የዕቅድ ዝግጅትና ትንተና ቋሚ ኮሚቴ

“ጌታ ቢፈቅድ ብንኖርም ይህን ወይም ያን እናደርጋለን ማለት ይገባችኋል።” ያዕ ፬ ÷ ፲፭

 

የመንበረ ፓትርያርክ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት በመላው ዓለም ባሉት አደረጃጀቶች ዘንድ ዘላቂነት እና ወጥነት ባለው ዘመኑን የዋጀ ተቋማዊ አሠራር አገልግሎቱን ለማሳለጥ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በረጅም እና በአጭር ጊዜያት የሚተገበሩ የአገልግሎት አቅጣጫዎችን፣ አጠቃላይ የመሪ ዕቅድ ስልቶችን እና መርሐ ግብሮችን ይቀርጻል። ሰ/ት/ቤቶች ለሕፃናት፣ ለአዳጊዎች እና ለወጣቶች የሚሰጧቸው ሁለገብ አገልግሎቶች በዓለማችን ላይ በየጊዜው የሚከሰተቱን መልካም ዕድሎች እና ፈተናዎች እንዲሁም በየአህጉረ ስብከቱ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ከክርስቲያናዊ ዕሴቶች ጋር ባገናዘበ መልኩ እንዲተገበሩ በመንፈሳዊ ጥበብ የተቃኙ ቀልጣፋ የአፈጻጸም ስልቶችን ለመከተል ይጥራል።

ከዕቅድ ዝግጅት እስከ አፈጻጸም ባለው ሂደት ውስጥም በመላው ዓለም ከመንበረ ፓትርያርክ የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ እስከ አጥቢያ ሰ/ት/ቤት ድረስ በተዘረጋው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች መዋቅራዊ አደረጃጀት ውስጥ በአንዲት ቤተ ክርስቲያን ጥላ ሥር ተሰባስበው ለአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ተልእኮ እና የሰ/ት/ቤት ራእይ መሳካት ሁለገብ እና ጉልህ ሚና እንዲኖራቸው ተሳትፏቸውን ያስተባብራል፤ አፈጻጸማቸውንም ይከታተላል።

በፌስቡክ ያግኙን