ርእይ

በ2030 የሰንበት ት/ቤቶች ተቋማዊ አቅም ጎልብቶና ተደራሽታቸው ሰፍቶ ፣ አባላት በወጥ ሥርዓተ ትምህርት ሁለንተናዊ አቅማቸው ተገንብቶ በቤተ ክርስቲያንና በሀገራዊ ጉዳዮች ጉልህና የተናበበ ሚና የሚጫወቱ ሆነው ማየት

ተልእኮ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተተኪ ትውልድ የሆኑ የሰንበት ት/ቤት አባላትን በተደራጀ መዋቅራዊ አንድነት፣ ወጥ በሆነ የትምህርት ሥርዓትና ግብዓት በማስተማር፣ የአገልጋዮችን አቅም በማሳደግ፣ ዘመኑን በዋጀ አሠራር፣ በተቀደሰ ሕይወት ቤተ ክርስቲያንን እና ሀገርን በሁለንተናዊ መልኩ የሚያገለግሉና የሚጠብቁ አገልጋዮችን ማፍራትና ማሰማራት

ዕሴቶች

እግዚአብሔርን መፍራት

ሰውን ማክበር

በፍቅር የሆነ አገልግሎት

ክርስቲያናዊ ኃላፊነትና ተጠያቂነት

ሁሉን በጥበብና ለመንፈሳዊ ዋጋ ማድረግ

ዓለም ዐቀፋዊ አገልግሎትን ማስፋት

ፅናትና ምስክርነት

ዘመኑን መቅደም፣ መዋጀት

ወቅታዊ ጉዳዮች

ከቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ከጥቅምት 11 ቀን 2014ዓ.ም. እስከ ጥቅምት 18 ቀን 2014ዓ.ም. ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባውን ሲያካሂድ ሰንብቶ ለቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን የሚበጁ ባለ ዘጠኝ ነጥብ ማኅበራዊና መንፈሳዊ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቋል፡፡

የሰ/ት/ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት በሁሉም አጥቢያዎች እንዲተገበር መመሪያ ተላለፈ

በዓለም አቀፍ ሰ/ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ በተወሰነው ውሳኔ መሠረት ሁሉም አኅጉረ ስብከት ተዘጋጅቶ የቀረበውን የአንደኛ ክፍል መጻሕፍት ተግባራዊ እንዲያደርጉ ለሁሉም አኅጉረ ስብከቶች ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ደብዳቤ ወጣ።

በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መሠረት የተዘጋጁት የ1ኛ ክፍል መጻሕፍት ተሰራጩ

ሥርዓተ ትምህርቱ በዋናነት በዓለም አቀፍ ደረጃ በሁሉም የኢትዮጰያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አጥቢያ ያሉ ሰንበት ትምህርት ቤቶችን በትምህርት አሰጣጥ ረገድ አንድ የሚያደርገው የሰንበት ትምህርት ቤቶች መማርያ እና ማስተማሪያ ሥርዓተ ትምህርት መጽሐፍ ለአንደኛ ክፍል ተጠናቅቆ ተሰራጨ

የ2014 ዓ.ም መስቀል በዓል የሰ/ት/ቤቶች ዝግጅት ላይ መሆናቸው ተገለጸ

በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በደማቁ ከሚከበሩ የአደባባይ በዓላት መካከል አንዱ የሆነው የመስቀል ደመራ በዓል ዝግጅት ትርኢትና ወረብ ለማቅረብ ከአዲስ አበባ ከሁሉም ሰንበት ትምህርት ቤቶች የተወጣጡ ቁጥራቸው ከ5500 ባላይ የሆነ ወጣቶች ለተከታታይ 25 ቀናት ዝግጅት አደረጉ . . .

የአንድነቱ መልእክት

ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት

ዘመንን በአግባቡ መሻገር የሚቻለው የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ወቅቱን ጠብቆ እንደየዘመኑ አኗኗር አቀራረቡን እና ተደራሸነቱን በማስፋት ሲሆን ጉዞው ዕድልና ችግርን ጎን ለጎን የሚያስተናገዱበት በመሆኑ በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት ቅዱስ ጳውሎስ ለክርስቲያኖች ባስተማረው ትምህርት “ የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሯችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፣የኑሯቸውን ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታችሁ ምሰሏቸው፡፡ ዕብ 13፡7 ያለውን መሠረት በመጠበቅ እና አሁን ያለውን የአገልግሎት ከባቢ በመረዳት ለሰ/ት/ቤቶች አገልግሎት ውጤታማነት አሁን የምናየውን ፈተና ለማለፍ በስትራቴጂ ማገልገል እና ልዩ ልዩ ችግሮችን እንደ አመጣጣቸው ለማለፍ በትጋት የመሠራት ስልትን መዘርጋት ላይ ይተጋል፡፡ “ ቀኖች ክፉዎች ናቸው እና ዘመኑን ዋጁ” ኤፌ5፡16

በፌስቡክ ያግኙን

መልእክታት

የቅዱስ ፓትርያርኩ መልእክት

የሰ/ት/ቤቶች አንድነት መጠንከር አለበት ። የሰ/ት/ቤቶች መዋቅር ዓለም አቀፋዊ አገልግሎት እና ቤተ ክርስቲያን ኃላፊነት የሰጠችው መዋቅር ነው፡፡ ለዚህም በሀሉም መዋቅር በአንድነት ሥትሠሩ ለቤተ ክርስቲያን ፀጋ ለእኛም ደስታችን ናችሁ፡፡

በ2013 ዓ.ም ዓመታዊ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ መልእክት የተወሰደ

የመምሪያው ሊቀ ጳጳስ መልእክት

የቤተ ክርስቲያናችን ተተኪ ትውልድ የሚፈራበት ተቋም ነው። ከትውልድ ወደ ትውልድ የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ በመጠበቅ እና በማስጠበቅ ለማስቀጠል በዚህ ዘመን ሰ/ት/ቤቶች አንድነት በጣም አስፈላጊ እና ተመሳሳይ አገልግሎት በሁሉም ቦታ ሥርዓቱን ጠብቆ ለማድረስ የሚረዳ በቅዱስ ሲኖዶስ ሕግ ተሰጥቶት በሁሉም የቤተ ክህነት መዋቅር የሚሠራበት ግዙፍ መዋቅር ነው፡፡ ለዚህም ሁሉም የቤተ ክርስቲያን አካል በሙሉ ቅድሚያ ሰጥቶ ድጋፍ እና እንክብካቤ ሊያደርግ ይገባል፡፡

በ2013 ዓ.ም ዓመታዊ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ መልእክት የተወሰደ

አስተያየትዎን ይጻፉልን