የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት - በኢ/ኦ/ተ/ቤ የመንበረ ፓትርያርክ ሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ አንድነቱ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ተቋማዊ ራእይ፣ ተልእኮ
      • መዋቅራዊ አደረጃጀት
      • የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ተቋማዊ አደረጃጀት
      • የሰንበት ት/ቤቶች የሥራ አመራር ምርጫ ማስፈጸሚያ
    • ስልታዊ እቅድ 2018 – 2021 ዓ/ም
  • ሥርዓተ ትምህርት
    • መሠረታዊ መረጃዎች
    • የሰንበት ት/ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት አደረጃጀት መመሪያ
    • የሥርዓተ ትምህርቱ መመማሪያ መጻሕፍት ይዘት
      • የአንደኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
      • የኹለተኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
      • የሦስተኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
    • የሥርዓተ ትምህርቱ ዓመታዊ የጊዜ ሰሌዳ /ካሌንደር
    • የመምህራን ሥልጠና እና መልእክቶች
    • መጻሕፍቱን ለማግኘት እና ተጨማሪ መረጃ
    • ልዩ ልዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች
  • ፕሮጀክቶች
  • መዝሙረ ማኅሌት
    • የመስከረም ወር መዝሙሮች
      • የዮሐንስ መዝሙር
      • የመስቀል መዝሙሮች
      • የብዙኃን ማርያም መዝሙር (መስከረም ፳፩ )
      • የዘመነ ጽጌ መዝሙር
    • የጥቅምት ወር መዝሙሮች
      • የአብርሃ ወአጽብሐ መዝሙር (ጥቅምት 4 ቀን)
    • የኅዳር ወር መዝሙሮች
      • የቅዱስ ሚካኤል መዝሙር (ኅዳር 12 ቀን)
    • የጥር ወር መዝሙሮች
      • የዘመነ ጥምቀት መዝሙር
      • የቃና ዘገሊላ መዝሙር (ጥር 12 ቀን)
    • የመጋቢት ወር መዝሙሮች
      • የወርኃ ጾም መዝሙሮች
      • የሆሣዕና መዝሙራት
      • የሰሙነ ሕማማት መዝሙሮች
  • ዜና
    • አጫጭር ዜናዎች
    • ዝርዝር ዜናዎች
    • ወቅታዊ መረጃዎች
    • ማስታወቂያ
      • የሰንበት ትምህርት ቤቶች መጻሕፍት እንግሊዝኛ ትርጉም ሥራ ተሳትፎ ጥሪ
  • ያግኙን
  • ቋንቋ
    • ትግርኛ
    • Afaanoromo
  • Menu Menu

ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ በ14ኛው ዓለም አቀፍ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ያስተላለፉት መልእክት

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ። አሜን

እንኳን ለ14ኛው ዓለም አቀፍ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ እና የሰንበት ት/ቤቶች ቀን አደረሳችሁ

“ተዘከሮ ለፈጣሪከ በመዋዕለ ውርዙትከ ዘእንበለ ይመጻእ መዋዕል እኩይ ወይመጽእ ዓመታተ በእለ ትብል ኢኮነኒ ቦቶን ፈቃድየ፦ የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጕብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ ደስ አያሰኙም የምትላቸውም ዓመታት ሳይደርሱ።” መክ 12፥1 ጠቢቡ ሰሎሞን ጭንቅ ቀን የመከራ ቀን ሳይመጣ የጉብዝና ወራት በተባለ የወጣትነት ዘመንን ለእግዚአብሔር መስጠት እንዲሚያስፈልግ ያስተምራል፡፡ ይህንንም መሠረት በማድረግ ቤተ ክርስቲያን የጉብዝናን ዘመን በቤተ ክርስቲያን በሰንበት ት/ቤት እንዲሆን ታስተምራለች።
ሰንበት ትምህርት ቤት በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ከፍተኛ ሥፍራ ካላቸው ተቋማት አንዱ ነው። ዘመን ተሻጋሪዋ ቤተ ክርስቲያናችን ቀድማ የነገዋ ቤተ ክርስቲያን ተረካቢ ትውልድን ስብስባ፣ ታላላቅ ሥራዎችን የምትሠራበት፣ ትውልዱን በማስተዋል በእውቀት በሃይማኖት በሥነ ምግባር በልዩ ልዩ ጸጋ የምትቀርጽበት የተወደደ ሥፍራ ሰንበት ት/ቤት ነው፡፡ ከሰንበት ትምህርት ቤት ብዙ ሊቃውንት፣ ብዙ መሪዎች፣ ብዙ መምህራን፣ ብዙ አገልጋዮች፣ ብዙ ባለሙያዎች እና ጠንካራ አማኞች ተገኝተዋል።

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ልጆቿ ጽድቅን ይማሩ ዘንድ በሰንበት ት/ቤት አሰባስባ እግዚአብሔርን አውቀው እንዲያመልኩ፣ ሕጉን ጠብቀው፣ በሃይማኖት፣ በምግባርና በትሩፋት ጸንተው አምላካቸውን መስለው እንዲኖሩ፣ የእርሱ የሆነችውን መንግሥተ እግዚአብሔርን እንዲወርሱ በብሉይ ከአምላኳ የተቀበለችውን ሕግጋተ እግዚአብሔርን አስተምራ በሐዲስ ኪዳንም በ40ና በ80 ቀን እያጠመቀች ለምዕመናን እንደ እድሜያቸው ቃለ እግዚአብሔርን በስብከት፣ በዝማሬ፣ በቅዳሴ፣ በሰዓታት፣ በማሕሌት፣ በቅኔ፣ በትርጓሜው እያስተማረች ምዕመናንን በሃይማኖት አንፃ ለመንግሥተ ሰማያት እያዘጋጀች ዛሬ ላይ ደርሳለች።

ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና የዚህ ጉባኤ ታዳሚዎች

ሰንበት ት/ቤት ሕጻናት ወጣቶች የቤተ ክርስቲያንን ዶግማ፣ ቅኖና፣ ሥርዓትና ትውፊት የሚማሩበት እና በእምነት፣ በምግባርና በሃይማኖት ጸንተው ይኖሩ ዘንድ መንፈሳዊ ሕይወታቸውን የሚያጠነክሩበት ታላቅ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ነው:: በመጽሐፍ ቅዱስ ሰንበት ት/ቤት ተብሎ የተፃፈ ቀጥተኛ የሆነ ስም ባይገኝም ዛሬ ላይ በሰንበት ትምህርት ቤት የሚተገበረው መንፈሳዊ አገልግሎት ማለትም ልጆችን በቤተ እግዚአብሔር ማስተማር በብሉይ ኪዳን ዘመንም ይፈጸም እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ያስረዳናል። የሰንበት ት/ቤት ፅንሰ ሀሳብም ከዚያ የመነጨ ነው። ኦሪት ዘዳግም 11÷18-21

በሐዲስ ኪዳንም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌ ልዩ ትኩረት ከሰጣቸው መካከል ሕፃናት (ወጣቶች) ወደ ቤተ ክርስቲያን ይመጡ ዘንድ ነበር። በዚህም ለሰንበት ትምህርት ቤት መነሻ የሆነ እና መሠረቱም መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሆኑን ያረጋግጥልናል። (ማቴ 18፥3፣ 21፥16፣ ማር 9፥37)። በዚህ መነሻነት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮዎቿ _ ሳይበረዙ _ ለትውልድ እንዲተላለፉ በተለይ በሕጻናት እና በወጣቶች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ለመሥራት ተሞክሯል።

ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና የዚህ ጉባኤ ታዳሚዎች

ይህ የቤተ ክርስቲያን ዋና ተልዕኮ ቅድሚያ የሚሰጠው ሐዋርያዊ ተግባር ሆኖ ሳለ እነዚህን የነገዋ ቤተ ክርስቲያን ተረካቢ የሰንበት ት/ቤት ልጆቻችንን በአግባቡ ባለመመልከታችን፣ እንደ አባት ለልጅ የሚደረገውን ባለማድረጋችን፣ የሚገባውን ሥፍራ ሰጥተን ባለመሥራታችን ምክንያት ከበረቱ የተበተኑ፣ ከቤቱ የራቁ፣ ከአገልግሎት የጠፉ፣ ጀመረው ያልጨረሱ፣ ወድቀው ያልተነሱ ያለአስታዋሽ የቀሩ ጥቂት የማይባሉ ናቸው።

በተጨማሪም በዚህ ዘመን መሰማማት፣ መደማመጥ፣ መታዘዝ፣ መከባበር፣ ትህትና እና ፍቅር የጎደለው ቤተሰብን፣ ቤተ ክርስቲያንን፣ ሀገርን፣ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን እና ሽማግሌዎችን የሚያከብር ትውልድ አጥተናል፡፡ በየዕለቱም ፍቅር ሳይሆን ጥላቻ፣ ርሕራሄ ሳይሆን ጭካኔ፣ መረዳዳት ሳይሆን መገፋፋት፣ ክብር ሳይሆን ማዋረድ፣ ምርቃት ሳይሆን እርግማን፣ ምስጋና ሳይሆን ስድብ እየበዛ ከመሄዱ አንጻር ትውልዱን እያጠፋ ይገኛል።

ስለዚህ ሰንበት ት/ቤት ይህን እና ተመሳሳይ ጉዳዮችን ለመቅረፍ ለቤተ ክርስቲያን ጥቅሙና አስፈላጊነቱ የጎላ በመሆኑ ከየትኛውም ሥራችን አስቀድመን በዚህ ትውልድ ላይ በትኩረት አስፈላጊውን በጀት በመበጀት በገጠር በከተማ በሙሉ ኃይላችን ነፍሳችን ጭምር ሰጥተን መሥራት ይጠበቅብናል፡፡
እግዚአብሔር ቢፈቅድ እኛ ከእናንተ ከሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጋር ከወጣቱ ጋር ቤተ ክርስቲያንን ከፍ የሚያደርጉ ታላላቅ ሥራዎችን እቅድ አቅደን፣ ተገቢውን ጥናት አጥንተን፣ ተመካከረን፣ … ተወያይተን ሥራዎችን መሥራት ይገባናል፡፡ እንሥራለን እግዚአብሔርም ይረዳናል።

ሰንበት ት/ቤቶች እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የቤተ ክርስቲያን አባቶች፣ ሊቃውንት፣ አገልጋዮች፣ መምህራን እና ጽኑ አማኞች መገኛ እንደመሆኑ መጠን በየአጥቢያው ሰበካ ጉባኤው የአብነት መምህራን በመቅጠር ሰንበት ትምህርት ቤቱን በማጠናከር ትውልዱን በኦርቶዶክሳዊ የሃይማኖት ትምህርት በማነጽ፣ ዶግማን፣ ቀኖናን እና ትውፊትን በማስተማር በየሀገረ ስብከቱ በሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ሰንበት ት/ቤቶች እንዲቋቋሙ፣ የተቋቋሙትም እንዲጠናከሩ ማድረግ ያስፈልጋል።

በተጨማሪም የሰንበት ት/ቤቶች አገልግሎትን የበለጠ ለማጠናከር ሆነ ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶችን በመስጠት ወጣቱን ትውልዱ በዘመናዊነት ተፅዕኖ ውስጥ ወድቆ ከመንፈሳዊ ሕይወት እንዳይወጣ ልዩ ክትትል ማድረግ የሰንበት ት/ቤቶች ለተቋቋሙበት ዓላማና ተግባር እንዲንቀሳቀሱ ማገዝ መርዳት እንደሚያስፈልግ መዘንጋት የለብንም፡፡

ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የዚሁ ጉባኤ ታዳሚዎች

ቤተ ክርስቲያን በባሕርይዋ አንዲት፣ ሐዋርያዊት፣ ቅድስት እና ኩላዊት (ዓለም አቀፋዊት) እንደመሆኗ መጠን ትውልዱ ይህን በተግባር ማየት ይሻል። እውነት ነው ብዙ ያንቀላፋንበት፣ በእውነት በዓላማ ያልተንቀሳቀስንበት፣ ትኩረት ሰጥተን ያልሠራንበት፣ ተግተን ያላገለገልንበት፣ ጊዜ ብዙ ነፍሳት እና ብዙ ትውልድ አሳጥቶናል። ቀላልም የማይባል ዋጋም ጭምር አስከፍሎናል፡፡ ስለሆነም ከየትኛውም ጊዜ በላይ በቤተ ክርስቲያናችን፣ በቤተሰብ፣ በማኅበራዊ፣ በሀገራዊ፣ በአንድነታችን፣ በጠፋው ሰላማችን፣ በቀዘቀዘው ፍቅራችን፣ በደከመው እድገታችን፣ ትጋት በሌለው መንፈሳዊ አገልግሎታችን እና በሃይማኖታችን ጉዳዮች ላይ ይሄ የእግዚአብሔር የሥራ ጊዜ ነውና በፍቅር፣ በሰላም፣ በአንድነት፣ በመከባበር፣ በመተባበር፣ በትሕትና እና በመናበብ፣ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ፣ እንደ አንድ ልብ መካሪ፣ በመሆን በተሰጠን ኃላፊነት ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ክብር እና እድገት ልንሠራ ያስፈልጋል።

የሰንበት ት/ቤቶችን አገልግሎት ያስፋልን፡፡

እግዚአብሔርበመንፈሳዊ በረከት ይባርካችሁ።

ተባረኩ ብሩክ ሁኑ፡፡

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ

ግንቦት 3ዐ ቀን 2017 ዓ.ም

አባ ሳዊሮስ

የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ
የደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም የበላይ ሓላፊ

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on LinkedIn
  • Share on Telegram
  • Share by Mail
https://eotc-gssu.org/a/wp-content/uploads/photo_2025-06-09_07-26-00.jpg 1280 719 Abenezer Mamushet https://eotc-gssu.org/a/wp-content/uploads/logo-2-1-300x74-1.png Abenezer Mamushet2025-06-09 07:30:382025-06-09 19:52:04ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ በ14ኛው ዓለም አቀፍ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ያስተላለፉት መልእክት
Search Search

Recent Posts

  • የሦስተኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
  • የኹለተኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
  • የአንደኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
  • የመስቀል ደመራ በዓል በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ
  • ሦስተኛ ዙር የ፲፪ ክፍል ምርቃት መርሐ ግብር ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ በተገኙበት ተከናወነ።

Archives

  • April 2026
  • September 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • May 2025
  • April 2025
  • October 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • November 2022
  • October 2022
  • September 2022
  • July 2022
  • June 2022
  • April 2022
  • February 2022
  • January 2022
  • October 2021
  • September 2021
© Ethiopian Orthodox Church Global Sunday School Union | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
  • Link to Youtube
  • Link to Telegram
  • Link to TikTok
Link to: ብፁዕ አቡነ ቀለሜንጦስ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ እና የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በ14ኛው የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ያስተላለፉት መልእክት Link to: ብፁዕ አቡነ ቀለሜንጦስ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ እና የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በ14ኛው የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ያስተላለፉት መልእክት ብፁዕ አቡነ ቀለሜንጦስ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ... Link to: የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ፲፬ኛው ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ የቃለ ጉባኤ ማጠቃለያ እና የጋራ የውሳኔ ሐሳብ Link to: የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ፲፬ኛው ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ የቃለ ጉባኤ ማጠቃለያ እና የጋራ የውሳኔ ሐሳብ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ፲፬ኛው ዓመታዊ ጠቅላላ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top