ርእይ

በ2030 የሰንበት ት/ቤቶች ተቋማዊ አቅም ጎልብቶና ተደራሽታቸው ሰፍቶ ፣ አባላት በወጥ ሥርዓተ ትምህርት ሁለንተናዊ አቅማቸው ተገንብቶ በቤተ ክርስቲያንና በሀገራዊ ጉዳዮች ጉልህና የተናበበ ሚና የሚጫወቱ ሆነው ማየት

ተልእኮ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተተኪ ትውልድ የሆኑ የሰንበት ት/ቤት አባላትን በተደራጀ መዋቅራዊ አንድነት፣ ወጥ በሆነ የትምህርት ሥርዓትና ግብዓት በማስተማር፣ የአገልጋዮችን አቅም በማሳደግ፣ ዘመኑን በዋጀ አሠራር፣ በተቀደሰ ሕይወት ቤተ ክርስቲያንን እና ሀገርን በሁለንተናዊ መልኩ የሚያገለግሉና የሚጠብቁ አገልጋዮችን ማፍራትና ማሰማራት

ዕሴቶች

እግዚአብሔርን መፍራት

ሰውን ማክበር

በፍቅር የሆነ አገልግሎት

ክርስቲያናዊ ኃላፊነትና ተጠያቂነት

ሁሉን በጥበብና ለመንፈሳዊ ዋጋ ማድረግ

ዓለም ዐቀፋዊ አገልግሎትን ማስፋት

ፅናትና ምስክርነት

ዘመኑን መቅደም፣ መዋጀት

ወቅታዊ ጉዳዮች

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሶዶ ዳጡ ወረዳ ከወሊሶ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኘው አሮ ባለ ወልድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተፈጸመውን እጅግ አሳዛኝ እና ኢ-ሲኖዶሳዊ የሆነ አስነዋሪ፤ ሕገ ወጥ የቀኖና ቤተ ክርስቲያን ጥሰት አስመልከቶ ቅዱስ ሲኖዶስ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት አስቸኳይ የምልዐተ ጉባዔ አድርጎ ያሳለፈው ውሳኔ ላይ የተሰጠ መግለጫ

ኢ-ቀኖናዊ የሆነውን “ሲመተ ኤጲስ ቆጶሳት” አስመልክቶ ከሀገር አቀፍ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የተሰጠ መግለጫ

ቀኖናዊ ሥርዓቷን ጠብቃና አስጠብቃ አያሌ ዘመናትን የተሻገረቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን  በተለይ ከጥቂት ዓመታት ወዲህ እየደረሰባት ካለው ፈተና፣ መሰናክል፣  መከራ እና ውጣ ውረድ  በእግዚአብሔር ቸርነት ተጠብቃ አሁን ካለንበት ዘመን ደርሳለች ::  ዛሬ ግን ከፈተናዎች ሁሉ የከፋው ፈተና የበጐች እረኛ አድርጋ ሾማ እስከ ማዕረገ ጵጵስና ባከበረቻቸው ልጆቿ  ተፈጽሞባታል።  መንጋውን እንዲጠብቁ የመረጠቻቸው ልጆቿ ሊያፈርሷትና ሊከፍሏት  መነሳታቸው  በእጅጉ አሳዝኖናል ::ይኸንን ኢ -ቀኖናዊ  ተግባርም በጽኑ እንቃወማለን።

በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት የሚገኙ የሰንበት ትምህርት ቤቶች የማጠቃለያ ፈተና  ተሰጠ

በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሥር በሚገኙ ሰንበት ትምህርት ቤቶች በሀገረ ስብከቱ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት አስተባባሪነት አዲሱን ሥርዓተ ትምህርት ተግባራዊ ባደረጉ ሰ/ት/ቤቶች ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየው ማጠቃለያ ፈተና በዛሬው ዕለት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።

በዓለ ጰራቅሊጦስ

ጰራቅሊጦስ የሚለው ቃል ከሦስቱ አካላት አንዱ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ መጠሪያ ሲኾን ፣ ትርጕሙም በጽርዕ (ግሪክ) ቋንቋ ናዛዚ (የሚናዝዝ)፣ መጽንዒ (የሚያጸና)፣ መስተፍሥሒ (የሚያስደስት) ማለት ነው፡፡ በዓለ ጰራቅሊጦስ በሌላ ቃል በዓለ ጰንጠቆስጤ በመባልም ይታወቃል፡፡ ይኸውም በግሪክ ቋንቋ በዓለ ኀምሳ፣ የፋሲካ ኀምሳኛ ዕለት፣ በዓለ ሠዊት (የእሸት፣ የመከር በዓል) ማለት ነው።

የአንድነቱ መልእክት

ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት

ዘመንን በአግባቡ መሻገር የሚቻለው የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ወቅቱን ጠብቆ እንደየዘመኑ አኗኗር አቀራረቡን እና ተደራሸነቱን በማስፋት ሲሆን ጉዞው ዕድልና ችግርን ጎን ለጎን የሚያስተናገዱበት በመሆኑ በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት ቅዱስ ጳውሎስ ለክርስቲያኖች ባስተማረው ትምህርት “ የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሯችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፣የኑሯቸውን ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታችሁ ምሰሏቸው፡፡ ዕብ 13፡7 ያለውን መሠረት በመጠበቅ እና አሁን ያለውን የአገልግሎት ከባቢ በመረዳት ለሰ/ት/ቤቶች አገልግሎት ውጤታማነት አሁን የምናየውን ፈተና ለማለፍ በስትራቴጂ ማገልገል እና ልዩ ልዩ ችግሮችን እንደ አመጣጣቸው ለማለፍ በትጋት የመሠራት ስልትን መዘርጋት ላይ ይተጋል፡፡ “ ቀኖች ክፉዎች ናቸው እና ዘመኑን ዋጁ” ኤፌ5፡16

በፌስቡክ ያግኙን

መልእክታት

የቅዱስ ፓትርያርኩ መልእክት

የሰ/ት/ቤቶች አንድነት መጠንከር አለበት ። የሰ/ት/ቤቶች መዋቅር ዓለም አቀፋዊ አገልግሎት እና ቤተ ክርስቲያን ኃላፊነት የሰጠችው መዋቅር ነው፡፡ ለዚህም በሀሉም መዋቅር በአንድነት ሥትሠሩ ለቤተ ክርስቲያን ፀጋ ለእኛም ደስታችን ናችሁ፡፡

በ2013 ዓ.ም ዓመታዊ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ መልእክት የተወሰደ

የመምሪያው ሊቀ ጳጳስ መልእክት

የቤተ ክርስቲያናችን ተተኪ ትውልድ የሚፈራበት ተቋም ነው። ከትውልድ ወደ ትውልድ የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ በመጠበቅ እና በማስጠበቅ ለማስቀጠል በዚህ ዘመን ሰ/ት/ቤቶች አንድነት በጣም አስፈላጊ እና ተመሳሳይ አገልግሎት በሁሉም ቦታ ሥርዓቱን ጠብቆ ለማድረስ የሚረዳ በቅዱስ ሲኖዶስ ሕግ ተሰጥቶት በሁሉም የቤተ ክህነት መዋቅር የሚሠራበት ግዙፍ መዋቅር ነው፡፡ ለዚህም ሁሉም የቤተ ክርስቲያን አካል በሙሉ ቅድሚያ ሰጥቶ ድጋፍ እና እንክብካቤ ሊያደርግ ይገባል፡፡

በ2013 ዓ.ም ዓመታዊ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ መልእክት የተወሰደ

አስተያየትዎን ይጻፉልን