ከአዲስ ተሿሚዎች የሚጠበቅ ተግባርና ኃላፊነት
ከአዲስ ተሿሚዎች የሚጠበቅ ተግባርና ኃላፊነት

ሥርዓተ ሲመተ ኤጲስ ቆጶሳት መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ሐምሌ 09 2015 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለመጀመሪያ ጊዜ የራሷ ልጆች ኤጲስ ቆጶስነት እንዲሾሙላት ባደረገች ጊዜ የተፈጸመውን መንፈሳዊ ተግባር በዘመኑ ታትሞ የወጣው ብርሃንና ሰላም ጋዜጣ የዘገበው “አመራረጡ ግን በዕጣ እንዲሆን ምክር ተቈርጦ ስለነበር በዕጣው ላይ ሰባት ቀን ሙሉ በቤተ ክርስቲያን ጸሎት እየተጸለየበት እና ቅዳሴ እየተቀደሰበት ቆይቶ ለአምስቱ መምህራን ዕጣ ወጣላቸው። ስማቸውም መምህር ደስታ፣ መምህር ኃይለ ማርያም፣ መምህር ወልደ ኪዳን፣ መምህር ኃይለ ሚካኤል ናቸው። አምስተኛው ግን ወደ ግብፅ አልወረዱም” በማለት ነበር (ብርሃንና ሰላም ሰኔ 6 ቀን 1921 ዓ.ም፣ ገጽ 189)። Read more