ርእይ

በ2030 የሰንበት ት/ቤቶች ተቋማዊ አቅም ጎልብቶና ተደራሽታቸው ሰፍቶ ፣ አባላት በወጥ ሥርዓተ ትምህርት ሁለንተናዊ አቅማቸው ተገንብቶ በቤተ ክርስቲያንና በሀገራዊ ጉዳዮች ጉልህና የተናበበ ሚና የሚጫወቱ ሆነው ማየት

ተልእኮ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተተኪ ትውልድ የሆኑ የሰንበት ት/ቤት አባላትን በተደራጀ መዋቅራዊ አንድነት፣ ወጥ በሆነ የትምህርት ሥርዓትና ግብዓት በማስተማር፣ የአገልጋዮችን አቅም በማሳደግ፣ ዘመኑን በዋጀ አሠራር፣ በተቀደሰ ሕይወት ቤተ ክርስቲያንን እና ሀገርን በሁለንተናዊ መልኩ የሚያገለግሉና የሚጠብቁ አገልጋዮችን ማፍራትና ማሰማራት

ዕሴቶች

እግዚአብሔርን መፍራት

ሰውን ማክበር

በፍቅር የሆነ አገልግሎት

ክርስቲያናዊ ኃላፊነትና ተጠያቂነት

ሁሉን በጥበብና ለመንፈሳዊ ዋጋ ማድረግ

ዓለም ዐቀፋዊ አገልግሎትን ማስፋት

ፅናትና ምስክርነት

ዘመኑን መቅደም፣ መዋጀት

ወቅታዊ ጉዳዮች

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ፲፬ኛው ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ የቃለ ጉባኤ ማጠቃለያ እና የጋራ የውሳኔ ሐሳብ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ፲፬ኛው ጠቅላላ ጉባኤ በጉባኤው ከቀረቡ ዓመታዊ ሪፖርቶች፣ ተዘጋጅተው ከቀረቡ ጥናታዊ ሰነዶች፣ ከየአህጉረ ስብከት ከቀረቡ አስተያየቶች እና ከጉባኤው ተሳታፊዎች ከተነሡ የውይይት ሐሳቦች ግብዓት በመነሣት ባለ 12 ነጥብ የቃለ ጉባኤ ማጠቃለያ እና የጋራ የውሳኔ ሐሳብ በማውጣት ተጠናቋል፡፡
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ

ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ በ14ኛው ዓለም አቀፍ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ያስተላለፉት መልእክት

ሰንበት ት/ቤቶች እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የቤተ ክርስቲያን አባቶች፣ ሊቃውንት፣ አገልጋዮች፣ መምህራን እና ጽኑ አማኞች መገኛ እንደመሆኑ መጠን በየአጥቢያው ሰበካ ጉባኤው የአብነት መምህራን በመቅጠር ሰንበት ትምህርት ቤቱን በማጠናከር ትውልዱን በኦርቶዶክሳዊ የሃይማኖት ትምህርት በማነጽ፣ ዶግማን፣ ቀኖናን እና ትውፊትን በማስተማር በየሀገረ ስብከቱ በሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ሰንበት ት/ቤቶች እንዲቋቋሙ፣ የተቋቋሙትም እንዲጠናከሩ ማድረግ ያስፈልጋል።
በ14ኛው ዓለም አቀፍ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ እና የሰንበት ት/ቤቶች ቀን የተላለፈ የብፁዕ አቡነ ቀለሜንጦስ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ እና የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መልእክት

ብፁዕ አቡነ ቀለሜንጦስ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ እና የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በ14ኛው የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ያስተላለፉት መልእክት

"አቀድም አእኵቶቶ ለእግዚአብሔር በእንተ ኵልክሙ እስመ ተሰምዐት ሃይማኖትክሙ ውስተ ኵሉ ዓለም"። መሰብሰባችን፣ ጽንዐ ሃይማኖታችን በዓለም ሁሉ ተሰምቶዋልና  በዚህ ጉባኤ ላይ እንድንገኝ እንድናመሰግነውም የፈቀደልንን ልዑል እግዚአብሔርን ከሁሉ በማስቀደም እናመሰግናለን።
ወቅታዊ መልእክት

ወቅታዊ መልእክት

የቅዱስ ሲኖዶስ ርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤ የሚወያይበትን አጀንዳ ተመልክተነዋል። የተያዘውም አጀንዳ ጠቃሚ እንደሆነ ተረድተናል። ነገር ግን አሁን የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ላይ የሚስተዋሉ ቁልፍ መፍትሔ የሚሹ ጉዳዮች ለውይይት ቀርበዋል ብለን አናምንም። ምክንያቱም ከአጥቢያ እስከ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ድረስ የሚስተዋሉ፤ በቅዱስ ሲኖዶስ በቁርጠኝነት ዘላቂ መፍትሔ ሊበጅላቸው የሚገቡ ዘርፈ ብዙ አስተዳደራዊ እና ተያያዥ ጉዳዮች ለውይይት ሳይቀርቡ ታልፈዋል።

የአንድነቱ መልእክት

ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት

ዘመንን በአግባቡ መሻገር የሚቻለው የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ወቅቱን ጠብቆ እንደየዘመኑ አኗኗር አቀራረቡን እና ተደራሸነቱን በማስፋት ሲሆን ጉዞው ዕድልና ችግርን ጎን ለጎን የሚያስተናገዱበት በመሆኑ በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት ቅዱስ ጳውሎስ ለክርስቲያኖች ባስተማረው ትምህርት “ የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሯችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፣የኑሯቸውን ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታችሁ ምሰሏቸው፡፡ ዕብ 13፡7 ያለውን መሠረት በመጠበቅ እና አሁን ያለውን የአገልግሎት ከባቢ በመረዳት ለሰ/ት/ቤቶች አገልግሎት ውጤታማነት አሁን የምናየውን ፈተና ለማለፍ በስትራቴጂ ማገልገል እና ልዩ ልዩ ችግሮችን እንደ አመጣጣቸው ለማለፍ በትጋት የመሠራት ስልትን መዘርጋት ላይ ይተጋል፡፡ “ ቀኖች ክፉዎች ናቸው እና ዘመኑን ዋጁ” ኤፌ5፡16

በፌስቡክ ያግኙን

መልእክታት

የቅዱስ ፓትርያርኩ መልእክት

የሰ/ት/ቤቶች አንድነት መጠንከር አለበት ። የሰ/ት/ቤቶች መዋቅር ዓለም አቀፋዊ አገልግሎት እና ቤተ ክርስቲያን ኃላፊነት የሰጠችው መዋቅር ነው፡፡ ለዚህም በሀሉም መዋቅር በአንድነት ሥትሠሩ ለቤተ ክርስቲያን ፀጋ ለእኛም ደስታችን ናችሁ፡፡

በ2013 ዓ.ም ዓመታዊ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ መልእክት የተወሰደ

የመምሪያው ሊቀ ጳጳስ መልእክት

የቤተ ክርስቲያናችን ተተኪ ትውልድ የሚፈራበት ተቋም ነው። ከትውልድ ወደ ትውልድ የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ በመጠበቅ እና በማስጠበቅ ለማስቀጠል በዚህ ዘመን ሰ/ት/ቤቶች አንድነት በጣም አስፈላጊ እና ተመሳሳይ አገልግሎት በሁሉም ቦታ ሥርዓቱን ጠብቆ ለማድረስ የሚረዳ በቅዱስ ሲኖዶስ ሕግ ተሰጥቶት በሁሉም የቤተ ክህነት መዋቅር የሚሠራበት ግዙፍ መዋቅር ነው፡፡ ለዚህም ሁሉም የቤተ ክርስቲያን አካል በሙሉ ቅድሚያ ሰጥቶ ድጋፍ እና እንክብካቤ ሊያደርግ ይገባል፡፡

በ2013 ዓ.ም ዓመታዊ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ መልእክት የተወሰደ

አስተያየትዎን ይጻፉልን