የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት - በኢ/ኦ/ተ/ቤ የመንበረ ፓትርያርክ ሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ አንድነቱ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ተቋማዊ ራእይ፣ ተልእኮ
      • መዋቅራዊ አደረጃጀት
      • የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ተቋማዊ አደረጃጀት
      • የሰንበት ት/ቤቶች የሥራ አመራር ምርጫ ማስፈጸሚያ
    • ስልታዊ እቅድ 2018 – 2021 ዓ/ም
  • ሥርዓተ ትምህርት
    • መሠረታዊ መረጃዎች
    • የሰንበት ት/ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት አደረጃጀት መመሪያ
    • የሥርዓተ ትምህርቱ መመማሪያ መጻሕፍት ይዘት
      • የአንደኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
      • የኹለተኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
      • የሦስተኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
    • የሥርዓተ ትምህርቱ ዓመታዊ የጊዜ ሰሌዳ /ካሌንደር
    • የመምህራን ሥልጠና እና መልእክቶች
    • መጻሕፍቱን ለማግኘት እና ተጨማሪ መረጃ
    • ልዩ ልዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች
  • ፕሮጀክቶች
  • መዝሙረ ማኅሌት
    • የመስከረም ወር መዝሙሮች
      • የዮሐንስ መዝሙር
      • የመስቀል መዝሙሮች
      • የብዙኃን ማርያም መዝሙር (መስከረም ፳፩ )
      • የዘመነ ጽጌ መዝሙር
    • የጥቅምት ወር መዝሙሮች
      • የአብርሃ ወአጽብሐ መዝሙር (ጥቅምት 4 ቀን)
    • የኅዳር ወር መዝሙሮች
      • የቅዱስ ሚካኤል መዝሙር (ኅዳር 12 ቀን)
    • የጥር ወር መዝሙሮች
      • የዘመነ ጥምቀት መዝሙር
      • የቃና ዘገሊላ መዝሙር (ጥር 12 ቀን)
    • የመጋቢት ወር መዝሙሮች
      • የወርኃ ጾም መዝሙሮች
      • የሆሣዕና መዝሙራት
      • የሰሙነ ሕማማት መዝሙሮች
  • ዜና
    • አጫጭር ዜናዎች
    • ዝርዝር ዜናዎች
    • ወቅታዊ መረጃዎች
    • ማስታወቂያ
      • የሰንበት ትምህርት ቤቶች መጻሕፍት እንግሊዝኛ ትርጉም ሥራ ተሳትፎ ጥሪ
  • ያግኙን
  • ቋንቋ
    • ትግርኛ
    • Afaanoromo
  • Menu Menu

በሰማይ የሀሉ ልብክሙ – ልቡናችሁ በሰማይ ይኑር ቅዳሴ እግዚእ

በሰማይ የሀሉ ልብክሙ - ልቡናችሁ በሰማይ ይኑርቅዳሴ እግዚእ

በሰማይ የሀሉ ልብክሙ – ልቡናችሁ በሰማይ ይኑር
ቅዳሴ እግዚእ

በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንም ሆነ በአኃት አብያተ ክርስቲያን ጸሎተ ቅዳሴ የሚጀመረው ካህኑ ከምእመናን ጋር በሚያደርገው ተዋሥዖ (ምልልስ) ነው፡፡ ብሔራውያን ሊቃውንት ከመጽሐፈ ኪዳን የወሰዱትን አኮቴተ ቁርባን ቅዳሴ እግዚእ (የጌታ ቅዳሴ) ብለው ሰይመውታል፡፡[1] የዚህ ቅዳሴ አውስኦ የሚጀምረው በዲያቆኑ ‹‹በሰማይ የሀሉ ልብክሙ-ልባችሁ በሰማይ ይኑር›› በሚል ቃል ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከትንሣኤው በኋላ ከሐዋርያት ጋር ለዐርባ ቀናት ያህል ሲቆይ ያስተማራቸው እና ከሰባቱ ኪዳናት አንዱ ነው፡፡ ሊቃውንቱ ይህ ቃል ጌታ አስቀድሞ በጸሎተ ሐሙስ ሕብስቱን ያከበረበት በለሆሳስ የደገመው ቃል መሆኑን ይነግሩናል፡፡ ይህንኑ ቃል ከትንሣኤው በኋላ ለሐዋርያት እንዳስተማራቸውም ያስረዳሉ፡፡[2]

ጸሎተ ቅዳሴ በዚህ ምድር ያለችው ቤተ ክርስቲያን ከሰማያውያን መላእክት ጋር ኅብረት የምትፈጥርበት ሥርዓት፣ እግዚአብሔር በአንድያ ልጁ ሞት ለገለጸልን ታላቅ ፍቅር የምስጋና መሥዋዕት የምታቀርብበት የአምልኮዋ ማዕከል ነው፡፡ ልባችሁ በሰማይ ይኑር የሚለው አምላካዊ መልእክት ወደ ፊት በመንግሥተ እግዚአብሔር ከሰማያውን መላእክት ጋር የምንፈጽመውን አምልኮ በምድር ሆነን መለማመድ ወደሚያስችለን ሕይወት የሚመራን አምላካዊ ትእዛዝ ነው፡፡

ምእመናንም ‹‹አዎን ልቡናችን በሰማይ ይኑር፡፡ ስለ ስምህ አጽናን፤ ጌታችን እና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የተዘጋጀንም አድርገን›› በማለት ልቡናን በሰማይ ማኖር ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ እንደማይቻል ያመኑትን ምስክርነት ይሰጣሉ፡፡ እንዲያስችላቸውም ሁሉን የሚያስችል ኃያል ስሙን ጠርተው ይማጸናሉ፡፡

ጌታችን ‹‹ልቡናችሁ በሰማይ ይሁን፤›› ማለቱ ትንሣኤ ልቡናን ሲያስተምራቸው እንደሆነ ሊቃውንቱ ያስረዳሉ፡፡ ሰው ትንሣኤ ልቡና ካላገኘ ነፍስ ከምድር ጋር ካጣበቃት ጊዜያዊ ሐሳብ ተላቅቃ፣ የዲያብሎስን አሽከላ ሰብራ ነጻ መውጣት ይሳናታል፡፡ የእያንዳንዱ ኦርቶዶክሳዊ ትንሣኤ ልቡና በምእመናን እና በቤተ ክርስቲያን መሪዎች ዘንድ እየተዳከመ የመጣው ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር እና መንፈሳዊነት ትንሣኤ እንዲያገኝ መሠረት ነው፡፡ መልካም እረኞች በማነሳቸው ምክንያት የተቀዛቀዘው በምድር ላይ የእግዚአብሔር መንግሥት የሆነችው ቤተ ክርስቲያን የተሰማራችበት ተልእኮ መንፈሳዊ ሙቀት ያገኛል፡፡

ይህ ዘመን ቤተ ክርስቲያን ልባቸውን በሰማይ የሚያኖሩ ምእመናንን፣ ካህናትንና ጳጳሳትን በባትሪ የምታፈላልግበት ዘመን ነው፡፡ ልባቸውን በሰማይ ያኖሩ፣ ኅሊናቸውን በሰማይ የሆነላቸው በክርስቶስ ኢየሱስ ካገኙት ዘላለማዊ ጸጋ ተካፋዮች ናቸው፡፡ ልባቸውን አጭርና አላፊ ከሆነ ምድራዊ ኑሯቸው ሸክም አላቀው ኆኅተ ሰማይን በሚያስከፍት መንፈሳዊ ተግባር ላይ ያሰማሩ ናቸው፡፡ ስለዚህም  ያለንበት ጊዜ ልባችንን በሰማይ የምናኖርበት ጸጋ እንዲሰጠን ደጅ የምንጠናበት፣ ልባቸውን በሰማይ ያኖሩ አባቶች እንዲሰጠን አብዝተን ልንማጸንበት የሚገባ ጊዜ ነው፡፡ ምክንያቱም ልባቸውን በላይ በሰማይ ያኖሩ አበው መልካም እረኝነትን ገንዘብ ያደርጋሉ፤ በበጎቹ፣ በጠቦቶቹ እና በግልገሎቹ መካከል ልዩነት ሳያደርጉ ለሁሉም ነፍስ እኩል ይጠነቀቃሉ፡፡

በእርግጥ ‹‹ልባችሁን በሰማይ አኑሩ፤›› ብሎ የሚመክር የቤተ ክርስቲያን አባት ድምፅ እዚህም እዚያም ይሰማል፡፡ የምእመናን ነፍስ እየተፈተነች ያለችው ደግሞ ይህን መንፈሳዊ መልእክት ለምእመናኑ ሲነግሩ ኖረው እነርሱ ግን ልባቸውን በሰማይ አኑረው የሕይወት መምህር መሆን ባልቻሉ ‹‹አባቶች›› ነው፡፡ ልባቸውን በሰማይ አላኖሩምና ‹‹አኑሩ›› የሚል መልእክታቸው የምእመናንን የልቡና ደጅ ማስከፈት አልቻለም፡፡ በሰማይ በምድር ለሚኖር እግዚአብሔር ሲገዙ አልታዩምና ጵጵስና በክብር ከተጻፈበት የምእመናን የኅሊና ሰሌዳ መፋቅ ጀመረ፡፡ የእግዚአብሔር ጥሪ ሳይደርሳቸው ራሳቸውን ለሹመት አጭተው ሹመት ባለበት በዚያ ሲገፋፉ ያዩ ምእመናን በልባቸው ላይ ለአባቶች የሰጡት ዙፋን ተገረሰሰባቸው፡፡ ኖላውያን ተብለዋል ልባቸውን ግን ለዘውጋቸው፣ ልባቸውን ለገነነ ፍቅረ ነዋያቸው፣ ልባቸውን ለመንደርተኝነታቸው አስረክበዋል፡፡ እግዚአብሔርን ተስፋ በማድረግ ለሚገኘው ሰማያዊ በረከት የቀረ ቦታ ልባቸው ውስጥ መኖሩ ያጠራጥራል፡፡

ለአገልግሎት የተቀበለውን ሥልጣነ ክህነት የምድር ሕይወቱን ሊያቀናበት የሚሻ ሰው ልቡን ገንዘቡን ባስቀመጠበት በዚህ በምድር እንጂ የነፍስ ፍስሐን ፍለጋ በሰማይ ማኖር ይከብደዋል፡፡ ገንዘብህ ባለበትልብህበዚያደግሞይኖራል። ከምድራዊነት መላቀቅ አይችልም፡፡ ልባቸውን በሰማይ ያደረጉ እውነተኛ አበው ግን መንፈሳቸው ለሰማያዊው ክብር ከመሸነፉ የተነሣ ለቁመተ ሥጋ ያህል የሚመገቡትን መቁኑን እንኳ ጨርሰው ሲረሱት እንመለከታለን፡፡ አንድ ማሳያ ታሪክ አንስተን እንቋጨው፤

አንድ አረጋዊ ሌላውን በተጋድሎ ላይ ያለ አረጋዊ አባትን ሊጎበኝ ወደ በዓቱ ሔዱ፡፡ አስተናጋጁ አረጋዊውም ረድዑን ትንሽ የሚቀመስ እንዲያዘጋጅ አደራ አለው፡፡ ረድዑ በሰዓቱ አዘጋጅቶ አቀረበ፡፡ እነርሱ ግን ስለ መንፈሳዊ ነገር እየተነጋገሩ እስከሚቀጥለው እኩለ ቀን ድረስ ቆዩ፡፡ ልባቸው በሰማይ ነውና የምድሩን ረሱት፡፡ አስተናጋጁ አባትም ረድዑን እንደ አዲስ ‹‹ልጄ ሆይ ትንሽ ነገር አዘጋጅልን›› አለው፡፡ እርሱም ከአንድ ቀን በፊት ያዘጋጀውን አቀረበላቸውና ያን ጊዜ በሉ፡፡[3] አባቶች በእግዚአብሔር ፈቃድ እንዲህ ሲገናኙ ከለመዱት መንፈሳዊ ተጋድሎ ዐረፍ ብለው ቃለ እግዚአብሔርን እየተነጋገሩ መሽቶ ሲነጋ፣ ቀን ሔዶ ቀን ሲተካ አይታወቃቸውም፡፡ አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ ከአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጋር በተገናኙ ጊዜ፣ እንዲሁም ሌሎች ቅዱሳን ስለመገናኘታቸው በተዘገበባቸው ድርሳናት ተመሳሳይ ነገር መፈጸሙ ተከተቧል፡፡ በሚነጋገሩት መንፈሳዊ ቃል ተመስጠው የሥጋ ረለብ፣ የአካል ድካም አይሰማቸውም፤ ልባቸውን በሰማይ አኑረዋልና፡፡

ዋቢ መጽሐፍት

  1. ቀሲስ ዶ/ር መብራቱ ኪሮስ (፳፻፲፪ ዓ.ም.)፤ አኮቴተ ቁርባን፤ ገጽ ፻፵፬፤ ፪፻፹፯፤
  2. ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ (፳፻፲ ዓ.ም.)፤ እረኛ ወይስ ምንደኛ፣ ገጽ ፺፤
  3. ዲ. ያረጋል አበጋዝ (፳፻፰ ዓ.ም.)፤ ከበርሐውያን ሕይወትና አንደበት፤ ገጽ ፵፫

 

 

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on LinkedIn
  • Share on Telegram
  • Share by Mail
https://eotc-gssu.org/a/wp-content/uploads/besemay.jpg 1080 1920 Abenezer Mamushet https://eotc-gssu.org/a/wp-content/uploads/logo-2-1-300x74-1.png Abenezer Mamushet2023-07-16 20:55:392023-07-16 20:56:57በሰማይ የሀሉ ልብክሙ – ልቡናችሁ በሰማይ ይኑር ቅዳሴ እግዚእ
Search Search

Recent Posts

  • የሦስተኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
  • የኹለተኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
  • የአንደኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
  • የመስቀል ደመራ በዓል በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ
  • ሦስተኛ ዙር የ፲፪ ክፍል ምርቃት መርሐ ግብር ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ በተገኙበት ተከናወነ።

Archives

  • April 2026
  • September 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • May 2025
  • April 2025
  • October 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • November 2022
  • October 2022
  • September 2022
  • July 2022
  • June 2022
  • April 2022
  • February 2022
  • January 2022
  • October 2021
  • September 2021
© Ethiopian Orthodox Church Global Sunday School Union | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
  • Link to Youtube
  • Link to Telegram
  • Link to TikTok
Link to: በሕገ ወጥ ሹመት የተሳተፉ አባቶችን ዕጩ አድርጎ ማቅረብ ያለው ዳፋ Link to: በሕገ ወጥ ሹመት የተሳተፉ አባቶችን ዕጩ አድርጎ ማቅረብ ያለው ዳፋ በሕገ ወጥ ሹመት የተሳተፉ አባቶችን ዕጩ አድርጎ... Link to: ቤተ ክርስቲያን ለምን ለውጥ ያስፈልጋል? Link to: ቤተ ክርስቲያን ለምን ለውጥ ያስፈልጋል? ቤተ ክርስቲያን ለምን ለውጥ ያስፈልጋል?
Scroll to top Scroll to top Scroll to top