ርእይ

በ2030 የሰንበት ት/ቤቶች ተቋማዊ አቅም ጎልብቶና ተደራሽታቸው ሰፍቶ ፣ አባላት በወጥ ሥርዓተ ትምህርት ሁለንተናዊ አቅማቸው ተገንብቶ በቤተ ክርስቲያንና በሀገራዊ ጉዳዮች ጉልህና የተናበበ ሚና የሚጫወቱ ሆነው ማየት

ተልእኮ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተተኪ ትውልድ የሆኑ የሰንበት ት/ቤት አባላትን በተደራጀ መዋቅራዊ አንድነት፣ ወጥ በሆነ የትምህርት ሥርዓትና ግብዓት በማስተማር፣ የአገልጋዮችን አቅም በማሳደግ፣ ዘመኑን በዋጀ አሠራር፣ በተቀደሰ ሕይወት ቤተ ክርስቲያንን እና ሀገርን በሁለንተናዊ መልኩ የሚያገለግሉና የሚጠብቁ አገልጋዮችን ማፍራትና ማሰማራት

ዕሴቶች

እግዚአብሔርን መፍራት

ሰውን ማክበር

በፍቅር የሆነ አገልግሎት

ክርስቲያናዊ ኃላፊነትና ተጠያቂነት

ሁሉን በጥበብና ለመንፈሳዊ ዋጋ ማድረግ

ዓለም ዐቀፋዊ አገልግሎትን ማስፋት

ፅናትና ምስክርነት

ዘመኑን መቅደም፣ መዋጀት

ወቅታዊ ጉዳዮች

50 ሺህ መጻሕፍት ለ50 ሰንበት ት/ቤቶች

የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት የሰንበት ትምህርት ቤት ማደራጃ ክፍል በጦርነት ወቅት ጉዳት ለደረሰባቸው ሰንበት ትምህርት ቤቶች 50 ሺህ መጻሕፍት ለማበርከት ድጋፍ ማሰባሰብ ጀመረ አስታወቀ።

እንኳን ለጾመ ነነዌ በሰላም አደረሳችሁ!

ሰብዓ ነነዌ (የነነዌ ሰዎች) ስለ ኃጢአታቸውና ስለ በደላቸው ምሕረትን ጠይቀው፣ ንስሐ ገብተው፣ ሦስት ቀን ጾመው እና ጸልየው እግዚአብሔር ይቅርታውን እና ምሕረቱን እንደገለጠላቸው እኛም ጾሙን ጾመን ንስሐ ገብተን አምላካችን ይቅር ይለን ዘንድ ተግተን እንለምነው።

የቋሚ ኮሚቴዎች እና ንዑሳን ኮሚቴዎች የውስጥ አሠራር መመሪያዎች ትግበራ ሂደት ላይ ገለጻ ተሰጠ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ መንበረ ፓትርያርክ የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት በመላው ዓለም ለሚገኙ ሰ/ት/ቤቶች የሚሰጠውን አገልግሎት ዘመኑን በዋጀ ተደራሽነት ወጥነት እና ዘላቂነት ባለው አሠራር ለመምራት እንዲያስችለው የሚያግዝ የቋሚ ኮሚቴዎች፣ የዋና ክፍሎች እና የንዑሳን ኮሚቴዎች የውስጥ አሰራር መመሪያ ረቂቅ ሰነድ መዘጋጀቱን ተከትሎ ትላንት እሁድ የሰነዶቹን የትግበራ ሂደት የሚዳስስ የግንዛቤ ማስጨበጫ ገለጻ ለሥራ አመራር አባላት መሰጠቱን የአንድነቱ ም/ሰብሳቢ ዲ/ን ስንታየሁ ምስጋናው ገለጹ።

መንፈሳዊ በዓል ለማክበር በወጡ ኦርቶዶክሳውያን ላይ የሚደርስ ጥቃትን አጥብቀን እንቃወማለን

ጥር 12 ቀን 2014 ዓ.ም የወይብላ ማርያም ታቦትን አክብረው በሚጓዙ ካህናት ፣ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች እና አዛውንት፣ ጎልማሳና ወጣት ምዕመናን ላይ ለጸጥታ ማስከበር ስራ በተሰማራ የጸጥታ አካል ኃይል የተሞላበት ጥቃት ምክንያት የደረሰው ችግር በቤተክርስቲያናችን ላይ የሚደርሰውን በደል የሚያሳይ ኢ፟-ሰብአዊ እና ኢ-ፍትሃዊ ድርጊት በመሆኑ የሰንበት ት/ ቤቶች አንድነት በጽኑ ይቃወማል።

የአንድነቱ መልእክት

ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት

ዘመንን በአግባቡ መሻገር የሚቻለው የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ወቅቱን ጠብቆ እንደየዘመኑ አኗኗር አቀራረቡን እና ተደራሸነቱን በማስፋት ሲሆን ጉዞው ዕድልና ችግርን ጎን ለጎን የሚያስተናገዱበት በመሆኑ በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት ቅዱስ ጳውሎስ ለክርስቲያኖች ባስተማረው ትምህርት “ የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሯችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፣የኑሯቸውን ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታችሁ ምሰሏቸው፡፡ ዕብ 13፡7 ያለውን መሠረት በመጠበቅ እና አሁን ያለውን የአገልግሎት ከባቢ በመረዳት ለሰ/ት/ቤቶች አገልግሎት ውጤታማነት አሁን የምናየውን ፈተና ለማለፍ በስትራቴጂ ማገልገል እና ልዩ ልዩ ችግሮችን እንደ አመጣጣቸው ለማለፍ በትጋት የመሠራት ስልትን መዘርጋት ላይ ይተጋል፡፡ “ ቀኖች ክፉዎች ናቸው እና ዘመኑን ዋጁ” ኤፌ5፡16

በፌስቡክ ያግኙን

መልእክታት

የቅዱስ ፓትርያርኩ መልእክት

የሰ/ት/ቤቶች አንድነት መጠንከር አለበት ። የሰ/ት/ቤቶች መዋቅር ዓለም አቀፋዊ አገልግሎት እና ቤተ ክርስቲያን ኃላፊነት የሰጠችው መዋቅር ነው፡፡ ለዚህም በሀሉም መዋቅር በአንድነት ሥትሠሩ ለቤተ ክርስቲያን ፀጋ ለእኛም ደስታችን ናችሁ፡፡

በ2013 ዓ.ም ዓመታዊ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ መልእክት የተወሰደ

የመምሪያው ሊቀ ጳጳስ መልእክት

የቤተ ክርስቲያናችን ተተኪ ትውልድ የሚፈራበት ተቋም ነው። ከትውልድ ወደ ትውልድ የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ በመጠበቅ እና በማስጠበቅ ለማስቀጠል በዚህ ዘመን ሰ/ት/ቤቶች አንድነት በጣም አስፈላጊ እና ተመሳሳይ አገልግሎት በሁሉም ቦታ ሥርዓቱን ጠብቆ ለማድረስ የሚረዳ በቅዱስ ሲኖዶስ ሕግ ተሰጥቶት በሁሉም የቤተ ክህነት መዋቅር የሚሠራበት ግዙፍ መዋቅር ነው፡፡ ለዚህም ሁሉም የቤተ ክርስቲያን አካል በሙሉ ቅድሚያ ሰጥቶ ድጋፍ እና እንክብካቤ ሊያደርግ ይገባል፡፡

በ2013 ዓ.ም ዓመታዊ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ መልእክት የተወሰደ

አስተያየትዎን ይጻፉልን