የተወገዙት በዕጩነት እንዳይቀርቡ ቤተ ክርስቲያን የምትቃወምባቸው መሠረታዊ ምክንያቶች

የተወገዙት በዕጩነት እንዳይቀርቡ ቤተ ክርስቲያን የምትቃወምባቸው መሠረታዊ ምክንያቶች

የተወገዙት በዕጩነት እንዳይቀርቡ ቤተ ክርስቲያን የምትቃወምባቸው መሠረታዊ ምክንያቶች

የተወገዙት በዕጩነት እንዳይቀርቡ ቤተ ክርስቲያን የምትቃወምባቸው መሠረታዊ ምክንያቶች

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በግንቦት ፳፻፲፭ ዓ.ም በነበረው የርክበ ካህናት መደበኛ ጉባኤው ዘጠኝ አዲስ ኤጲስ ቆጶሳትን ለመሾም አስመራጭ ኮሚቴ መሠየሙ ይታወቃል። አስመራጭ ኮሚቴውም አዲስ ኤጲስ ቆጶሳት በሚመደብባቸው ዘጠኝ አህጉረ ስብከት ተሿሚዎችን በመምረጥ የመጨረሻዎቹን ፲፰ ዕጩዎችን በመለየት አቅርቦ ዘጠኙ በቅዱስ ሲኖዶስ ተመርጠው ለሹመት በመዘጋጀት ላይ ይገኛሉ። ከእነዚህ ዕጩዎች ውስጥም ሦስቱ ጥር ፲፬ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም በሕገ ወጥ የኤጲስ ቆጶሳት ሢመት የተሳተፉ መሆናቸው ይታወቃል። ነገር ግን በዕጩነት የሚያቀርባቸው ምንም ምክንያት የለም። በዕጩነት ቢቀርቡም ቅዱስ ሲኖዶስ መቀበል አልነበረበትም። ምክንያቱም የፈጸሙት ተግባር በያዙት የክህነት መዓርግ ስንኳ ለመቀጠል የሚያስችላቸው ባለመሆኑ ነው። ከቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ አንጻር ውጉዛኑ በዕጩነት መቅረብ የለባቸውም የምንልባቸው ምክንያቶችም የሚከተሉት ናቸው። Read more

የተማረ ግብረ ገብ ይሾም

የተማረ ግብረ ገብ ይሾም

የተማረ ግብረ ገብ ይሾም

የተማረ ግብረ ገብ ይሾም

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከኤጲስ ቆጶሳት ሢመት ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ እየተነሡ ያሉ ጉዳዮች አሉ። አንደኛውና ዋናው ከእኛ ዘር፣ ጎሣና ቋንቋ ተናጋሪ በኤጲስ ቆጶስነት አልተሾሙም የሚል ሲሆን፣ ሌላው ደግሞ ቅዱስ ሲኖዶስን የአንድ አካባቢ አባቶች የተሰበሰቡበት ነው የሚል ነው። ይህም ቅዱስ ሲኖዶስን በመንፈስ ቅዱስ እንደሚመራ የቤተ ክርስቲያን አካል ሳይሆን የዘር ውክልና ያለበት የፌዴሬሽን ምክር ቤት አድርጎ የመውሰድ የተሳሳተ አረዳድ ወይም ክፉ አሳብ ነው። ብዙ ጊዜ ይህን አሳብ የሚያራምዱት ግን ምእመናን ሳይሆኑ በአቋራጭ ጳጳስ እንሆናለን ብለው የሚያስቡ አካላትና ደጋፊዎቻቸው ናቸው። ጥያቄውም ከመንፈሳዊነት ይልቅ ወደ ፖለቲካዊነት ያጋደለ ነው። Read more

“ንጹሐንን ከርኩሳን ጋር አታጥፋቸው”

“ንጹሐንን ከርኩሳን ጋር አታጥፋቸው”

“ንጹሐንን ከርኩሳን ጋር አታጥፋቸው”

“ንጹሐንን ከርኩሳን ጋር አታጥፋቸው”

ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ በግዞት ካለበት ወደ እስክንድርያ እንደማይመለስ ያረጋገጠው አርዮስ የእስክንድርያ ክርስቲያኖች ሊቀበሉት እንደሚችሉ ተስፋ በማድረግ ወደዚያ ሔዶ ነበር። የአርዮስ ወደ እስክንድርያ መመለስ በቀላሉ ሊበርድ የማይችል ሁከት አስነሣ። የሁከቱ ምክንያትም የእስክንድርያ ክርስቲያኖች መንፈሳዊ አባታቸውን ቅዱስ አትናቴዎስን በስደት ማጣታቸው አንሶ በአርዮስ መመለስ እጅግ መበሳጨታቸው ነበር (አዶንያስ ብርሃነ፣ ገጽ ፪፻፴፭)።

በአርዮስ ወደ እስክንድርያ መመለስ ምክንያት የእስክንድርያ ክርስቲያኖች ተቃውሞ ማስነሣታቸውን የሰማው ንጉሡ ቈስጠንጢኖስ የተቀሰቀሰውን ሁከት ለማርገብ በማሰብና አርዮስ ወደ ቍስጥንጥንያ ቢሄድ አውሳብዮሳውያኑ (የአርዮስ ተከታዮች አርዮሳውያን እንደተባሉት የአውሳብዮስ ዘቂሣርያ ተከታዮች ደግሞ አውሳብዮሳውያን ተብለዋል። እነዚህም መንፈቀ አርዮሳውያን ናቸው) በክብር እንደሚቀበሉት በማመን ወደ ቍስጥንጥንያ እንዲመለስ መልእክት ላከበት። በዘመኑ በቍስጥንጥንያ መንበር ላይ ከሜትሮፌን በመቀጠል ሊቀ ጵጵስና ተሾሞ የነበረው ቅዱስ አሌክሳንደር (ኢትዮጵያውያን ምንጮች እለ እስክድሮስ በማለት ይጠሩታል) የሚባለው አባት በአውሳብዮሳውያኑ አሳብ አልተስማማም ነበር። አውሳብዮሳውያኑ አርዮስን ካልተቀበለው ከመዓርጉ እንደሚሽሩት ቢዝቱበትም ጽኑ ሃይማኖት ስለነበረው ቅዱስ አሌክሳንደር አሳባቸውን ሳይቀበለው ቀረ (አዶንያስ ብርሃነ፣ ገጽ ፪፻፴፭)።

ቅዱስ አሌክሳንደርን አውሳብዮሳውያን ቢያባብሉትም ከዓላማው ፍንክች አልል አለ። ማባበሉ አልሠራላቸው ሲል ለስደት እንደሚዳርጉት አስፈራሩት። ነገር ግን በማስፈራራታቸው አልተርበደበደም። ቅዱስ አሌክሳንደር የቀናችው ሃይማኖት ጠበቃ ነውና በአውሳብዮሳውያን ዛቻና ማስፈራሪያ ሳይሸበር ‘አርዮስን ወደ ቤተ ክርስቲያን ማስገባት ክሕደቱን ማስገባት ነው’ በማለት በአቋሙ ጸና።

በሊቀ ጳጳሱ በአሌክሳንደር በአቋም መጽናት ምክንያት አርዮስ ለሁለተኛ ጊዜ የሚያምንበትን ጽፎ ለንጉሡ እንዲያቀርብ ተደረገ። ንጉሡ ስለሃይማኖቱ በጠየቀው ጊዜ አርዮስ በቅዱስ እለ እስክንድሮስ የተወገዘባቸውን ኑፋቄዎች በመሰወር የቀናቸውን ሃይማኖት እንደሚከተል በማስመሰል እየማለና እየተገዘተ የማምንበት ነው በማለት በጽሑፍ አቀረበ። ቀጥሎም እለ እስክንድሮስ እርሱን ያወገዘባቸውን ኑፋቄዎች ፈጽሞ እንደማይመለስባቸው በመሐላ ባረጋገጠ ጊዜ ንጉሡ ቈስጠንጢኖስ “እምነትህ የቀናች ብትሆን በመማልህ ደግ አደረግህ፤ እምነትህ የረከሰች መሆኑን እያወቅህ ሰውረህ ምለህ ከሆነ ግን እግዚአብሔር እንደ መሐላህ ይፍረድብህ” በማለት አሰናበተው (አዶንያስ ገጽ ፪፻፴፭-፪፻፴፮)።

አውሳብዮሳውያን በተለመደ ተንኮላቸው አርዮስን በግድ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሊያስገቡት ቢሞከሩም ቅዱስ አሌክሳንደር ተቃወማቸው። መልካም ምስክር የሆነው የቍስጥንጥንያው ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ አሌክሳንደር ርእስ መናፍቅ የሆነው አርዮስ ወደ ምእመናን አንድነት ሊመለስ አይገባውም በማለቱም አውሳብዮሳውያኑ በግድ ለማስገባት መዛት ጀመሩ። አንተ ሳትፈቅድ በንጉሡ እንዲጠራ እንዳደረግነው ሁሉ አንተ ወደድክም ጠላህም ነገ በቤተ ክርስቲያን ከእኛ ጋር የምሥጢራት ተካፋይ ይሆናል በማለት ቁርጥ ውሳኔያቸውን አሳውቀውት ሄዱ። አውሳብዮሳውያን በቅዱስ አሌክሳንደር ላይ ዝተውበት የሄዱበት ዕለትም ቅዳሜ ነበር።

ከእግዚአብሔር በቀር ሌላ ረዳት የሌለው መሆኑን የተረዳው ቅዱስ አሌክሳንደር ወደ ቅድስት ሄራኒ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ፣ ከመሠዊያው ሥር በግንባሩ ተደፍቶ በጽኑ ኀዘን ወደ አምላኩ ይጸልይ ጀመር። በዚህ ዕለት ከአጠገቡ ያልተለየው መቃርዮስ የሚባል የእስክንድርያ ካህን ነበር። ሊቀ ጳጳሱ አሌክሳንደር አምላኩን ከተማጸነባቸው ቃላት መካከል ካህኑ መቃርዮስ የሚያስታውሳቸው “አርዮስ ነገ ወደ ምእመናን አንድነት የሚጨመር ከሆነ እኔን ባርያህን አሰናብተኝ” የሚለውና “ንጹሐኑንም ከርኩሳን ጋር አታጥፋቸው። ነገር ግን ቤተ ክርስቲያንህን የምትታደጋት ከሆነ፣ እንደምትታደጋትም አምናለሁ፤ አርዮስንና ኑፋቄውን ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዳይገቡ ከልክላቸው” የሚሉት ይገኙበታል። ይህ የቅዱስ አሌክሳንደር ጸሎት እስራኤልን የምታጠፋቸው ከሆነ እኔን ከሕይወት መጽሐፍህ ደምስሰኝ ያለውን የሊቀ ነቢያት የሙሴን ጸሎት የሚያስታውስ ነው (ዘጸ. ፴፪፣፴፪)።

አርዮስ በቀጣዩ ቀን ማለትም እሑድ ከምእመናንና ከካህናት ጋር አንድ በሚያደርገው ሥጋውና ደሙ እንደሚተባበር አስቦ በዝግጅት ላይ ሳለ ገና በዋዜማው ቅዳሜ ፀሐይ እንኳ ሳትጠልቅ ፈራጁ እግዚአብሔር በክፉዎች ላይ ፍርዱን አሳየ። ታሪክ ጸሐፊው ሩፊኖስ ድርጊቱ የተፈጸመው እሑድ ጠዋት መሆኑን ሲጽፍ ሌሎች ቅዳሜ ወደ ማታ መሆኑን ገልጠዋል። አርዮስ በዚያች ቀን ማለትም ቅዳሜ ወደ ማታ ድንገተኛ ከባድ የሆድ ሕመም ተሰምቶት ወደ አንበሳ መደብ (መጸዳጃ ቤት) ለመሔድ ፈለገ። ሰዎችን እንዲያሳዩት ጠይቆም አሳይተውት በፍጥነት ሮጦ ገባ። አርዮስ አንበሳ መደብ ገብቶ ረዘም ያለ ጊዜ በመቆየቱም ይጠብቁት የነበሩት ሰዎች ወደ ውስጥ ቢገቡ አርዮስ በተቀመጠበት ቦታ የውስጥ አካሉ ተዘርግፎ አገኙት። ብዙ ደም በመፍሰሱና የውስጥ አካሉ በመዘርገፉ ወዲያው ሞተ።

በዕለቱ በአርዮስ ላይ በተፈጸመው ተአምር ምክንያት ንጉሡ አርዮስ በእውነት መናፍቅ እንደ ነበረ ተረድቶ የኒቅያ ጉባኤ አባቶች እምነት ትክክለኛ መሆኑን አረጋገጠ። አርዮስ የሞተበት ቦታም በነሶቅራጥስ ዘመን በቍስጥንጥንያ ሰዎች በአዕማዱ መካከል በእጃቸው እየጠቆሙ የሚያሳዩት በጣም የታወቀ ቦታ ነበር። በዚያ ቦታም ለረጅም ዘመን ሰው አይጠቀምም ነበር። በተፈጥሮ ግዳጅ ምክንያት ወደዚያ የሚገቡ ሰዎችም እርስ በርሳቸው በዚያ መቀመጫ አንጠቀምም ይባባሉ እንደ ነበር ይነገራል። በኋላ ዘመንም የአርዮስን ኑፋቄ የሚደግፍ አንድ ባለጸጋ ሰው ድርጊቱ እንዲረሳና የአርዮስም ክፉ አሟሟት በትውልዱ ሁሉ ሲዘከር እንዳይኖር ቦታውን ገዝቶ ታላቅ ሕንፃ ሠራበት (አዶንያስ፣ ገጽ ፪፻፴፯)።

አውሳብዮሳውያን በመቅሰፍት በተደመደመው የአርዮስ ፍጻሜ በጣም አፈሩ። ቅዱስ አሌክሳንደር ዘቍስጥንጥንያ ደግሞ በዚህ የቤተ ክርስቲያን የደስታ ቀን ከንጹሐን ምእመናን ጋር በጸሎትና በመሥዋዕት እግዚአብሔርን አመሰገነ። የሊቀ ጳጳሱ ደስታ አርዮስ ሞተ ብሎ ሳይሆን ከሕሊና በላይ በሆነው በእግዚአብሔር ርትዕ ፍርድ ነው። ምክንያቱም እግዚአብሔር በቅዱስ አሌክሳንደር ተማጽኖ አርዮሳዊው ክሕደት ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዳይገባ አድርጓልና ነው።

በንጉሡና በአውሳብዮሳውያን ድጋፍ አግኝቶ የነበረውና ቤተ ክርስቲያን ያወገዘችው የአርዮስ ኑፋቄ ርትዕት ከሆነው አስተምህሮ ጋር እንዳይደባለቅ በማድረጉ ቅዱሱ አባት አምላኩን ሲያመሰግን ውሏል። በአርዮስን ድንገት መቀሰፍ ምክንያት ክደው ከቤተ ክርስቲያን ተለይተው ከነበሩ ሰዎች መካከል አንዳንዶች ወደ ርትዕት ሃይማኖት ተመልሰዋል። ቤተ ክርስቲያንን በጎሣና በጎጥ ለመከፋፈል እና በኑፋቄ ለመበከል የሚሞክሩ አካላት ሁሉ መጨረሻቸው እንደ አርዮስ መሆኑን መረዳት ይገባል። ለመንጋውና ለራሳቸው በመጠንቀቅ ቤተ ክርስቲያንን እንዲጠብቁ በመንፈስ ቅዱስ የተሾሙ ጳጰሳት ደግሞ እጅጉን አርአያነት ባለው ሕይወት፣ ፈቃደ እግዚአብሔርብ በማስቀደም መምራት ይገባቸዋል። የተሰጣቸው መንፈሳዊ ኃላፊነት ሸክም እንጂ ማጌጫ አይደለም። ስለሆነም የተሾሙበትን ዓላማ በመዘንጋት ሥጋዊ መሻታቸውን ለማስፈጸም መሥራት አይገባቸውም። ይህን በሚያደርጉ ሁሉ ላይ ሰዎች አቅም አጥተው ዝም ሲሉ እግዚአብሔር ሥራውን እንደሚጀምር ከዚህ ታሪክ መረዳት አዋቂነት ነው።

ዋቢ መጻሕፍት

  1. መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፣ መጽሐፍ ቅዱ የብሉያትና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት፣ ፳፻ ዓ.ም።
  2. አዶንያስ ብርሃነ። ጉባኤያተ ቤተ ክርስቲያን (ከ፶- ፫፻፹ ዓ.ም) ቅጽ ፩። አዲስ አበባ፤ ዘካርያስ ማተሚያ ቤት፣ ፳፻፲፬ ዓ.ም።
በትሕትና የሚሸሹት በፍቅር የሚሸከሙት

በትሕትና የሚሸሹት በፍቅር የሚሸከሙት

በትሕትና የሚሸሹት በፍቅር የሚሸከሙት

በትሕትና የሚሸሹት በፍቅር የሚሸከሙት

የክርስትናን ቀደምት ዘመናት ታሪክ ስናገላብጥ የአበው እና እማት የኑራቸው ፍሬዎች፣ የተጋድሏቸው ምስክሮች የሆኑ ድንቅ ድንቅ ታሪኮች ተመዝግበው እናገኛለን፡፡ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ ብሎ ያዘዛቸውን አምላክ ቃል ሲተገብሩት እናያለን፡፡ ማስተዋል ለቻለ ትእዛዙን ጠብቀው፣ በፍጹም ልባቸው ፈጣሪያቸውን በማመን፣ በትሕትና፣ በመታዘዝ፣ ወንድማቸውን እንደ ራስ በመውደድ ቅድስናን ገንዘብ ሊያድርጓት ያለ መታከት የተጋደሉበት ፍኖት ትልቅ የወንጌል መዓድ ነው፡፡ ቢያነቧቸው ትምህርት የሚሆኑ፣ ቢተገብሯቸው በረከት የሚያሰጡ አስደማሚ የቅዱሳን ገድል ተከትበውባቸዋልና፡፡ ዛሬ አንዱን ቅዱስከድርሳንቀድተን እንዘክራለን፡፡ Read more

ለክፉዎች መድኃኒት የሚሆን የጵጵስና አገልግሎት

ለክፉዎች መድኃኒት የሚሆን የጵጵስና አገልግሎት

ለክፉዎች መድኃኒት የሚሆንየጵጵስና አገልግሎት

ለክፉዎች መድኃኒት የሚሆን የጵጵስና አገልግሎት

በቤተ ክርስቲያን ታሪክ በክፋቱ በሚታወቀው ዲዮቅልጥያኖስ ዘመነ መንግሥት ብፁዕ አባ ጢሞቴዎስ የሚባሉ በሀገረ ግብፅ የእንስና ወይም እንዴናው ሀገረ ስብከት ኤጲስ ቆጶስ ነበሩ። የወንጌል ገበሬ ስለነበሩ በሀገረ ስብከታቸው እየዞሩ ወንጌለ መንግሥትን ለሰው ልጅ ሁሉ ያስተምሩ የነበረው ሳይታክቱ ነበር። የኤጲስ ቆጶሱ ዞረው ወንጌልን ማስተማራቸው የጠቅላይ ግዛቱን ገዥ ዕለት ዕለት ያበሳጨው ነበር። ሀገረ ገዥውም ስለተበሳጨ አስጠርቶ “በክርስቶስ ማመንህንና ወንጌልን ዞረህ ማስተማርህን ተው” በማለት አስጠነቀቃቸው (መጽሐፈ ስንክሳር ኅዳር ፲፫ የሚነበበው)። Read more

ቅዱስ ሲኖዶስ ዘጠኝ ኢጲስ ቆጶሳትን መረጠ

ቅዱስ ሲኖዶስ ዘጠኝ ኢጲስ ቆጶሳትን መረጠ

ቅዱስ ሲኖዶስ ዘጠኝ ኢጲስ ቆጶሳትን መረጠ

ቅዱስ ሲኖዶስ ዘጠኝ ኢጲስ ቆጶሳትን መረጠ

ቅዱስ ሲኖዶስ ዘጠኝ ኢጲስ ቆጶሳትን መረጠ

ቅዱስ ሲኖዶስ ዘጠኝ ኢጲስ ቆጶሳትን መረጠ
—-
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ፤ ዛሬ ረቡዕ፣ ሰኔ 28 ቀን 2015 ዓ.ም. በአካሄደው ልዩ ስብሰባ ዘጠኝ ኢጲስ ቆጶሳትን መርጧል።

ዛሬ የተመረጡት ኢጲስ ቆጶሳት በኦሮሚያ እና በደቡብ ክልሎች፤ ተደርበው በቆዩ፣ ክፍት በሆኑ እና አንገብጋቢ ተብለው በግንቦት 2015 ዓ.ም. በነበረው የርክበ ካህናት መደበኛ ጉባኤ ስብሰባ ላይ በተለዩትና ሰባት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ያሉበት አስመራጭ ኮሚቴ በተሰየመላቸው መሠረት ነው።

ኢጲስ ቆጶሳቱ የተመረጡላቸው ሀግረ ስብከቶች ሰባቱ በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ሲሆን ሁለቱ በደቡብ ኢትዮጵያ የሚገኙ ናቸው። ከይፋዊው የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ላይ ባገኘነው መረጃ መሠረት ዝርዝራቸ፦

ለኦሮሚያ ክልል ሰባት አህጉረ ስብከት፤
1. አባ ሣህለ ማርያም ቶላ – ምዕራብ አርሲ – ሻሸመኔ ሀገረ ስብከት
2. አባ ወልደ ገብርኤል አበበ – ምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት
3. አባ ጥላሁን ወርቁ – ምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት
4. አባ ዓምደ ሚካኤል ኀይሌ – ሆሮ ጉድሩ ወለጋ – ሻምቡ ሀገረ ስብከት
5. አባ ኀይለ ማርያም ጌታቸው – ድሬዳዋ ሀገረ ስብከት
6. አባ ተክለ ሃይማኖት ገብሬ – ምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት
7. አባ እስጢፋኖስ ገብሬ – ቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት

ለደቡብ ኢትዮጵያ ሁለት አህጉረ ስብከት፤
8. አባ ክፍለ ገብርኤል ተክለ ሐዋርያት – ጌድኦ አማሮ እና ቡርጂ ልዩ ወረዳዎች ሀገረ ስብከት
9. አባ ስብሐት ለአብ ወልደ ማርያም – ዳውሮ እና ኮንታ ሀገረ ስብከት ናቸው።

የመንግሥት ጣልቃገብነት ከሕገ ወጡ ቡድን ድጋፍ እስከ ጳጳሳት ምርጫ

የመንግሥት ጣልቃገብነት ከሕገ ወጡ ቡድን ድጋፍ እስከ ጳጳሳት ምርጫ

የመንግሥት ጣልቃገብነት ከሕገ ወጡ ቡድን ድጋፍ እስከ ጳጳሳት ምርጫ

የመንግሥት ጣልቃገብነት ከሕገ ወጡ ቡድን ድጋፍ እስከ ጳጳሳት ምርጫ

የሃይማኖትና የመንግሥት ግንኙነትን በተመለከተ አገራት የየራሳቸውን ሥርዓት ይከተላሉ። መንግሥት ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮም በተለያዩ ዘመናት ሃይማኖትና መንግሥት የተለያዩ የግንኙነት መርሖችን አልፈዋል። ሃይማኖት ከመንግሥት በላይ የሆነበት ጊዜ የነበረውን ያህል መንግሥትም ከሃይማኖት በላይ ተደርጎ የተወሰደበት ዘመን እንደነበር የዘርፉ ምሁራን ይገልጻሉ። ባለንበት ዘመን አብዛኛዎቹ አገራት የሚመሩት መንግሥትና ሃይማኖት የተለያዩ ናቸው በሚለው መርሕ ነው። ይህም ሆኖ ዓለማዊ መንግሥት ኖሯቸው፣ አንድን ሃይማኖት ብሔራዊ ሃይማኖት አድርገው ያወጁ አገራት አሉ። እንግሊዝ እና ግብጽ ለዚህ ተጠቃሽ ምሳሌዎች ናቸው።[1] ወደ አገራችን ኢትዮጵያ ስንመጣ እስከ ፲፱፻፷፮ ዓ.ም ድረስ ኦርቶዶክስ ክርስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ ቆይቷል። በተለይም በ፲፱፻፹፯ ዓ.ም የወጣው የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት ስለ ሃይማኖትና መንግሥት መለያየት ግልጽ ድንጋጌ አስቀምጧል። የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ፲፩ መንግሥትና ሃይማኖት የተለያዩ እንደሆኑ፣ መንግሥታዊ ሃይማኖት እንደማይኖርና መንግሥት በሃይማኖት ጉዳዮች፣ ሃይማኖትም በመንግሥት ጉዳዮች ጣልቃ እንደማይገቡ ይደነግጋል። ሆኖም ግን መንግሥት ላወጣው ሕግ ተገዥ ባለመሆን በሃይማኖታዊ ጉዳዮች ጣልቃ ሲገባ ይስተዋላል። Read more

የኤጲስ ቆጶሳት አስመራጭ ኮሚቴ ያከናወናቸው ተግባራትና ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገባቸው ጉዳዮች

የኤጲስ ቆጶሳት አስመራጭ ኮሚቴ ያከናወናቸው ተግባራትና ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገባቸው ጉዳዮች

የኤጲስ ቆጶሳት አስመራጭ ኮሚቴ ያከናወናቸው ተግባራትና ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገባቸው ጉዳዮች

የኤጲስ ቆጶሳት አስመራጭ ኮሚቴ ያከናወናቸው ተግባራትና ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገባቸው ጉዳዮች

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በግንቦት ፳፻፲፭ ዓ.ም በነበረው የርክበ ካህናት መደበኛ ጉባኤው ዘጠኝ አዲስ ኤጲስ ቆጶሳትን ለመሾም ሰባት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ያሉበት አስመራጭ ኮሚቴ መሠየሙ ይታወቃል። አዲስ ኤጲስ ቆጶሳት የሚመደብባቸው ዘጠኙ አህጉረ ስብከትም ምዕራብ ወለጋ፣ ምሥራቅ ወለጋ፣ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ፣ ምዕራብ አርሲ (ሻሸመኔ)፣ ድሬ ዳዋ፣ ምሥራቅ ሐረርጌ፣ ቡኖ በደሌ፣ ጌዴኦ፣ ቡርጂና አማሮ እንዲሁም ዳውሮ ኮንታ አህጉረ ስብከት ናቸው። የአስመራጭ ኮሚቴው አባላት ደግሞ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ፣ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ፣ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ፣ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ፣ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል፣ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስና ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል ሲሆኑ አስመራጭ ኮሚቴው ግንቦት ፳፫ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ሥራውን በይፋ የጀመረ መሆኑን የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሕዝብ ግንኙነት አገልግሎት አሳውቋል። Read more

ተሿሚዎችን ለምእመናን አለማሳወቅ የሚያስከትለው መዘዝ

ተሿሚዎችን ለምእመናን አለማሳወቅ የሚያስከትለው መዘዝ

ተሿሚዎችን ለምእመናን አለማሳወቅ የሚያስከትለው መዘዝ

ተሿሚዎችን ለምእመናን አለማሳወቅ የሚያስከትለው መዘዝ

በዘመናችን ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን ውጭ የሚፈጸሙ ጉዳዮች በርክተዋል። አባቶች የሠሩትን ቀኖና እያፈረሱ የቤተ ክርስቲያንን ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ አስጠብቃለሁ ብሎ መናገር አይቻልም። ከእግዚአብሔር ይልቅ ቄሳርን ለማስደሰት የሚደረገው ሙከራ በእግዚአብሔር የሚያስጠይቅ በታሪክም የሚያስወቅስ ነው። ቤተ ክርስቲያን ጉባኤ ከለባት ብላ በምትጠራው የኬልቄዶን ጉባኤ እነ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ንጉሥ ለማስደሰት ብለው እንደ ሌሎቹ መለካውያን ቢሆኑ ኖሮ ርትዕት የሆነችው ሃይማኖት ከዘመናችን ባልደረሰች ነበር። Read more

ፍኖተ-ጎርጎርዮስ

ፍኖተ-ጎርጎርዮስ

ሕዝበ ክርስቲያኑ የቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙን ትምህርቱን ሰምተው ግብሩን ዐይተው ሲወዱት ኖረዋል፡፡ ወላጆቹን በተለይ በእርግና ዘመን ላይ የነበረ አባቱን ጠይቆ ለመመለስ ወደ ወላጆቹ በሔደበት አጋጣሚ በሕዝቡ ግፊት ሥልጣነ ክህነት እንዲቀበል ተደረገ፡፡ እርሱ ግን ገዳማዊ ሕይወትን እጅግ ወድዶ ነበርና በብሕትውና ወደሚኖርበት ገዳም ሔዶ ተደበቀ፡፡ የቃልም የሕይወትም መምህር ነበር፤ በአንዲት በዓት ረጅም ጊዜ በጾም በጸሎት በመወሰን የሚታወቅ ገዳማዊ አባት፡፡ በትምህርትም ዓለማዊውን ትምህርት ከቂሣሪያ እስከ አቴና በመጓዝ በግሪክ ፍልስፍና የተራቀቀ፣ በመንፈሳዊው ትምህርትም ከሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ በኋላ ነባቤ መለኮት (ታኦሎጎስ) እስከ መባል የደረሰ የነገረ መለኮት ሊቅ ነበር፡፡