ርእይ

በ2030 የሰንበት ት/ቤቶች ተቋማዊ አቅም ጎልብቶና ተደራሽታቸው ሰፍቶ ፣ አባላት በወጥ ሥርዓተ ትምህርት ሁለንተናዊ አቅማቸው ተገንብቶ በቤተ ክርስቲያንና በሀገራዊ ጉዳዮች ጉልህና የተናበበ ሚና የሚጫወቱ ሆነው ማየት

ተልእኮ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተተኪ ትውልድ የሆኑ የሰንበት ት/ቤት አባላትን በተደራጀ መዋቅራዊ አንድነት፣ ወጥ በሆነ የትምህርት ሥርዓትና ግብዓት በማስተማር፣ የአገልጋዮችን አቅም በማሳደግ፣ ዘመኑን በዋጀ አሠራር፣ በተቀደሰ ሕይወት ቤተ ክርስቲያንን እና ሀገርን በሁለንተናዊ መልኩ የሚያገለግሉና የሚጠብቁ አገልጋዮችን ማፍራትና ማሰማራት

ዕሴቶች

እግዚአብሔርን መፍራት

ሰውን ማክበር

በፍቅር የሆነ አገልግሎት

ክርስቲያናዊ ኃላፊነትና ተጠያቂነት

ሁሉን በጥበብና ለመንፈሳዊ ዋጋ ማድረግ

ዓለም ዐቀፋዊ አገልግሎትን ማስፋት

ፅናትና ምስክርነት

ዘመኑን መቅደም፣ መዋጀት

ወቅታዊ ጉዳዮች

ተሿሚዎችን ለምእመናን አለማሳወቅ የሚያስከትለው መዘዝ

ተሿሚዎችን ለምእመናን አለማሳወቅ የሚያስከትለው መዘዝ

በዘመናችን ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን…
ፍኖተ-ጎርጎርዮስ

ፍኖተ-ጎርጎርዮስ

ሕዝበ ክርስቲያኑ የቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙን ትምህርቱን ሰምተው ግብሩን ዐይተው ሲወዱት ኖረዋል፡፡ ወላጆቹን በተለይ በእርግና ዘመን ላይ የነበረ አባቱን ጠይቆ ለመመለስ ወደ ወላጆቹ በሔደበት አጋጣሚ በሕዝቡ ግፊት ሥልጣነ ክህነት እንዲቀበል ተደረገ፡፡ እርሱ ግን ገዳማዊ ሕይወትን እጅግ ወድዶ ነበርና በብሕትውና ወደሚኖርበት ገዳም ሔዶ ተደበቀ፡፡ የቃልም የሕይወትም መምህር ነበር፤ በአንዲት በዓት ረጅም ጊዜ በጾም በጸሎት በመወሰን የሚታወቅ ገዳማዊ አባት፡፡ በትምህርትም ዓለማዊውን ትምህርት ከቂሣሪያ እስከ አቴና በመጓዝ በግሪክ ፍልስፍና የተራቀቀ፣ በመንፈሳዊው ትምህርትም ከሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ በኋላ ነባቤ መለኮት (ታኦሎጎስ) እስከ መባል የደረሰ የነገረ መለኮት ሊቅ ነበር፡፡
ሄሮድያዳ ዛሬም የዮሐንስን አንገት ለማስቀላት እየተዋጋች ነው።

ሄሮድያዳ ዛሬም የዮሐንስን አንገት ለማስቀላት እየተዋጋች ነው

በእኛ ዘመን ጥቂት የማይባሉ መነኮሳት ሢመት ጣዖት ሆኖ ሲፈትናቸው እያየን ነው፡፡ አንዳንዶቹ ጵጵስናቸው ቤተ መቅደስን ሳይሆን ቤተ መንግሥትን ለማገልገል የተቀበሉት ሥልጣን ይመስል በቤተ መቅደስ ተኮፍሰው፣ በቤተ መንግሥት አደግድገው ይታያሉ፡፡ ከእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ክብር በላይ ሢመቱ ጎልቶ እየታየ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ፍቅረ ሢመት የሚሠሩትን ያሳጣቸው መነኮሳትን ዕፍረት የለሽ አስረሽ ምችው (ለሹመት መቅበጥበጥ) እንድታስተናግድ ተገዳለች፡፡ አንዱ በሲሞናዊነት ሌላው በዘውገኝነት ቅኝት ዳንኪራ ይረግጣል፡፡ አንዱ የባለሥልጣናትን ፍላጎት፣ ሌላው ወገኔ ያላቸውን ጳጳሳት መሻት በመፈጸም ኤጲስ ቆጶስነትን ሊገበያት ደፋ ቀና ይላል፡፡
“ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁ” ገላ. ፪፡፲፬

“ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁ” ገላ. ፪፡፲፬

ምእመናን በሚሰሙት ቋንቋ መማር አለባቸው፣ አገልግሎቱ በሚፈለገው መጠን መስፋት አለበት የሚለው ቤተ ክርስቲያን የተመሠረተችበት መሠረታዊ ዓላማ ስለሆነ ቸል ሊባል አይገባውም። እንዲያውም እንዲህ ዐይነቱ ጥያቄ በተገልጋዩ ሳይቀርብ አገልግሎቱን በሚመራው መዋቅር ቀድሞ መታሰብ ያለበት ነው። ይህን ለመሰሉ ጥያቄዎች አግባብነት ያለው መልስ በጊዜው አለመሰጠቱ የጥያቄውን ዐውድ እንዲቀየር፣ ጥያቄውም በሌሎች በማይመለከታቸው አካላት ሳይቀር እንዲጠለፍ ዕድል ይፈጥራል። አሁን በገቢር በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እያየን ያለነውም ይህኑ ነው። በሚሰሙት ቋንቋ መማር የሚገባቸውን የእምነቱ ተከታዮች አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ የቤተ ክርስቲያን ሰማያዊ ግዴታ ነው። ቤተ ክርስቲያንን ማንም በዚህ ቋንቋ አስተምሪ በዚህ አታስተምሪ ብሎ ትእዛዝ ሊሰጣት አይችልም፣ አይገባምም።

የአንድነቱ መልእክት

ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት

ዘመንን በአግባቡ መሻገር የሚቻለው የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ወቅቱን ጠብቆ እንደየዘመኑ አኗኗር አቀራረቡን እና ተደራሸነቱን በማስፋት ሲሆን ጉዞው ዕድልና ችግርን ጎን ለጎን የሚያስተናገዱበት በመሆኑ በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት ቅዱስ ጳውሎስ ለክርስቲያኖች ባስተማረው ትምህርት “ የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሯችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፣የኑሯቸውን ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታችሁ ምሰሏቸው፡፡ ዕብ 13፡7 ያለውን መሠረት በመጠበቅ እና አሁን ያለውን የአገልግሎት ከባቢ በመረዳት ለሰ/ት/ቤቶች አገልግሎት ውጤታማነት አሁን የምናየውን ፈተና ለማለፍ በስትራቴጂ ማገልገል እና ልዩ ልዩ ችግሮችን እንደ አመጣጣቸው ለማለፍ በትጋት የመሠራት ስልትን መዘርጋት ላይ ይተጋል፡፡ “ ቀኖች ክፉዎች ናቸው እና ዘመኑን ዋጁ” ኤፌ5፡16

በፌስቡክ ያግኙን

መልእክታት

የቅዱስ ፓትርያርኩ መልእክት

የሰ/ት/ቤቶች አንድነት መጠንከር አለበት ። የሰ/ት/ቤቶች መዋቅር ዓለም አቀፋዊ አገልግሎት እና ቤተ ክርስቲያን ኃላፊነት የሰጠችው መዋቅር ነው፡፡ ለዚህም በሀሉም መዋቅር በአንድነት ሥትሠሩ ለቤተ ክርስቲያን ፀጋ ለእኛም ደስታችን ናችሁ፡፡

በ2013 ዓ.ም ዓመታዊ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ መልእክት የተወሰደ

የመምሪያው ሊቀ ጳጳስ መልእክት

የቤተ ክርስቲያናችን ተተኪ ትውልድ የሚፈራበት ተቋም ነው። ከትውልድ ወደ ትውልድ የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ በመጠበቅ እና በማስጠበቅ ለማስቀጠል በዚህ ዘመን ሰ/ት/ቤቶች አንድነት በጣም አስፈላጊ እና ተመሳሳይ አገልግሎት በሁሉም ቦታ ሥርዓቱን ጠብቆ ለማድረስ የሚረዳ በቅዱስ ሲኖዶስ ሕግ ተሰጥቶት በሁሉም የቤተ ክህነት መዋቅር የሚሠራበት ግዙፍ መዋቅር ነው፡፡ ለዚህም ሁሉም የቤተ ክርስቲያን አካል በሙሉ ቅድሚያ ሰጥቶ ድጋፍ እና እንክብካቤ ሊያደርግ ይገባል፡፡

በ2013 ዓ.ም ዓመታዊ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ መልእክት የተወሰደ

አስተያየትዎን ይጻፉልን