የአንደኛ ክፍል ፈተና ተሰጠ
በባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የተሰጠው የአንደኛ ክፍል የአጋማሽ ዓመት ፈተና እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን የሀገረ ስብከቱ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት አስታወቀ። ፈተናው እሑድ ፣ ታኅሣሥ 10 ቀን፣ 2014 ዓ/ም የተሰጠ ሲሆን፤ በሀገረ ስብከቱ በሚገኙ እና የአዲሱን ሥርዓተ ትምህርት ትግበራ ባስጀመሩ ሃያ ሰባት ሰንበት ት/ቤቶች የሚገኙ አንድ ሺህ ሁለት መቶ አርባ ሰባት (1,247) ህጻናት ፈተናውን ወስደዋል።
ከነዚህም ሰንበት ት/ቤቶች መካከል ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተማሪ በማስፈተን ቅድሚያውን የወሰዱ ሰንበት ት/ቤቶች የሚከተሉት ናቸው፦
- ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ሰ/ት/ቤት አንድ መቶ ሃያ አራት (124) ህጻናት በማስፈተን፣
- መንበረ ስብሐት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሰ/ት/ቤት አንድ መቶ አምስት (105) ህጻናት በማስፈተን፣
- የጽርሐ አርያም ደብረ ሲና በዓታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ሰ/ት/ቤት ስድሳ ዘጠኝ (69) ህጻናትን በማስፈተን፣
ከዚሁ ጋር በማከልም በመጀመሪያው መንፈቀ ዓመት የትምህርት ክፍለ ጊዜ የሚሰጡት የትምህርት ዓይነቶች መሠረተ ሃይማኖት ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እና የልሳነ ግእዝ መሆናቸውን የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት አስታውቋል።