የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት - በኢ/ኦ/ተ/ቤ የመንበረ ፓትርያርክ ሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ አንድነቱ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ተቋማዊ ራእይ፣ ተልእኮ
      • መዋቅራዊ አደረጃጀት
      • የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ተቋማዊ አደረጃጀት
      • የሰንበት ት/ቤቶች የሥራ አመራር ምርጫ ማስፈጸሚያ
    • ስልታዊ እቅድ 2018 – 2021 ዓ/ም
  • ሥርዓተ ትምህርት
    • መሠረታዊ መረጃዎች
    • የሰንበት ት/ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት አደረጃጀት መመሪያ
    • የሥርዓተ ትምህርቱ መመማሪያ መጻሕፍት ይዘት
      • የአንደኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
      • የኹለተኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
      • የሦስተኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
    • የሥርዓተ ትምህርቱ ዓመታዊ የጊዜ ሰሌዳ /ካሌንደር
    • የመምህራን ሥልጠና እና መልእክቶች
    • መጻሕፍቱን ለማግኘት እና ተጨማሪ መረጃ
    • ልዩ ልዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች
  • ፕሮጀክቶች
  • መዝሙረ ማኅሌት
    • የመስከረም ወር መዝሙሮች
      • የዮሐንስ መዝሙር
      • የመስቀል መዝሙሮች
      • የብዙኃን ማርያም መዝሙር (መስከረም ፳፩ )
      • የዘመነ ጽጌ መዝሙር
    • የጥቅምት ወር መዝሙሮች
      • የአብርሃ ወአጽብሐ መዝሙር (ጥቅምት 4 ቀን)
    • የኅዳር ወር መዝሙሮች
      • የቅዱስ ሚካኤል መዝሙር (ኅዳር 12 ቀን)
    • የጥር ወር መዝሙሮች
      • የዘመነ ጥምቀት መዝሙር
      • የቃና ዘገሊላ መዝሙር (ጥር 12 ቀን)
    • የመጋቢት ወር መዝሙሮች
      • የወርኃ ጾም መዝሙሮች
      • የሆሣዕና መዝሙራት
      • የሰሙነ ሕማማት መዝሙሮች
  • ዜና
    • አጫጭር ዜናዎች
    • ዝርዝር ዜናዎች
    • ወቅታዊ መረጃዎች
    • ማስታወቂያ
      • የሰንበት ትምህርት ቤቶች መጻሕፍት እንግሊዝኛ ትርጉም ሥራ ተሳትፎ ጥሪ
  • ያግኙን
  • ቋንቋ
    • ትግርኛ
    • Afaanoromo
  • Menu Menu

“ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ።” ዳን 10፡13

እንኳን ለተራዳኢው መልአክ ለቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ!
#ሚካኤል ማለት መኑ ከመ አምላክ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው የሚል ትርጉም አለው። ይህም እንደ እግዚአብሔር ያለ በባሕርይው ቅዱስ የሆነ ፣ እንደ እግዚአብሔር ያለ ንጹሐ ባሕርይ ፣ እንደ እግዚአብሔር ያለ ፍጹም ማነው የሚል ነው። ቅድስና ፣ ንጽሕና እና ፍጹምነት የባሕርይ ገንዘቡ የሆነ ከእግዚአብሔር በቀር የለምና። ዘዳ 33፡26
ሰኔ 12 በዚህች ቀን የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በዓለ ሲመቱ ይታሰባል። እንዲሁም የባህራንን የሞቱን ደብዳቤ ወደ ሕይወት የቀየረበት እንዲሁም ቅድስት አፎምያን ከሰይጣን ያዳነበት መታሰቢያ ነው። “በመንገድ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ስፍራ ያገባህ ዘንድ፥ እነሆ፥ እኔ መልአክን በፊትህ እሰድዳለሁ።” ዘጸ 23፡20 ይህ መልአክ በብሉይ እስራኤል ዘሥጋን ከግብጽ ባርነት መርቶ ነጻ እንዳወጣቸውና ምድረ ርስት ከንዐንን እንዲወርሱ በመንገዳቸው ሁሉ እንደረዳቸው፤ እንደጠበቃቸው ሁሉ ባሕራንም ይሄድ ከነበረበት የሞት መንገድ ሕይወትን ሰጥቶ ፤ አፎምያን ደግሞ ከጥንተ ጠላታችን ከዲያብሎስ እጅ በተራዳኢነቱ አድኖ ለክብር አብቅቷቸዋል።
በባሕራን እና በቅድስት አፎሚያ ታሪክ ውስጥ የምናገኘው የመልአኩ ተራዳኢነት ዛሬ ላይ ላለነው ለክርስቲያኖች በሕይወታችን ውስጥ የመልአኩን ተራዳኢነት አምነን እንድንጠቀም ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ ነው። ቅዱስ ሚካኤል ወይም ቅዱሳን መላእክት በሰዎች የዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ መዳን መንግሥተ ሰማይን ለመውረስ በሚደረጉ ሒደቶች ሁሉ የሚራዱና የሚያግዙ ናቸው። ቅዱስ ጳውሎስ በዕብራውያን መልእክቱ ላይ “ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስ አይደሉምን?” ብሏል። ዕብ 1፡14 ዛሬም እኛ ከቅዱሳን መናፍስት ወገን አንዱና አለቃቸው የሆነ ቅዱስ ሚካኤል መዳን መንግሥተ ሰማይን እንወርስ ዘንድ የሚላክ የሚያገለግል አይደለምን እንላለን። ማመን መጠመቅ በጎ ሥራ መሥራት ሕጉን ትዕዛዙን መጠበቅ ንስሐ መግባት እነዚህ በሙሉ ወደ መዳን / መንግሥተ ሰማያት / የሚያደርሱን መንገዶች ናቸው ፡፡
የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል
ለሰዎች የሚራራ ፣ በተጨነቁም ጊዜ የሚያረጋጋ ፣ በደከሙ ጊዜ የሚያበረታ ፣ ባዘኑ ጊዜ የሚያጽናና ነው። ሉቃ 22፡43 ፣ ዳን 10፡20
የሰው ልጆችን ከመከራ ሥጋ እና ከመከራ ነፍስ የሚያድን የሚታደግ ነው። መዝ 33፡7 ፣ ዘፍ 48፡16 ፣ ዕብ 1፡14
ሰውን ከሚገጥመው ክፉ ነገር ሁሉ ይራዳል። ዳን 10፡13 ፣ ዳን 12፡1
ስለ ሰዎች ይማልዳል ከአምላካቸው ያስታርቃል። ዘካ 1፡12-13
ለሰው ሁሉ በጎን የሚያደርግ መልአክ ነው። ሔኖክ 6፡1-2
የከበረ መልአክ ነው። ከክብሩ የተነሳም ምድር ሁሉ ትበራለች። ራእ 10፡1 ፣ ራእ 18፡1
ትሕትናን የሚያስተምር ትሑት መምህረ ትሕትና ነው። ይሁ 1፡9
በሰዎች ድኅነት ሀሴት ደስታን የሚያደርግ ነው። ሉቃ 15፡7
የመልአኩ የቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነቱ አማላጅነቱ በዚህም ዓለም በወዲያኛውም ዓለም ይጠብቀን።
ይቆየን!
መልካም በዓል!
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on LinkedIn
  • Share on Telegram
  • Share by Mail
https://eotc-gssu.org/a/wp-content/uploads/social-media-post-ቅዱስ-ሚካኤልjpg.jpg 3508 2480 Abenezer Mamushet https://eotc-gssu.org/a/wp-content/uploads/logo-2-1-300x74-1.png Abenezer Mamushet2025-06-18 21:21:392025-06-18 21:21:39“ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ።” ዳን 10፡13
Search Search

Recent Posts

  • የሦስተኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
  • የኹለተኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
  • የአንደኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
  • የመስቀል ደመራ በዓል በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ
  • ሦስተኛ ዙር የ፲፪ ክፍል ምርቃት መርሐ ግብር ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ በተገኙበት ተከናወነ።

Archives

  • April 2026
  • September 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • May 2025
  • April 2025
  • October 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • November 2022
  • October 2022
  • September 2022
  • July 2022
  • June 2022
  • April 2022
  • February 2022
  • January 2022
  • October 2021
  • September 2021
© Ethiopian Orthodox Church Global Sunday School Union | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
  • Link to Youtube
  • Link to Telegram
  • Link to TikTok
Link to: የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና የሞዴልና ማጠቃለያ ፈተና ለመፈተን ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የሀገር አቀፍ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት አሳወቀ። Link to: የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና የሞዴልና ማጠቃለያ ፈተና ለመፈተን ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የሀገር አቀፍ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት አሳወቀ። የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና የሞዴልና ማጠቃለያ... Link to: ከየሀገረ ስብከቱ ለተውጣጡ የሰንበት ትምህርት ቤት መምህራን የክረምት የአሠልጣኞች ሥልጠና ለመስጠት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የሰ/ት/ቤቶች አንድነት አስታወቀ። Link to: ከየሀገረ ስብከቱ ለተውጣጡ የሰንበት ትምህርት ቤት መምህራን የክረምት የአሠልጣኞች ሥልጠና ለመስጠት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የሰ/ት/ቤቶች አንድነት አስታወቀ። ከየሀገረ ስብከቱ ለተውጣጡ የሰንበት ትምህርት...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top