እነርሱ እያቃጠሉ እኛ ስንሠራ አንኖርም
እነርሱ እያቃጠሉ እኛ ስንሠራ አንኖርም
ዘመናችን “መታዘዝ እንደ ድካም፣ ትሕትና እንደ ውርደት፣ ራስን መግዛት ራስን እንደ መጨቈን፣ በሥርዓት ማደር እንደ ኋላ ቀርነት፣ ክህነታዊ ተዋረድን የጠበቀ አገልግሎት ዘመን እንዳለፈበት የጭቆና መሣሪያ፣ ሃይማኖተኛነት እንደ ተራ ወግ አጥባቂነት ተፈርጆ ይዘመትበታል፡፡ ነባር ሃይማኖትን መቃወምን እንደ ሃይማኖት የያዘ መስተጻርርነት አየሩን ሞልቶታል” በማለት በአማን ነጸረ የጻፈው በተግባር ተገልጦ የሚታይበት ነው። ፀረ -ኦርቶዶክሶችም ይባል አክራሪዎች በኦርቶዶክሳውያን እንደሚሸነፉ ሲረዱ እግር ላይ ወድቀው የሚለምኑት በኦርቶዶክሳውያን መልካም ዕሴት ላይ ተሸጋግረው አዘናግተው ለማጥቃት ወይም ጊዜ ለመግዛት እንጂ በሚልኩት ሽምግልናም ሆነ በሚያቀርቡት ተማጽኖ አምነውበት አይደለም።
የአክራሪዎች መርሕ ራስ ብቻ ደኅና የሚል ነው። የራሳቸው ደኅንነት ከሌላው ደኅንነት ጭምር እንደሚመነጭ አመዛዝነው መረዳት የሚችሉበት አእምሮ የተነሣቸው ናቸው። መደጋገፍ የሚባለው አብሮ የመኖር ባህል፣ መከባበር የሚሉት መልካም ዕሴት አይገባቸውም። ሁሉ ነገር የእኛ፣ ሁሉን እኛ ይዘነው ሌላው ከገጸ ምድር ይጠፋ የሚል ነው። ለቀጣይ ትውልድ ማሰብ የሚባል ነገር አያውቁም። ሌላው የለፋበትን ነጥቆ መውሰድ ወይም ማውደም ሃይማኖት ብለው የያዙት እኩይ ድርጊት ነው። እግዚአብሔር የፈጠረውን ትውልድ በማጥፋት “የፈጠርከውን አጠፋንልህ” ብለው ለባለቤቱ ሪፖርት የሚያቅርቡ ናቸው። እንዲህ ያለው መረን የለቀቀ አስተሳሰብ ክቡር የሆነውን ፍጡር ከእንስሳ ተራ የሚያስመድብ ነው። Read more