የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት - በኢ/ኦ/ተ/ቤ የመንበረ ፓትርያርክ ሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ አንድነቱ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ተቋማዊ ራእይ፣ ተልእኮ
      • መዋቅራዊ አደረጃጀት
      • የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ተቋማዊ አደረጃጀት
      • የሰንበት ት/ቤቶች የሥራ አመራር ምርጫ ማስፈጸሚያ
    • ስልታዊ እቅድ 2018 – 2021 ዓ/ም
  • ሥርዓተ ትምህርት
    • መሠረታዊ መረጃዎች
    • የሰንበት ት/ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት አደረጃጀት መመሪያ
    • የሥርዓተ ትምህርቱ መመማሪያ መጻሕፍት ይዘት
      • የአንደኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
      • የኹለተኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
      • የሦስተኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
    • የሥርዓተ ትምህርቱ ዓመታዊ የጊዜ ሰሌዳ /ካሌንደር
    • የመምህራን ሥልጠና እና መልእክቶች
    • መጻሕፍቱን ለማግኘት እና ተጨማሪ መረጃ
    • ልዩ ልዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች
  • ፕሮጀክቶች
  • መዝሙረ ማኅሌት
    • የመስከረም ወር መዝሙሮች
      • የዮሐንስ መዝሙር
      • የመስቀል መዝሙሮች
      • የብዙኃን ማርያም መዝሙር (መስከረም ፳፩ )
      • የዘመነ ጽጌ መዝሙር
    • የጥቅምት ወር መዝሙሮች
      • የአብርሃ ወአጽብሐ መዝሙር (ጥቅምት 4 ቀን)
    • የኅዳር ወር መዝሙሮች
      • የቅዱስ ሚካኤል መዝሙር (ኅዳር 12 ቀን)
    • የጥር ወር መዝሙሮች
      • የዘመነ ጥምቀት መዝሙር
      • የቃና ዘገሊላ መዝሙር (ጥር 12 ቀን)
    • የመጋቢት ወር መዝሙሮች
      • የወርኃ ጾም መዝሙሮች
      • የሆሣዕና መዝሙራት
      • የሰሙነ ሕማማት መዝሙሮች
  • ዜና
    • አጫጭር ዜናዎች
    • ዝርዝር ዜናዎች
    • ወቅታዊ መረጃዎች
    • ማስታወቂያ
      • የሰንበት ትምህርት ቤቶች መጻሕፍት እንግሊዝኛ ትርጉም ሥራ ተሳትፎ ጥሪ
  • ያግኙን
  • ቋንቋ
    • ትግርኛ
    • Afaanoromo
  • Menu Menu

ቤተ ክርስቲያን የአንድ አካል ብቻ አይደለችም፤ የካህናት፣የምእመናን እና የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት ጭምር እንጂ!

ከሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የተላለፈ ወቅታዊ መልእክት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ዋና ተግባሩ የሆነውን ሐዋርያዊ ተልእኮ በትጋት እና በስፋት ከማስፈጸም ይቅል በሥጋ ሐሳብ ተቀፍድዶ ጥንታዊቷን እና አማናዊቷን ቤተ ክርስቲያን በማይመጥን ደረጃ ላይ መገኘቱን የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ተገንዝቧል። በተለይ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን፣ አደረጃጀቱን ለማዘመን እና የሥራ አፈጻጸም ስልትን ከዘመኑ ጋር ለማጣጣም እንዲያስችል በተለየዩ ጊዜያት በባለሙያዎች ተጠንተው የተዘጋጁ መፍትሔ አመላካች ሰነዶች ልዩ ልዩ ምክንያት እየተለጠፈባቸው ተገፍተው መወገዳቸውን ታዝበናል። ስለሆነም አስተዳደራዊ ክፍተቱ በከፍተኛ ደረጃ የወለደው ችግር የአደባባይ ምሥጢር ሆኖ ተገልጧል::
ከቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ድክመት ጋር ተያይዞ እየተስተዋሉ ያሉ ዘርፈ ብዙ የውስጥ ችግሮች እና የሥነ ምግባር ጥሰቶች መንፈሳዊ አገልግሎቱን ያቀጨጩ፣ በመንፈሳዊነት ዐውድ አንገታችን ያስደፉ፣ በሌሎች ዘንድ ለስላቅ መንገድ የከፈቱ፣ ለትችት የዳረጉን የትውልዱ ስብራቶች እንደ ሆኑ ተገንዝበናል  ::

ቤተ ክርስቲያን ጥንተ ሥርዓቷን አስጠብቃ ዘመኑን የዋጀ መዋቅራዊ አደረጃጀት፣ ብቃት ያለው አስተዳደር እና ሐዋርያዊ አገልግሎቷን የምትመራበት መሪ ዕቅድ ትግበራ እውን እንዲሆን በተደጋገሚ ስንጠይቅ ይሁንታ ባገኘ ጊዜም በዝግጅቱ በመሳተፍ በርካታ ዓመታትን በተስፋ አሳልፈናል:: በያዝነው ዓመትም በቅዱስ ሲኖዶስ ይሁንታ በተሰጠው ዘላቂ መፍትሔ ቋሚ ኮሜቴ ውስጥ በመሳተፍ የሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት ቅድመ ምልመላ መሥፈርት፣ የሀገረ ስብከት አደራጃጀት እና ምደባን አስመልክቶ አስፈላጊና ጠቃሚ የጥናት ሰነዶች እንዲዘጋጅ ተራድተናል። በዚህም ተገቢ ሰነድ ተዘጋጅቶ ቀርቧል።
የሁሉም የሆነችው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በተለይ በዚህ አስጨናቂ ወቅት አባቶች የልጆችን ድምፅ በመስማት፣ እርስ በእርስ በመደማመጥና በመናበብ፣ አቃፊ በመሆን፣ በጥበብ መጓዝ ያስፈልጋል ብለን የምናምን ሲሆን እኔ ብቻ አውቅልሀለሁ ብሎ የልጆችን ቀና የአስተዳደር ለውጥ ሐሳብ መግፋትና ከተሳትፎ ማግለል ከባድ ዋጋ እንደሚያስከፍል መረዳትም ያስፈልጋል ብለን እናምናለን:: ቤተ ክርስቲያን በሁሉ ልብ ውስጥ ያለች ናት። በመሆኑም የጥቂት ጳጳሳት ብቻ ሳትሆን የካህናት፣ የምእመናን እና የሰንበት ትምህርት ቤት ድርሻ ተሰናስሎ የሚገለጥባት መንፈሳዊ ተቋም ናት::
በሕገ ቤተ ክርስቲያን እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አንድነትና አስተዳደር ለማጠናከር በወጣው የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ደንብ (ቃለ ዓዋዲ) መሠረት የቤተ ክርስቲያኗ አስተዳደር መመራት ያለበት ከጠቅላይ ቤተ ክህነት እስከ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ድረስ ከካህናት፣ ከምእመናን እና ከሰንበት ት/ቤት ወጣቶች በተውጣጡ መዋቅሮች ነው፡፡ በዚህም አግባብ ይህን ታሳቢ ያደረገ አሳታፊ አሠራርን ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን እንገለጻለን።
ሀገራዊ ሰላም ለማስፈን በሚደረገው ጥረት ቤተ ክርስቲያን የሚኖራት ሱታፌ በትክክል ሊሠራበት ይገባል። ከዚህ በፊት እንደሚደረገው ወሳኝ አስተዋጽኦ ማድረግ በማያስችል ሁኔታ ከአንድ አካል ብቻ ኮሚቴ አቋቁሞ ለዜና ግብአት ከመሆን  ባለፈ እውነተኛ ተሳትፎ እንዲኖረን አግባብነት ያላቸውን ሊቃውንት፣ ምሁራን፣ ሰንበት ትምህርት ቤቶች እና ማኅበራትን በማሳተፍ ወደ ሥራ እንዲገባ እንጠይቃለን፡፡
– በቅዱስ ሲኖዶስ ይሁንታ በተሰጠው ዘላቂ መፍትሔ ጠቋሚ ኮሜቴ የሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት ቅድመ ምልመላ መሥፈርትን፣ የሀገረ ስብከት አደራጃጀትን እና ምደባን አስመልክቶ ካህናት፤ ምእመናን እና ሰንበት ትምህርት ቤቶች የተሳተፉበት ጠቃሚ ሰነድ ተዘጋጅቶ ለቅዱስ ሲኖዶስ ቀርቧል። ይሁንና ለምልዐተ ጉባኤው ገንቢ ግብዓት እንዳይሆን አለመቅረቡ የቀደመ ለውጥ ጠል በሽታ ማሳያ ነው። ቅዱስ ሲኖዶስ ይህንን ዘመኑን ያልዋጀና የሰነበተ ደዌ በመንፈስ ቅዱስ አጋዥነት ቆርጦ እንዲጥል እና የተዘጋጀው ጥናት እና አቅጣጫ ጠቋሚ የመፍትሔ ሐሳብ በመሆኑ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቀኖና፣ ክብር እና አንድነት ቅድሚያ በመስጠት እንዲጠቀምበት፣ ግልፅና መርኀን የተከተለ የምልመላ፣ የምርጫ እና የምደባ ሥርዓት ለመከተል የሚያስችለው የጥናት ሰነድ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አርፎበት ተግባራዊ እንዲሆን በልጅነት መንፈስ እንጠይቃለን።
*በተደራቢነት የተያዙ አኅጉረ ስብከቶች እና በቁጥራቸው ብዙ የሆኑ አድባራትና ገዳማት ያሉባቸው አኅጉረ ስብከቶችን ተገቢ እና ውጤታማ አገልግሎት መስጠት በሚያስችል መልኩ ተጨማሪ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት በቀረበው መሥፈርት መሠረት በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ እና ሕግ መሠረት እንዲከናወን እናሳስባለን፡፡
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ በውጪያዊ እና በውስጣዊ ግፊት፣ ከሲሞናዊነት እኩይ ተግባር፣ ለውጥ ጠልና ጎታች በሆኑ አመለካከቶች እንዳይያዝ በመጠንቀቅ ቤተ ክርስቲያንን የመጠበቅ መንፈሳዊ ግዴታውን እንዲወጣ እንጠይቃለን። እንዲሁም ጥር ፲፰ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም. በግልጽ ደብዳቤ ለቅዱስ ሲኖዶስ ያቀረብነውን የመፍትሔ ሐሳብ በአግባቡ በመመልከት በግብዓትነት እንድትጠቀሙበት በፍጹም ትሕትና እና በልጅነት መንፈስ እንጠይቃለን።

የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት

ግንቦት ፭፣ ቀን ፳፻፲፭ ዓ/ም

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on LinkedIn
  • Share on Telegram
  • Share by Mail
https://eotc-gssu.org/a/wp-content/uploads/logo-300.png 300 300 gssu https://eotc-gssu.org/a/wp-content/uploads/logo-2-1-300x74-1.png gssu2023-05-13 15:40:042023-05-13 21:13:06ቤተ ክርስቲያን የአንድ አካል ብቻ አይደለችም፤ የካህናት፣የምእመናን እና የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት ጭምር እንጂ!
Search Search

Recent Posts

  • የሦስተኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
  • የኹለተኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
  • የአንደኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
  • የመስቀል ደመራ በዓል በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ
  • ሦስተኛ ዙር የ፲፪ ክፍል ምርቃት መርሐ ግብር ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ በተገኙበት ተከናወነ።

Archives

  • April 2026
  • September 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • May 2025
  • April 2025
  • October 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • November 2022
  • October 2022
  • September 2022
  • July 2022
  • June 2022
  • April 2022
  • February 2022
  • January 2022
  • October 2021
  • September 2021
© Ethiopian Orthodox Church Global Sunday School Union | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
  • Link to Youtube
  • Link to Telegram
  • Link to TikTok
Link to: ከቅዱስ ሲኖዶስ ለ ፫ ቀናት የታወጀውን የነነዌ ፆም እና ምሕላ መጠናቀቅን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ Link to: ከቅዱስ ሲኖዶስ ለ ፫ ቀናት የታወጀውን የነነዌ ፆም እና ምሕላ መጠናቀቅን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ ከቅዱስ ሲኖዶስ ለ ፫ ቀናት የታወጀውን የነነዌ... Link to: የቅዱስ ፓትርያርኩ የግንቦት ፳፻፲፭ ዓ.ም ርክበ ካህናት ጉባኤ መክፈቻ ንግግር Link to: የቅዱስ ፓትርያርኩ የግንቦት ፳፻፲፭ ዓ.ም ርክበ ካህናት ጉባኤ መክፈቻ ንግግር የቅዱስ ፓትርያርኩ የግንቦት ፳፻፲፭ ዓ.ም ርክበ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top