ከደቂቀ እስጢፋኖስ እስከ መንበረ ሰላማ

ከደቂቀ እስጢፋኖስ እስከ መንበረ ሰላማ
አባ እስጢፋኖስን እና ተከታዮቹንበተመለከተ ብዙ ይጻፋል፣ ይነገራል። የእርሱ እና የተከታዮቹ ጉዳይ ማንም እንደፈለገ ለመዘወር የተመቸ ነው። ከትግራይ ክልል የተነሡ ተስፈንጣሪ ፖለቲከኞች ባላንጣችን የሚሉትን ሸዋን ለመተቸት ይጠቅሱታል። በክልሉ ኑፋቄያቸውን ለመዝራት ፈልገው ያልተሳካላቸው ተሐድሶ መናፍቃን በዕውቀቱ አቻ የሌለው፣ በአስተምህሮው እንከን የማይገኝበት አስመስለው ያቀርቡታል። ቤተ ክርስቲያኗን በዘር ለመከፋፈል የሚደክሙ አካላት አርአያነቱን እንከተል በማለት የፈጣራ ድርሰት ጽፈው ያነቡለታል። እንደ አባ እስጢፋኖስ ያለ ምግባረ ብልሹ ራሱን ኮፍሶ ሌላውን ስለሚያናንቅ እንዲህ ያለው ምግባር የመናፍቃንመለያ መሆኑን መረዳት ከተደጋጋሚ ጥፋት ይታደጋል። Read more