ጦርነቱን ወደ ሰላም በማሸጋገር ምድሪቱንም፣ ትውልዱንም ማሳረፍ ከሁሉም ወገን ይጠበቃል
የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ተቀዳሚ ተግባር ሐዋርያዊ አገልግሎትን ማከናወን ቢሆንም የአገር ሰላም እንዲሰፍን የመሪነት ሚናስትጫወት ኖራለች። የምንገኝበት ዘመንም ከእስከ አሁኑ የበለጠ የሰላም ሐዋርያ መሆንን የሚጠይቅ ነው። እንኳን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በኢትዮጵያ ጉዳይ ይመለከተኛል የሚል አካል ሁሉ ሰላም የሚሰፍንበትን መንገድ መፈለግ ከሚያስፈልግበት ደረጃ ላይ እንገኛለን። የቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሰላም አምባሳደርነት ለአንድ ወገን ያደላ ሳይሆን የሁሉም እናትነት መሆኗን በተግባር መግለጥ ይገባዋል። Read more