይ ክልል የሚገኙ አራት ጳጳሳትም “መንበረ ሰላማ የትግራይ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት” እና “የጳጳሳት ጉባኤ” አቋቁመናል፤ “ኤጲስ ቆጶሳትን መርጠናል፤ ሾመናል” በማለት በሕገ ወጥ ድርጊት ብቅ ብለዋል።

ጳጳሳቱ ድርጊቱን ሲፈጽሙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለአቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን የሰጠችው ክብር አንሶ ለመጨመር አለመሆኑ መታወቅ አለበት። ለዘመናት ጸንቶ የኖረውን ጉዳይ ግለሰቦች ተነሥተው “አጥሯል እናስረዝመው፣ ረዝሟል እናሳጥረው” ማለት እንደማይችሉም የሚታወቅ ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የኖረችው በመንበረ ማርቆስ ቢሆንም ከዘመናት በኋላ ራሷን ስትችል መንበሯ በኢትዮጵያዊው አዲስ ሐዋርያ በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ሥም ተሰይሟል።

ተልእኮዋ ሰማያዊ የሆነውን ቤተ ክርስቲያን ራሳቸው ከፈጠሩት ከዘመን አመጣሽ የዘውግ ፖለቲካ ጋር በማገናኘት ከመንበረ ተክለ ሃይማኖት ወደ መንበረ ሰላማ ለመመለስ አስመስለው የሚያቀርቡት ማታለያ መሆኑን መረዳት ይገባል። የተወሰደ መንበር ያለ አስመስሎ በተንኮል የዋሀንን በማሳሳት ደጋፊ አድርጎ ቤተ ክርስቲያንን ለመክፈል መሞከር የሚጎዳው ራሳቸውን መሆኑን መረዳት ይገባል። “ማርቆስ አባቴ፣ እስክንድርያ እናቴ” ስትል ለኖረችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአቡነ ሰላማም ሆነ የአቡነ ተክለ ሃይማኖት የሚባል መንበር ኖሯት አያውቅም። የአቡነ ተክለ ሃይማኖት መንበር የዕጨጌነት እንጂ የፕትርክና አለመሆኑንም መገንዘብ ያስፈልጋል።

ስለሆነም በምንም መንገድ ከሐዋርያዊው ቅብብሎሽ ያፈነገጠ ተግባር እየፈጸሙ ሥሙን ማሽሞንሞን የቅዱስ ጴጥሮስን ትምህርት ትታ በመንበሩ ስትመካ የኖረችውን ካቶሊክን በተግባር መምሰል መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል።  የቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊነት የሚገለጸው በዋናነት ከሐዋርያት ጀምሮ ሳይቋረጥ በመጣ የክህነት ክትትል ነው። የክህነት ክትትል ከሐዋርያት የሚጀመር ነው። መናብርት ሁሉ መሠረታቸው ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከዋለበት ውለው፣ ካደረበት አድረው በእግርና በሕይወት የተከተሉት ቅዱሳን ሐዋርያትና አርድዕት ናቸው። ከእነርሱ መሠረትነት ውጪ ሌላ ለመመሥረት እየሞከሩ የተወሰደ ለመመለስ የተነሱ አስመስለው ማቅረባቸው አታላይነት መሆኑን አንባብያን ሁሉ ሊገነዘቡት ይገባል። ስለሆነም በትግራይ ክልል የሚገኙ አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት የሚቀነቀነው የትግራይ ቤተ ክህነት እና የመንበረ ሰላማ ጉዳይ፣ እንዲሁም ፈጸምን የሚሉት “የኤጲስ ቆጶሳት ሢመት” ከሕገ ቤተ ክርስቲያን ያፈነገጠና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን የጣሰ በመሆኑ ሳያውቁ ድጋፍ የሚያደርጉ አካላት ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ይገባል። ጳጳሳቱ ከፈጸሙት ስሕተት በንስሓ በመመለስ የራሳቸውንም ግራ ሲያጋቡት የከረሙትን ምእመን ሕይወትም ማስተካከል ይኖርባቸዋል። በንስሓ ካልተመለሱ ግን ከቤተ ክርስቲያን አንድነት የሚለዩ፣ በታሪክም ሲወቀሱ የሚኖሩ መሆናቸውን መረዳት ይኖርባቸዋል።

 

ዋቢ መጽሐፍት

  1. አረጋዊ በርሔ (ዶ/ር)፣ የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ፖለቲካዊ ታሪክ። ፳፻፲፫ ዓ.ም፣ ገጽ ፫፻፹፪-፫፻፹፭

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on LinkedIn
  • Share on Telegram
  • Share by Mail
https://eotc-gssu.org/a/wp-content/uploads/tgray-2.jpg 1080 1920 Abenezer Mamushet https://eotc-gssu.org/a/wp-content/uploads/logo-2-1-300x74-1.png Abenezer Mamushet2023-08-01 20:08:432023-08-01 20:08:43“የመንበረ ሰላማ” እና “የትግራይ ጠቅላይ ቤተ ክህነት” ጉዳይ
Search Search

Recent Posts

  • የሦስተኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
  • የኹለተኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
  • የአንደኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
  • የመስቀል ደመራ በዓል በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ
  • ሦስተኛ ዙር የ፲፪ ክፍል ምርቃት መርሐ ግብር ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ በተገኙበት ተከናወነ።

Archives

  • April 2026
  • September 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • May 2025
  • April 2025
  • October 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • November 2022
  • October 2022
  • September 2022
  • July 2022
  • June 2022
  • April 2022
  • February 2022
  • January 2022
  • October 2021
  • September 2021
© Ethiopian Orthodox Church Global Sunday School Union | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
  • Link to Youtube
  • Link to Telegram
  • Link to TikTok
Link to: ራስን በራስ መሾም በቤተ ክርስቲያን ላይ ያስከተለው መዘዝ Link to: ራስን በራስ መሾም በቤተ ክርስቲያን ላይ ያስከተለው መዘዝ ራስን በራስ መሾም በቤተ ክርስቲያን ላይ ያስከተለው... Link to: የአምቡላንሱ ችግር የሰርክ ችግር እንዳይሆን Link to: የአምቡላንሱ ችግር የሰርክ ችግር እንዳይሆን የአምቡላንሱ ችግር የሰርክ ችግር እንዳይሆን
Scroll to top Scroll to top Scroll to top