ርእይ

በ2030 የሰንበት ት/ቤቶች ተቋማዊ አቅም ጎልብቶና ተደራሽታቸው ሰፍቶ ፣ አባላት በወጥ ሥርዓተ ትምህርት ሁለንተናዊ አቅማቸው ተገንብቶ በቤተ ክርስቲያንና በሀገራዊ ጉዳዮች ጉልህና የተናበበ ሚና የሚጫወቱ ሆነው ማየት

ተልእኮ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተተኪ ትውልድ የሆኑ የሰንበት ት/ቤት አባላትን በተደራጀ መዋቅራዊ አንድነት፣ ወጥ በሆነ የትምህርት ሥርዓትና ግብዓት በማስተማር፣ የአገልጋዮችን አቅም በማሳደግ፣ ዘመኑን በዋጀ አሠራር፣ በተቀደሰ ሕይወት ቤተ ክርስቲያንን እና ሀገርን በሁለንተናዊ መልኩ የሚያገለግሉና የሚጠብቁ አገልጋዮችን ማፍራትና ማሰማራት

ዕሴቶች

እግዚአብሔርን መፍራት

ሰውን ማክበር

በፍቅር የሆነ አገልግሎት

ክርስቲያናዊ ኃላፊነትና ተጠያቂነት

ሁሉን በጥበብና ለመንፈሳዊ ዋጋ ማድረግ

ዓለም ዐቀፋዊ አገልግሎትን ማስፋት

ፅናትና ምስክርነት

ዘመኑን መቅደም፣ መዋጀት

ወቅታዊ ጉዳዮች

“ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁ” ገላ. ፪፡፲፬

“ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁ” ገላ. ፪፡፲፬

ምእመናን በሚሰሙት ቋንቋ መማር አለባቸው፣ አገልግሎቱ በሚፈለገው መጠን መስፋት አለበት የሚለው ቤተ ክርስቲያን የተመሠረተችበት መሠረታዊ ዓላማ ስለሆነ ቸል ሊባል አይገባውም። እንዲያውም እንዲህ ዐይነቱ ጥያቄ በተገልጋዩ ሳይቀርብ አገልግሎቱን በሚመራው መዋቅር ቀድሞ መታሰብ ያለበት ነው። ይህን ለመሰሉ ጥያቄዎች አግባብነት ያለው መልስ በጊዜው አለመሰጠቱ የጥያቄውን ዐውድ እንዲቀየር፣ ጥያቄውም በሌሎች በማይመለከታቸው አካላት ሳይቀር እንዲጠለፍ ዕድል ይፈጥራል። አሁን በገቢር በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እያየን ያለነውም ይህኑ ነው። በሚሰሙት ቋንቋ መማር የሚገባቸውን የእምነቱ ተከታዮች አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ የቤተ ክርስቲያን ሰማያዊ ግዴታ ነው። ቤተ ክርስቲያንን ማንም በዚህ ቋንቋ አስተምሪ በዚህ አታስተምሪ ብሎ ትእዛዝ ሊሰጣት አይችልም፣ አይገባምም።
ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ

የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት በኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ሂደት ላይ ያለውን ጥያቄ በደብዳቤ አሳወቀ

የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት በኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ሂደት ላይ ያለውን ጥያቄ ለአስመራጭ ኮሚቴው በደብዳቤ አሳውቋል። የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት፤ በቀኖና ቤተ ክርስቲያን አግባብ የኢጲስ ቆጶሳት ምልመላ፣ መስፈርት እና ሂደት ለሕዝብ ይፋ ሆኖ በግልፅ መከናወን እንደሚኖርበት በደብዳቤው አጽእኖት ሰጥቷል። በተጨማሪም፤ እስካሁን በተኼደበት መንገድ ከተቀጠለ፤ የሕግና የቀኖና ጥሰት፣ እንዲሁም ይሁንታ የማጣት ጉዳይ ሊከሰት እንደሚችል አሳስቧል። ደብዳቤውን የተረከቡት የአስመራጭ ኮሚቴው ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ፣ ደብዳቤውን ለኮሚቴው አቅርበው እንደሚመክሩበት አሳውቀዋል።
እርሱን የምሾመው ለመንበሩ ክብር እንዲሰጠው ነው

እርሱን የምሾመው ለመንበሩ ክብር እንዲሰጠው ነው

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለጳጳሳት ምርጫ የምትጨነቀውም ለመንጋው የማይራሩ ክፉዎች ተሾመው ምእመናንን ከእግዚአብሔር እንዳያራርቋቸው ነው። ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን የጳጳሳት ምርጫ የሚያሳስባት ዓላማው ሰማያዊ፣ ተልእኮው ሰውን ለመንግሥተ ሰማያት ማብቃት በመሆኑ ነው። ጳጳሳት ኖላዊ መሆናቸውን የተረዱ አባቶችም መንበራቸው ክፍት በሆኑ አህጉረ ስብከት ላይ የሚመድቧቸው አባቶች ማንነት ያሳስባቸዋል። ጉዳዩ አሳሳቢ የሚሆንበት የመጀመሪያው ምክንያት ለጵጵስና የሚመረጡ አባቶች ምግባረ ብልሹ ከሆኑ ሰዎችን ለድኅነት ማብቃት ሲገባቸው ከድኅነት ስለሚያርቋቸው ነው።
ኤጲስ ቆጶስ ለመሾም የሚያገለግለው መስፈርት

ኤጲስ ቆጶስ ለመሾም የሚያገለግለው መስፈርት

ኤጲስ ቆጶሳትን ለማጨት በወጣው መስፈርት መሠረት ለሢመት የሚገቡትን መፈለግ፣ ጣልቃ የሚገቡትን አካላት ድርጊት በማስቆም ለቤተ ክርስቲያን የሚሆኑትን ብቻ መሾም ይገባል። አባቶችን ለኤጲስ ቆጰስነት ለማጨት ሲታሰብ ሃይማኖት ከምግባር የሠመረላቸው መሆኑ ጥያቄ ውስጥ የሚገባም አይደለም። ዕውቀት፣ ጥብዓትና ርኅራኄ ያላቸው መሆንም ይገባቸዋል። እነዚህን መስፈርቶች ያሟሉ አባቶች ከተመረጡ ለሀገረ ስብከታቸውም ለምእመናንም ኖላዊ መሆናቸውን ተረድተው መንጋውን ለመጠበቅ ይተጋሉ። የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል የሚባለውም ኃላፊነቱ ከባድ በመሆኑ ነው። የተጣለበትን ኃላፊነት ያልተረዳ ግዴለሽ ሰዎች ከተሾሙ በራሳቸው ኃጢአት ብቻ ሳይሆን በሌሎችም ኃጢአት እንደሚጠየቁ መረዳት ይገባል።

የአንድነቱ መልእክት

ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት

ዘመንን በአግባቡ መሻገር የሚቻለው የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ወቅቱን ጠብቆ እንደየዘመኑ አኗኗር አቀራረቡን እና ተደራሸነቱን በማስፋት ሲሆን ጉዞው ዕድልና ችግርን ጎን ለጎን የሚያስተናገዱበት በመሆኑ በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት ቅዱስ ጳውሎስ ለክርስቲያኖች ባስተማረው ትምህርት “ የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሯችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፣የኑሯቸውን ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታችሁ ምሰሏቸው፡፡ ዕብ 13፡7 ያለውን መሠረት በመጠበቅ እና አሁን ያለውን የአገልግሎት ከባቢ በመረዳት ለሰ/ት/ቤቶች አገልግሎት ውጤታማነት አሁን የምናየውን ፈተና ለማለፍ በስትራቴጂ ማገልገል እና ልዩ ልዩ ችግሮችን እንደ አመጣጣቸው ለማለፍ በትጋት የመሠራት ስልትን መዘርጋት ላይ ይተጋል፡፡ “ ቀኖች ክፉዎች ናቸው እና ዘመኑን ዋጁ” ኤፌ5፡16

በፌስቡክ ያግኙን

መልእክታት

የቅዱስ ፓትርያርኩ መልእክት

የሰ/ት/ቤቶች አንድነት መጠንከር አለበት ። የሰ/ት/ቤቶች መዋቅር ዓለም አቀፋዊ አገልግሎት እና ቤተ ክርስቲያን ኃላፊነት የሰጠችው መዋቅር ነው፡፡ ለዚህም በሀሉም መዋቅር በአንድነት ሥትሠሩ ለቤተ ክርስቲያን ፀጋ ለእኛም ደስታችን ናችሁ፡፡

በ2013 ዓ.ም ዓመታዊ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ መልእክት የተወሰደ

የመምሪያው ሊቀ ጳጳስ መልእክት

የቤተ ክርስቲያናችን ተተኪ ትውልድ የሚፈራበት ተቋም ነው። ከትውልድ ወደ ትውልድ የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ በመጠበቅ እና በማስጠበቅ ለማስቀጠል በዚህ ዘመን ሰ/ት/ቤቶች አንድነት በጣም አስፈላጊ እና ተመሳሳይ አገልግሎት በሁሉም ቦታ ሥርዓቱን ጠብቆ ለማድረስ የሚረዳ በቅዱስ ሲኖዶስ ሕግ ተሰጥቶት በሁሉም የቤተ ክህነት መዋቅር የሚሠራበት ግዙፍ መዋቅር ነው፡፡ ለዚህም ሁሉም የቤተ ክርስቲያን አካል በሙሉ ቅድሚያ ሰጥቶ ድጋፍ እና እንክብካቤ ሊያደርግ ይገባል፡፡

በ2013 ዓ.ም ዓመታዊ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ መልእክት የተወሰደ

አስተያየትዎን ይጻፉልን