ርእይ

በ2030 የሰንበት ት/ቤቶች ተቋማዊ አቅም ጎልብቶና ተደራሽታቸው ሰፍቶ ፣ አባላት በወጥ ሥርዓተ ትምህርት ሁለንተናዊ አቅማቸው ተገንብቶ በቤተ ክርስቲያንና በሀገራዊ ጉዳዮች ጉልህና የተናበበ ሚና የሚጫወቱ ሆነው ማየት

ተልእኮ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተተኪ ትውልድ የሆኑ የሰንበት ት/ቤት አባላትን በተደራጀ መዋቅራዊ አንድነት፣ ወጥ በሆነ የትምህርት ሥርዓትና ግብዓት በማስተማር፣ የአገልጋዮችን አቅም በማሳደግ፣ ዘመኑን በዋጀ አሠራር፣ በተቀደሰ ሕይወት ቤተ ክርስቲያንን እና ሀገርን በሁለንተናዊ መልኩ የሚያገለግሉና የሚጠብቁ አገልጋዮችን ማፍራትና ማሰማራት

ዕሴቶች

እግዚአብሔርን መፍራት

ሰውን ማክበር

በፍቅር የሆነ አገልግሎት

ክርስቲያናዊ ኃላፊነትና ተጠያቂነት

ሁሉን በጥበብና ለመንፈሳዊ ዋጋ ማድረግ

ዓለም ዐቀፋዊ አገልግሎትን ማስፋት

ፅናትና ምስክርነት

ዘመኑን መቅደም፣ መዋጀት

ወቅታዊ ጉዳዮች

ቤተ ክርስቲያን ምን ዓይነት አመራር ያስፈልጋታል?

ቤተ ክርስቲያን ምን ዓይነት አመራር ያስፈልጋታል?

መንፈሳዊ ጉድለቶችን በማስተካከል፣ አስተዳደራዊ ሥርዓትን በማዘመን፣ አሳታፊና ተደራሽ የሆነ አሠራር በመዘርጋት፣ ሕግና ሥርዓትን የተከተለ የሰው ሀብትና የፋይናንስ አስተዳደር ዕውን በማድረግ ያስፈልጋል። በተለይም ወደላይኛው መዓረግ የሚመጡ አባቶች የሚመረጡበት ጥብቅ መስፈርት በማስቀመጥ ግልጽና ተጠያቂነት ያለበት የአሿሿም ሥርዓት፣ የምእመናንን ሱታፌ ያማከለ ጥቆማ እና እግዚአብሔርን ያስቀደመ ምርጫ በማድረግ ይደልዎ የሚባሉ አባቶችን ብቻ መሾም ይገባል።

“የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸውማል።” መዝ 33:7

በየዓመቱ ሰኔ 12 ቀን የመልአኩ የቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል የሚከበረው በዚህ ዕለት መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል የባሕራንን የሞት ደብዳቤ ወደ ሕይወት የቀየረበት እና ቅድስት አፎምያን ከሰይጣን ያዳነበትን በማሰብ ነው።

፲፪ኛው የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ የአቋም መግለጫ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ የዓለም አቀፍ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት አስራ ኹለተኛው ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ከግንቦት 26-27 ቀን 2015 ዓ.ም ተከናውኖ በቀረቡ ሪፖርቶች፣ ጥናታዊ ሰነዶች፣ ከሁሉም አካባቢዎች ከቀረቡ የውይይት ግብዓቶች በመነሳት ባለ አስራ አንድ ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል።

ዕርገተ ክርስቶስ

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተነሣ በኋላ ባሉት ፵ ቀናት በተለያዩ ጊዜያት ለደቀመዛሙርቱ ተገልጾ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ያስተምራቸው ነበር፡፡ ስለክርስቶስ የተነገረውን የቅዱሳት መጻሕፍት ትንቢት ከዚያ በፊት አላስተዋሉም ነበር፡፡ ጌታችንም ስለ እርሱ የተጻፉትን ተረጎመላቸው፣ አዕምሮቸውንም ከፈተላቸው መጻሕፍትንም አስተዋሉ፤ እምነታቸውን አጸናላቸው፡፡ ስለ ትንሣኤው የነበራቸውን ጥርጣሬም ከልቦናቸው አጸዳላቸው፡፡

የአንድነቱ መልእክት

ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት

ዘመንን በአግባቡ መሻገር የሚቻለው የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ወቅቱን ጠብቆ እንደየዘመኑ አኗኗር አቀራረቡን እና ተደራሸነቱን በማስፋት ሲሆን ጉዞው ዕድልና ችግርን ጎን ለጎን የሚያስተናገዱበት በመሆኑ በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት ቅዱስ ጳውሎስ ለክርስቲያኖች ባስተማረው ትምህርት “ የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሯችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፣የኑሯቸውን ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታችሁ ምሰሏቸው፡፡ ዕብ 13፡7 ያለውን መሠረት በመጠበቅ እና አሁን ያለውን የአገልግሎት ከባቢ በመረዳት ለሰ/ት/ቤቶች አገልግሎት ውጤታማነት አሁን የምናየውን ፈተና ለማለፍ በስትራቴጂ ማገልገል እና ልዩ ልዩ ችግሮችን እንደ አመጣጣቸው ለማለፍ በትጋት የመሠራት ስልትን መዘርጋት ላይ ይተጋል፡፡ “ ቀኖች ክፉዎች ናቸው እና ዘመኑን ዋጁ” ኤፌ5፡16

በፌስቡክ ያግኙን

መልእክታት

የቅዱስ ፓትርያርኩ መልእክት

የሰ/ት/ቤቶች አንድነት መጠንከር አለበት ። የሰ/ት/ቤቶች መዋቅር ዓለም አቀፋዊ አገልግሎት እና ቤተ ክርስቲያን ኃላፊነት የሰጠችው መዋቅር ነው፡፡ ለዚህም በሀሉም መዋቅር በአንድነት ሥትሠሩ ለቤተ ክርስቲያን ፀጋ ለእኛም ደስታችን ናችሁ፡፡

በ2013 ዓ.ም ዓመታዊ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ መልእክት የተወሰደ

የመምሪያው ሊቀ ጳጳስ መልእክት

የቤተ ክርስቲያናችን ተተኪ ትውልድ የሚፈራበት ተቋም ነው። ከትውልድ ወደ ትውልድ የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ በመጠበቅ እና በማስጠበቅ ለማስቀጠል በዚህ ዘመን ሰ/ት/ቤቶች አንድነት በጣም አስፈላጊ እና ተመሳሳይ አገልግሎት በሁሉም ቦታ ሥርዓቱን ጠብቆ ለማድረስ የሚረዳ በቅዱስ ሲኖዶስ ሕግ ተሰጥቶት በሁሉም የቤተ ክህነት መዋቅር የሚሠራበት ግዙፍ መዋቅር ነው፡፡ ለዚህም ሁሉም የቤተ ክርስቲያን አካል በሙሉ ቅድሚያ ሰጥቶ ድጋፍ እና እንክብካቤ ሊያደርግ ይገባል፡፡

በ2013 ዓ.ም ዓመታዊ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ መልእክት የተወሰደ

አስተያየትዎን ይጻፉልን