ርእይ

በ2030 የሰንበት ት/ቤቶች ተቋማዊ አቅም ጎልብቶና ተደራሽታቸው ሰፍቶ ፣ አባላት በወጥ ሥርዓተ ትምህርት ሁለንተናዊ አቅማቸው ተገንብቶ በቤተ ክርስቲያንና በሀገራዊ ጉዳዮች ጉልህና የተናበበ ሚና የሚጫወቱ ሆነው ማየት

ተልእኮ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተተኪ ትውልድ የሆኑ የሰንበት ት/ቤት አባላትን በተደራጀ መዋቅራዊ አንድነት፣ ወጥ በሆነ የትምህርት ሥርዓትና ግብዓት በማስተማር፣ የአገልጋዮችን አቅም በማሳደግ፣ ዘመኑን በዋጀ አሠራር፣ በተቀደሰ ሕይወት ቤተ ክርስቲያንን እና ሀገርን በሁለንተናዊ መልኩ የሚያገለግሉና የሚጠብቁ አገልጋዮችን ማፍራትና ማሰማራት

ዕሴቶች

እግዚአብሔርን መፍራት

ሰውን ማክበር

በፍቅር የሆነ አገልግሎት

ክርስቲያናዊ ኃላፊነትና ተጠያቂነት

ሁሉን በጥበብና ለመንፈሳዊ ዋጋ ማድረግ

ዓለም ዐቀፋዊ አገልግሎትን ማስፋት

ፅናትና ምስክርነት

ዘመኑን መቅደም፣ መዋጀት

ወቅታዊ ጉዳዮች

‹‹በበጎነት ላይ ዕውቀትን ጨምሩ›› (፪ኛ ጴጥ. ፩፥፭-፯)

‹‹በበጎነት ላይ ዕውቀትን ጨምሩ›› ፪ኛ ጴጥ. ፩፥፭-፯

እግዚአብሔር ሕዝቡን ይመሩ ዘንድ የወደዳቸውን ኖሎት አንድም በሕዝበ ክርስቲያኑ በኩል ይደልዎ ይደልዎ አስብሎ አልያም እንደ ድሜጥሮስ ድንግል በተኣምራት ክብራቸውን ገልጦ ይሾማቸዋል፡፡ በሁለቱም የአመራረጥ መንገዶች ማዕከላዊው ጉዳይ ሕዝቡ መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ ምእመናን ሕግጋተ እግዚአብሔርን የሚማሩት በዋናነት ከኤጲስ ቆጶሱ፣ ከካህኑ ከናፍር ነው፤ የእግዚአብሔር እንደራሴ ነውና፡፡ በዕውቀቱ የታመመች ነፍስን የሚፈውስበት መድኃኒት ከቃለ እግዚአብሔር ይቀምማል፡፡ እየመጠነ ለግልገሎቹ፣ ለጠቦቶቹና ለበጎቹ ይሰጣል፡፡ ካህኑ በትምህርት ላሳመናቸው ልጆቹ በሕይወትም አርአያ ሆኖ፣ ከሥነ ምግባር ርካብ ሳይወርዱ ወደ ሰማያዊ ርስት መምራት የሚችልበትን ዕውቀትና ክህሎትም እንዲኖረው ይፈለጋል፡፡
ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳትና የምእመናን ሱታፌ

ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳትና የምእመናን ሱታፌ

ምእመናን መንጋውን ለመጠበቅ፣ ቤተ ክርስቲያንን ለማገልግል በሚመረጡ ኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ላይ ያላቸው ሱታፌ ከፍተኛ ነው። ተሿሚዎች ይገባቸዋል ተብለው ለሹመቱ ብቁ መሆናቸው የሚረጋገጠው በምእመናን ምስክርነት ነው። ምእመናን በሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት የነበራቸው ተሳትፎ የመምረጥና የምስክርነት ብቻ ሳይሆን በመመረጥም ጭምር ነበር። ይህንም በእነ ዲሜጥሮስ ታሪክ ማስታወስ የምንችለው ነው። ምእመናን ቤታቸው በሆነች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ጸንተው ለመኖር የሚሾምላቸውን አካል የማወቅ፣ የመምረጥ፣ የማይገባው መሆኑን ካወቁ ደግሞ ሊሾምብን አይገባም ብለው የመናገር ፈቃዱና ነጻነቱ ስላላቸው፣ ይህም በቀኖና ቤተ ክርስቲያን ጸንቶ ሲሠራበት የኖረ ስለሆነ ይህ ሥልጣናቸው ሊከበርላቸው ይገባል።
እንኳን ደስ አለዎ ወይስ እግዚአብሔር ያስችልዎ?

እንኳን ደስ አለዎ ወይስ እግዚአብሔር ያስችልዎ?

በጥንቷ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ በርካታ ቅዱሳን አበው ለኤጲስ ቆጰስነት ሢመት የተገባን አይደለንም ብለው ሥልጣንን አምርረው ሲሸሹ በተደጋጋሚ ታይተዋል፡፡ የእስክንድርያው ፓትርያርክ ቅዱስ አትናቴዎስ ከአራተኛው ክፍለ ዘመን የቤተ ክርስቲያን ፈርጦች ውስጥ ከቀዳሚዎቹ የሚመደብ ነው፡፡ ትምህርቱ፣ መንፈሳዊ ቅንዓቱ፣ ተጋድሎው እና አጠቃላይ አባትነቱ ሐዋርያዊ የሚል ቅጽል አጎናጽፎታል፡፡ ገና በወጣትነቱ ፓትርያርኩን እለ እስክንድሮስን ተከትሎ በኒቂያ ጉባኤ በመገኘት በጥልቅ የነገረ መለኮት ዕውቀቱ አርዮስን ተከራክሮ የረታው፣ አትናቴዎስ በተባሕትዎ አኗኗሩም ይታወቃል፡፡
አክሊል የሆነችው ሢመት መርጣ የምታርፍባቸው አባቶች

አክሊል የሆነችው ሢመት መርጣ የምታርፍባቸው አባቶች

የጵጵስና አክሊል የምታርፍባቸው አባቶች ሲመረጡ መንፈሳዊ ሕይወት ያላቸው መሆናቸው ቀዳሚው የምርጫ መስፈርት ሲሆን የአስተዳደር ብቃት ደግሞ ሁለተኛው መስፈርት መሆን ይገባዋል። ለመንፈሳዊው ሹመት ብቁ የሆኑትን ማግኘት የሚቻለውም በብልጣ ብልጥነት ወይም እኔ ያልኩት ካልሆነ በሚል ግትርነትም አይደለም። ገንዘብ ሰጥተው ለመሾም የሚሞክሩትንም፣ ገንዘብ ተቀብለው ለማሾም የሚጣጣሩትንም. የእኔ ወገን ብቻ ይሾምልኝ የሚሉትም ድርጊታቸው ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን ያፈነገጠ መሆኑን ማወቅ አለባቸው። ለመንፈሳዊው ሹመት የሚታጩ አባቶች አምላክን የሚያስደስቱ፣ ሰዎችን ወደ አምላካቸው ለማቅረብ የማይታክቱ፣ ምድራውያንን ከሰማያውያን የሚያገናኙ መሆን እንዳለባቸው ነው።

የአንድነቱ መልእክት

ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት

ዘመንን በአግባቡ መሻገር የሚቻለው የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ወቅቱን ጠብቆ እንደየዘመኑ አኗኗር አቀራረቡን እና ተደራሸነቱን በማስፋት ሲሆን ጉዞው ዕድልና ችግርን ጎን ለጎን የሚያስተናገዱበት በመሆኑ በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት ቅዱስ ጳውሎስ ለክርስቲያኖች ባስተማረው ትምህርት “ የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሯችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፣የኑሯቸውን ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታችሁ ምሰሏቸው፡፡ ዕብ 13፡7 ያለውን መሠረት በመጠበቅ እና አሁን ያለውን የአገልግሎት ከባቢ በመረዳት ለሰ/ት/ቤቶች አገልግሎት ውጤታማነት አሁን የምናየውን ፈተና ለማለፍ በስትራቴጂ ማገልገል እና ልዩ ልዩ ችግሮችን እንደ አመጣጣቸው ለማለፍ በትጋት የመሠራት ስልትን መዘርጋት ላይ ይተጋል፡፡ “ ቀኖች ክፉዎች ናቸው እና ዘመኑን ዋጁ” ኤፌ5፡16

በፌስቡክ ያግኙን

መልእክታት

የቅዱስ ፓትርያርኩ መልእክት

የሰ/ት/ቤቶች አንድነት መጠንከር አለበት ። የሰ/ት/ቤቶች መዋቅር ዓለም አቀፋዊ አገልግሎት እና ቤተ ክርስቲያን ኃላፊነት የሰጠችው መዋቅር ነው፡፡ ለዚህም በሀሉም መዋቅር በአንድነት ሥትሠሩ ለቤተ ክርስቲያን ፀጋ ለእኛም ደስታችን ናችሁ፡፡

በ2013 ዓ.ም ዓመታዊ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ መልእክት የተወሰደ

የመምሪያው ሊቀ ጳጳስ መልእክት

የቤተ ክርስቲያናችን ተተኪ ትውልድ የሚፈራበት ተቋም ነው። ከትውልድ ወደ ትውልድ የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ በመጠበቅ እና በማስጠበቅ ለማስቀጠል በዚህ ዘመን ሰ/ት/ቤቶች አንድነት በጣም አስፈላጊ እና ተመሳሳይ አገልግሎት በሁሉም ቦታ ሥርዓቱን ጠብቆ ለማድረስ የሚረዳ በቅዱስ ሲኖዶስ ሕግ ተሰጥቶት በሁሉም የቤተ ክህነት መዋቅር የሚሠራበት ግዙፍ መዋቅር ነው፡፡ ለዚህም ሁሉም የቤተ ክርስቲያን አካል በሙሉ ቅድሚያ ሰጥቶ ድጋፍ እና እንክብካቤ ሊያደርግ ይገባል፡፡

በ2013 ዓ.ም ዓመታዊ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ መልእክት የተወሰደ

አስተያየትዎን ይጻፉልን