ሰላምሽ ዛሬ ነው ኢየሩሳሌም

ወደ አንቺ መጥቷልና አምላክ ዘለዓለም(2)

ሆሣዕና በአርያ እያሉ ዘመሩ ሕጻናት በኢየሩሳሌም

አንቺ ቤተልሔም የዳዊት ከተማ

የሕዝቦችሽ ብርሃን መጣልሽ በግርማ(2)

ሆሣዕና እያሉ አመሰገኑት በኢየሩሳሌም

አእሩግ ሕጻናት

አዝ…….

ኪሩቤል መንበሩ የሚሸከሙለት

መስቀል ተሸከመ ሊሆነን መድኃኒጽ(2)

የኢየሱስን ሕማም ደናግልም አይተው

እያለቀሱለት ሂዱ ተከትለው(2)

አዝ….

(መዝሙረ ስብሐት)

ሆሣዕና(2) በአርያም ሆሣዕና በአርያም

ቅድስት ሀገር ሆይ ኢየሩሳሌም

ክብርሽ ብዙ ነው በመላው ዓለም

በአህያ ላይ ሆኖ ወዳንች የገባው

ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም መድኃኒት ነው

አዝ…………

ኃይልና ሥልጣንም ባንድ ላይ ስላለው

ጠላቶችሽ ፈሩ ሕዝብሽም ደስ አለው

አዝ………

እናውቃለን ባዮች ግብዞች ሲቀሩ

ወጣት ሽማግሌ ሕጻናትም ሆነው ባንድነት ዘመሩ

አዝ………..

ሰውማ ቢዘመር ምን ያስገርመናል

ሆሣዕና ሰው ቀርቶ ድንጋይ ያናግራል

አዝ……..

(አእምሮ ማንደፍሮ)

ሆሣዕና ዕምርት እንተ አቡነ ዳዊት(2)

ቡርክት እንተ ትመጽእ መንግሥት(2)

(ቅዱስ ያሬድ)

 ይባእ ንጉሠ ስብሐት(2)

ይባእ አምላከ ምሕረት(4)

             (ቅዱስ ያሬድ)

ሆሣዕና ሆሣዕና ሆሣዕና ለወልደ ዳዊት

አባቶች እናቶች ሕጻናት በሙሉ

ለዓለም መድኃኒት ሆሣዕና በሉ(2)

አዝ……

ከአህያዋ ጀርባ አምላክ ቁጭ አለና

አሳየ ለሕዝቡ ታላቁን ትህትና

አዝ…

ሆሣዕና በአርያም(2)

የዳዊት ልጅ ገባ በኢየሩሳሌም(2)

ቤቱን ቢያደርጉበት የዓመጽ መደብር

በጌትነት ገባ የሰው ልጅ በክብር(2)

አዝ…….

በእህያ ተቀምጦ ሲመጣ ቢያዩት

ሕጻናት በአንድነት አመሰገኑት(2)

አዝ…..

ሊቃነ ካህናት በጣም ተቆጥተው

ይማከሩ ጀመር ብለው እንስቀለው(2)

አዝ………..

(ናዝሬት ቅ/ማርያም)

የዘመን ፍጻሜ እስከዚህ የሌለህ(3)

ዘለዓለም የምትኖር ፍጹም አምላክ ነህ

ሆሣዕና(3) በአርያም

ቡሩክ ሆሣዕና አምላክ እስራኤል

ተቀምጦ መጣ በአህያ ግልገል

ሆሣዕና(3) በአርያም

ትንሹም ትልቁም በአንድነት ዘመሩ

አመሰገኑት(3) ሆሣዕና እያሉ

ሆሣዕና(3) በአርያም

በጣም ደስ ይበልሽ ዕልል በይ ጽዮን

ንጉሥሽ መጣልሽ(3) ሊሆንሽ መድኅን

ሆሣዕና(3) በአርያም

ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና ለወልደ ዳዊት(2)

ለንጉሠ እሥራኤል ለንጉሠ እስራኤል(2)

(መምህር ዕቁ ባሕርይ ተከስተ)