ከወርቃማው ሕግ አትንሸራተቱ (የነገረ ሰብእ ትምህርት ጉድለት የወለደው አገራዊ ቀውስ ክፍል ሁለት)
የተከበራችሁ የማኅበራዊ ሚዲያችን ተከታታዮች አስቀድምን ባስነበብነው የዚህ ጽሑፍ የመጀመሪያ ክፍል ሰው በእግዚአብሔር አርአያ እና ምሳሌ የተፈጠረ የፍጥረታት ንጉሥ፣ ከሌሎች ፍጥረታት ተለይቶ ዐዋቂ እና ሕያውነት ያለው፣ በፍጥረታት ላይ የሠለጠነ ባለጸጋ ፍጡር መሆኑን አቅርበን ነበር። በዚህም ምክንያት ሰው ነጻ ፈቃዱን ተጠቅሞ ሲጠፋ ከሦስቱ አካላት አንዱ ወልድ “እስመ በፈቃዱ፣ ወበሥምረተ አቡሁ ወመንፈስ ቅዱስ መጽዐ አድኀነነ” እንደ ተባለው ሰው ሆኖ ሰውን ከውድቀት አነሣው። ዘጠና ዘጠኙን ነገደ መላእክት ትቶ አንዱን ነገድ ሰውን ለመፈለግ ሰው የሆነው ለሰው ካለው ጽኑ ፍቅር የተነሣ ነው። Read more