ለአገራችን ኢትዮጵያ ሰላምን ስጣት
ሊቀ ነቢያት ሙሴ እስራኤላውያን ከአሕዛብ ነገሥታት ጋር ጦርነት በሚያደርጉበት ወቅት ወንድሞቻችሁ ወደ ጦርነት ሔደው እናንተ ከቤታችሁ ተቀምጣችኋል ሲላቸው “እኛ ባሪያዎችህ ሁላችን ጋሻ ጦራችንን ይዘን በእግዚአብሔር ፊት ጌታችን እንደተናገረ ወደ ጦርነት እንሔዳለን” (ዘኁ. ፴፪፡፳፯) የሚል መልስ ሰጥተውታል። በዓለም ላይ ሰላም ሲታጣ አገራት ሰላም አስከባሪ ኃይል በመላክ ሰላምን በፈረስ አንገት፣ በጦር አንደበት ሊያመጧት ይሻሉ። የተከሠተውን የሰላም እጦት ወደ ነበረበት ለመመለስ ጦርነት ያውጃሉ። ሰላምን የሚሹ ሁሉ ለጦርነት እንዲዘጋጁ ዐዋጅ ይነግራሉ። ሰላም የጦርነት አለመኖር ቢሆንም የሚለካው በውጤቱ ነውና የተባለው ሰላም እስከሚመጣ ሕዝቡ በጦርነት ይሳተፋል። ይህ የዕለት ከዕለት የየአገራት አነዋወር መገለጫ ነው። Read more