የመረጃና ልዩ ልዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ

“የጥበብን ሥራዋን በልቡ የሚያስብ ምሥጢሯንም የተማረ ሰው የተደነቀ ነው። ጥበብን ተከተላት ምሥጢሯንም መርምር ሥራቷንም ጠብቅ” (መጽ ሲራ ፲፬ ፥ ፳፩ – ፳፪)

የመንበረ ፓትርያርክ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ የመረጃ እና ልዩ ልዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሰ/ት/ቤቶች አገልግሎት ዙሪያ የሚጠናቀሩ የዕለት ተዕለት እና ስልታዊ መረጃዎችን እንዲሁም ታሪካዊ ሂደቶችን ለመክተብ ዘመኑን በዋጁ የሥነ መላ ውጤቶች አማካኝነት የጽሑፍ፣ የድምጽ እና የምስል መዛግብቶችን እና ወጥነት ያላቸው የመረጃ ቋቶችን ያደራጃል። ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን በጠበቁ የድረ ገጽ እና የማኅበራዊ ትሥሥር ገጾች እንዲሁም የመገናኛ ዘዴዎች አማካኝነት በየዘርፉ እና በየእርከኑ ያለውን የሰ/ት/ቤቶች እንቅስቃሴ ለሕዝበ ክርስቲያኑ ያስተዋውቃል። የሰ/ት/ቤቶች አገልግሎትም በየጊዜው ዘመኑን በዋጀ መልኩ በመረጃ በተደገፉ ጥናቶች እና ዕቅዶች መሠረት እየተሻሻለ እንዲሄድ እና ለትውልድ እንዲተላለፍ አስፈላጊውን የሥነ መላ ግብዓቶች ያደራጃል።

በመላው ዓለም ከመንበረ ፓትርያርክ የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ እስከ አጥቢያ ሰ/ት/ቤት ድረስ በተዘረጋው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች መዋቅራዊ አደረጃጀት ውስጥ የሰ/ት/ቤቶች መረጃ በተከታታይነት እና በተቀላጠፈ ሁኔታ እንዲመዘገብ፣ እንዲሰራጭ እና ለዕቅዶች ግብዓትነት እንዲውል አስፈላጊ የሆኑ የሥነ መላ መተግበሪያዎችን ለማደራጀት ይተጋል።

በፌስቡክ ያግኙን