የሰላም ዋጋው ስንት ነው?
ሰላም የሚለው ቃል ሲጠራ ቀላል ቢመስልም ዋጋው ግን በገንዘብ ከመተመን በላይ ነው፡፡ ሰላም እንኳን ለሰው ልጅ ለእንስሳት፣ ለአራዊት እና በጠቅላላው ለሥነ ፍጥረት በጣም አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ ሰላም ከሌለ ማንም ወጥቶ መግባት፣ ነግዶ ማትረፍ፣ አርሶ መብላት፣ ደግሶ መዳር አይችልም፡፡ ሠርቶ የመለወጥን ተስፋም ያመነምናል፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በጸሎተ ቅዳሴዋ “እግዚአብሔር በይቅርታው አንድ ያደርገን ዘንድ ስለ ሰላም እንማልዳለን፤ በዘመኑ ሁሉ ፍጹም ሰላምን እግዚአብሔር ይሰጣት ዘንድ እግዚአብሔርን ስለምትወድ ስለ አገራችን ኢትዮጵያ እንማልዳለን” በማለት ዕለት ዕለት ፈጣሪዋን የምታሳስበው ያለ ምክንያት አይደለም – ሰላም የሁሉ ነገር መሠረት ስለሆነ እንጂ፡፡ እንኳን ሰማያዊ ለሆነው ሃይማኖት ለምድራዊ ኑሮም ቢሆን ዓለም የምትሸልመው ሳይታክቱ ለሰላም የደከሙትን ነው፡፡ Read more