የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት - በኢ/ኦ/ተ/ቤ የመንበረ ፓትርያርክ ሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ አንድነቱ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ተቋማዊ ራእይ፣ ተልእኮ
      • መዋቅራዊ አደረጃጀት
      • የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ተቋማዊ አደረጃጀት
      • የሰንበት ት/ቤቶች የሥራ አመራር ምርጫ ማስፈጸሚያ
    • ስልታዊ እቅድ 2018 – 2021 ዓ/ም
  • ሥርዓተ ትምህርት
    • መሠረታዊ መረጃዎች
    • የሰንበት ት/ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት አደረጃጀት መመሪያ
    • የሥርዓተ ትምህርቱ መመማሪያ መጻሕፍት ይዘት
      • የአንደኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
      • የኹለተኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
      • የሦስተኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
    • የሥርዓተ ትምህርቱ ዓመታዊ የጊዜ ሰሌዳ /ካሌንደር
    • የመምህራን ሥልጠና እና መልእክቶች
    • መጻሕፍቱን ለማግኘት እና ተጨማሪ መረጃ
    • ልዩ ልዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች
  • ፕሮጀክቶች
  • መዝሙረ ማኅሌት
    • የመስከረም ወር መዝሙሮች
      • የዮሐንስ መዝሙር
      • የመስቀል መዝሙሮች
      • የብዙኃን ማርያም መዝሙር (መስከረም ፳፩ )
      • የዘመነ ጽጌ መዝሙር
    • የጥቅምት ወር መዝሙሮች
      • የአብርሃ ወአጽብሐ መዝሙር (ጥቅምት 4 ቀን)
    • የኅዳር ወር መዝሙሮች
      • የቅዱስ ሚካኤል መዝሙር (ኅዳር 12 ቀን)
    • የጥር ወር መዝሙሮች
      • የዘመነ ጥምቀት መዝሙር
      • የቃና ዘገሊላ መዝሙር (ጥር 12 ቀን)
    • የመጋቢት ወር መዝሙሮች
      • የወርኃ ጾም መዝሙሮች
      • የሆሣዕና መዝሙራት
      • የሰሙነ ሕማማት መዝሙሮች
  • ዜና
    • አጫጭር ዜናዎች
    • ዝርዝር ዜናዎች
    • ወቅታዊ መረጃዎች
    • ማስታወቂያ
      • የሰንበት ትምህርት ቤቶች መጻሕፍት እንግሊዝኛ ትርጉም ሥራ ተሳትፎ ጥሪ
  • ያግኙን
  • ቋንቋ
    • ትግርኛ
    • Afaanoromo
  • Menu Menu

ኢ-ቀኖናዊ የሆነውን “ሲመተ ኤጲስ ቆጶሳት” አስመልክቶ ከሀገር አቀፍ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የተሰጠ መግለጫ

ቀኖናዊ ሥርዓቷን ጠብቃና አስጠብቃ አያሌ ዘመናትን የተሻገረቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን  በተለይ ከጥቂት ዓመታት ወዲህ እየደረሰባት ካለው ፈተና፣ መሰናክል፣  መከራ እና ውጣ ውረድ  በእግዚአብሔር ቸርነት ተጠብቃ አሁን ካለንበት ዘመን ደርሳለች ::  ዛሬ ግን ከፈተናዎች ሁሉ የከፋው ፈተና የበጐች እረኛ አድርጋ ሾማ እስከ ማዕረገ ጵጵስና ባከበረቻቸው ልጆቿ  ተፈጽሞባታል።  መንጋውን እንዲጠብቁ የመረጠቻቸው ልጆቿ ሊያፈርሷትና ሊከፍሏት  መነሳታቸው  በእጅጉ አሳዝኖናል ::ይኸንን ኢ -ቀኖናዊ  ተግባርም በጽኑ እንቃወማለን። በመሆኑም ፦

  1. ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን ውጪ በሕገወጥ መልኩ ኤጲስ ቆጶሳትን ለመሾም እና ሲኖዶስን ለመክፈል የተደረገውን ሕገ ወጥ እንቅስቃሴ አጥብቀን እንቃወማለን :: ድርጊቱ ታላቋን ፣ ጥንታዊቷን፣ ታሪካዊቷን ፤ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ለማዳከም የተሸረበ ሴራ መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው። በመሆኑም  ከሙሉ ክብሯ፣ ሥርዓቷ እና እሴቶቿ ጋር  የምንወርሳትን ቤተ ክርስቲያን በእኛ ዘመን ለመክፈል የተነሱ  የውስጥ እና የውጪ ጠላቶቿን በፍፁም አንታገሰም ::
  2. ቅዱስ ሲኖዶስ በድፍረትና በማን አለብኝነት የተፈፀመውን ኢ- ቀኖናዊ ሲመተ ኤጲስ ቆጶሳትን አስመልክቶ ሕጋዊ እና የታላቋን ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ክብር እና መብት የሚያስከብር  እርምጃ እንዲወስድ እንጠይቃለን።
  3. ቅዱስ ሲኖዶስ ኢ- ቀኖናዊ ለሆነው የመንደር ኤጲስ ቆጶሳት ሲመት መነሻ የሆነውን ምክንያት በማጥናትና በመለየት ተገቢውንና  አስፈላጊውን ሁሉ በማድረግ መንፈሳዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ እንጠይቃለን :: ከዚሁ ጋር ተያይዞ በዋነኝነት የብዙ ችግሮች  ምክንያት መሆኑ በጉልህ የሚስተዋለው አስተዳደራዊ ክፍተት   ዘላቂና  አስተማማኝ ተግባራዊ መፍትሔ  እንዲሰጠው አበክረን እንጠይቃለን።
  4. ለዚህ ችግር መፍትሔ ለመስጠት የተለመደውን አካሄድ መከተል ነገሩን ከማዳፈን የዘለለ እልባት ስለማያስገኝ ዘግይቶ ለሚፈጠረው ችግር አባቶች ቀዳሚ ተጠያቂ እንደምትሆኑ በልጅነት አንደበት እየገለጥን   የአስተዳዳር አካላት ፣ምዕመናን ና ምዕመናት የጀመራችሁትን ቤተ ክርስቲያንን የመጠበቅ ኃላፊነት እያደነቅን ፤ አሁንም በበለጠ በጋራ ሆነን ክርስቲያናዊ ኃላፊነታችንን እንድንወጣ ጥብቅ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
  5. መንግስትም ሀገረ መንግስቱን በኃይል ለመናድ የሚንቀሳቀስ ኃይል ቢኖር  ሕግ የማስከበር እርምጃ እንደሚወስድ ሁሉ ሕጋዊ ሰውነት ላላት ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ሕግ በማስከበር ሥራው ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ፤በግልጥ እና በስውር የሚደርሰው ጥቃት እና ትንኮሳ የማያባራ የእርስ በእርስ ችግር የሚያስከትልና ሰላምና መረጋጋትን በሀገራቸን የሚያሳጣ በመሆኑ  ከቅዱስ ሲኖዶስ ጎን በመሆን ፤አፍራሽ እና እኩይ ዓላማ ያነገቡ የበግ ለምድ ለባሽ  ኃይሎች ላይ በቁርጠኝነት ሕጋዊ እርምጃ በመውስድ  ኃላፊነቱን እንዲወጣ በጥብቅ እንጠይቃለን ::

በመጨረሻም ወቅታዊ የአስተዳደር ክፍተቶች ፣ ግለሰባዊ ፍላጎቶችን እና ልዩነቶችን  ወደ ጎን በመተው  ሁሉም ኦርቶዶክሳዊ  በቤተ ክርስቲያናችን ችግር መፍትሔ  ላይ በማተኮር  እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ በኅብረት እንዲቆም እንጠይቃለን።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on LinkedIn
  • Share on Telegram
  • Share by Mail
https://eotc-gssu.org/a/wp-content/uploads/abune-matias-1.png 430 430 gssu https://eotc-gssu.org/a/wp-content/uploads/logo-2-1-300x74-1.png gssu2023-01-24 08:13:522023-05-13 17:41:57ኢ-ቀኖናዊ የሆነውን “ሲመተ ኤጲስ ቆጶሳት” አስመልክቶ ከሀገር አቀፍ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የተሰጠ መግለጫ
Search Search

Recent Posts

  • የሦስተኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
  • የኹለተኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
  • የአንደኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
  • የመስቀል ደመራ በዓል በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ
  • ሦስተኛ ዙር የ፲፪ ክፍል ምርቃት መርሐ ግብር ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ በተገኙበት ተከናወነ።

Archives

  • April 2026
  • September 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • May 2025
  • April 2025
  • October 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • November 2022
  • October 2022
  • September 2022
  • July 2022
  • June 2022
  • April 2022
  • February 2022
  • January 2022
  • October 2021
  • September 2021
© Ethiopian Orthodox Church Global Sunday School Union | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
  • Link to Youtube
  • Link to Telegram
  • Link to TikTok
Link to: የቃና ዘገሊላ መዝሙር (ጥር 12 ቀን) Link to: የቃና ዘገሊላ መዝሙር (ጥር 12 ቀን) የቃና ዘገሊላ መዝሙር (ጥር 12 ቀን) Link to: ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ Link to: ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top