የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት - በኢ/ኦ/ተ/ቤ የመንበረ ፓትርያርክ ሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ አንድነቱ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ተቋማዊ ራእይ፣ ተልእኮ
      • መዋቅራዊ አደረጃጀት
      • የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ተቋማዊ አደረጃጀት
      • የሰንበት ት/ቤቶች የሥራ አመራር ምርጫ ማስፈጸሚያ
    • ስልታዊ እቅድ 2018 – 2021 ዓ/ም
  • ሥርዓተ ትምህርት
    • መሠረታዊ መረጃዎች
    • የሰንበት ት/ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት አደረጃጀት መመሪያ
    • የሥርዓተ ትምህርቱ መመማሪያ መጻሕፍት ይዘት
      • የአንደኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
      • የኹለተኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
      • የሦስተኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
    • የሥርዓተ ትምህርቱ ዓመታዊ የጊዜ ሰሌዳ /ካሌንደር
    • የመምህራን ሥልጠና እና መልእክቶች
    • መጻሕፍቱን ለማግኘት እና ተጨማሪ መረጃ
    • ልዩ ልዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች
  • ፕሮጀክቶች
  • መዝሙረ ማኅሌት
    • የመስከረም ወር መዝሙሮች
      • የዮሐንስ መዝሙር
      • የመስቀል መዝሙሮች
      • የብዙኃን ማርያም መዝሙር (መስከረም ፳፩ )
      • የዘመነ ጽጌ መዝሙር
    • የጥቅምት ወር መዝሙሮች
      • የአብርሃ ወአጽብሐ መዝሙር (ጥቅምት 4 ቀን)
    • የኅዳር ወር መዝሙሮች
      • የቅዱስ ሚካኤል መዝሙር (ኅዳር 12 ቀን)
    • የጥር ወር መዝሙሮች
      • የዘመነ ጥምቀት መዝሙር
      • የቃና ዘገሊላ መዝሙር (ጥር 12 ቀን)
    • የመጋቢት ወር መዝሙሮች
      • የወርኃ ጾም መዝሙሮች
      • የሆሣዕና መዝሙራት
      • የሰሙነ ሕማማት መዝሙሮች
  • ዜና
    • አጫጭር ዜናዎች
    • ዝርዝር ዜናዎች
    • ወቅታዊ መረጃዎች
    • ማስታወቂያ
      • የሰንበት ትምህርት ቤቶች መጻሕፍት እንግሊዝኛ ትርጉም ሥራ ተሳትፎ ጥሪ
  • ያግኙን
  • ቋንቋ
    • ትግርኛ
    • Afaanoromo
  • Menu Menu

ተሿሚዎችን ለምእመናን አለማሳወቅ የሚያስከትለው መዘዝ

ተሿሚዎችን ለምእመናን አለማሳወቅ የሚያስከትለው መዘዝ

ተሿሚዎችን ለምእመናን አለማሳወቅ የሚያስከትለው መዘዝ

በዘመናችን ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን ውጭ የሚፈጸሙ ጉዳዮች በርክተዋል። አባቶች የሠሩትን ቀኖና እያፈረሱ የቤተ ክርስቲያንን ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ አስጠብቃለሁ ብሎ መናገር አይቻልም። ከእግዚአብሔር ይልቅ ቄሳርን ለማስደሰት የሚደረገው ሙከራ በእግዚአብሔር የሚያስጠይቅ በታሪክም የሚያስወቅስ ነው። ቤተ ክርስቲያን ጉባኤ ከለባት ብላ በምትጠራው የኬልቄዶን ጉባኤ እነ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ንጉሥ ለማስደሰት ብለው እንደ ሌሎቹ መለካውያን ቢሆኑ ኖሮ ርትዕት የሆነችው ሃይማኖት ከዘመናችን ባልደረሰች ነበር።

ቅዱስ ሲኖዶስ በያዝነው ዓመት የግንቦት ርክበ ካህናት ጉባኤው በተጓደሉ መናብርት ላይ ኤጲስ ቆጶሳትን እንዲሾሙ በመወሰን ለሢመት የሚመጥኑትን አባቶች በማፈላለግ ለጉባኤው እንዲያቀርብ ሰባት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን ያካተተ ኮሚቴ መሠየሙ ይታወቃል። ይህ ተግባርና ኃላፊነት የተጣለበት ኮሚቴ ሥራውን ሁሉ እያከናወነ ያለው በድብቅ ነው። ጥቆማዎችን የተቀበለው ከሊቃነ ጳጳሳት ብቻ ነው። የተሰጡት ጥቆማዎችን ለሕዝብ ይፋ አድርጎ አስተያየት አልተቀበለም። ተጠቋሚዎችን የሚመርጥበት መስፈርት ምን እንደሆነ በምልዓተ ጉባኤውም ሆነ በአስመራጭ ኮሚቴው ለምእመናን አልተገለጸም። ለሹመት የሚቀርቡት አባቶች በቤተ ክርስቲያን ጸንቶ በቆየው ሥርዓት መሠረት ስለ ትምህርታቸው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ስለ መንፈሳዊ ሕይወታቸውና ንጽህናቸው ደግሞ ምእመናን የመሰከሩላቸው እንዲሆኑ አልተገለጹም። ኮሚቴው ይህን በማድረጉም በመጽሐፈ ሲኖዶስ “ኤጲስ ቆጶስ ሆኖ ሊሾም የቀረበ ሰው ካለ ይህ በሀገረ ስብከቱ ሰዎች ሁሉ ስምምነት መሆን አለበት” (ሲኖዶስ፣ ገጽ ፻፵፭) ተብሎ የተሠራውን ሥርዓት ተገዳድሯል። በኮሚቴው ውስጥ ያሉ አባላት ይህን ቀኖና አያውቁትም ማለት ከባድ ነው። ቀኖና እያፈረሱ የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ማስፋት አይቻልም። ሊቃነ ጳጳሳት ሕግና ሥርዓትን ካላከበሩ ምእመናንን ለሕግና ለሥርዓት ተገዥ ሁኑ ብሎ ለማዘዝ የሚችሉበት መንፈሳዊ ልዕልና ያጣሉ። ዐዲስ ኤጲስ ቆጶስ የሚሾሙባቸው አህጉረ ስብከት ክርስቲያኖች በእኔ አውቅልሃለሁ የተሾሙባቸውን አባቶች አንቀበልም ቢሉ በግድ ሊጫንባቸው አይገባም። በተለይም የሃይማኖት ሕጸጽ፣ የምግባር ጉድለት፣ የታወቀ ነውርና ነቀፋ ያለባቸው አባቶች ቢሾሙባቸው ምእመናን አንቀበልም ማለታቸው አይቀርም። በዚህ ወቅት ቅዱስ ሲኖዶስ በግድ ተቀበሉ ሊላቸው ነው ወይስ ምርጫውን ሊከልስ?

እንዲህ ያለው ተግባር ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን መጣስ ብቻ ሳይሆን የኮሚቴውን አባላት በገንዘብ ደልለው፣ በትውውቅና በቅርርብ ተጠቅመው ወይም በኃይል አስፈራርተው ለመሾም በር እንደሚከፍት መረዳትም ይገባል። በዚህ መንገድ ሥልጣን የያዙ አባቶች መንፈስ ቅዱስ መረጠን ብለው ሊናገሩ እንደማይችሉም መረዳት ያስፈልጋል። እንዲህ ባሉት መፍቀሬ ሢመት አባቶች ላይም መንፈስ ቅዱስ እንደሚያድር ቤተ ክርስቲያን አታስተምርም። ቤተ ክርስቲያን አገልግሎቷ በግልጽ ነው። በተለይም ለአንድ ቀንና ለወራት ሳይሆን እስከ ዕድሜ ልክ ድረስ የሆነውን የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ በግልጽ አሠራር፣ በጸና ቀኖናዊ ሥርዓት አለመፈጸም ቤተ ክርስቲያንን አሳልፎ እንደ መስጠት ይቆጠራል። ያለ ቅዱስ ሲኖዶስ ዕውቅና በድብቅ ኤጲስ ቆጶስነት ተሾመናል ሲሉ የነበሩ፣ ይህን ሕገ ወጥ ሢመት ተከትሎ ለብዙ ምእመናን ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ እስርና እንግልት ምክንያት የሆኑ፣ የሊቃነ ጳጳሳት ቀራቢዎች ስለሆኑ ብቻ የተጠቆሙ፣ መደለያ በመስጠት በዕጩነት የቀረቡ አባቶች ቤተ ክርስቲያንን ሊያጠፏት እንጂ ሊያሰፏት አይችሉም።

አሁን እየተፈጸመ ያለው የምርጫ ሒደት ጥር ፲፬ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም በቤተ ክርስቲያን ላይ ለተከሠተው ታሪካዊ ስሕተት መፍትሔ የሚሆን ሳሆን ሌላ ችግር ይዞ የሚመጣ ነው። ቅዱስ ሲኖዶስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በታሪኳ አጋጥሟት የማያውቀውን ጥቁር ጠባሳ ለመፍታት የሔደበት መንገድ ማስታመምን መሠረት ያደረገ ነው። የተከሰተውን ችግር መፍታት መልካም ሆኖ ዘላቂ መፍትሔ የማያመጣ አካሔድ መጓዝ ደግሞ ከእግዚአብሔር እንደሚያጣላ፣ ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን እንደሚያስወጣ መዘንጋት የለበትም። ለተከሰተው ችግር መፍትሔው በዘላቂነት ችግሩን ሥር ነቅሎ የሚያወጣውን ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን የጠበቀ ተግባር መፈጸም ነው።

ስለሆነም በዕጩነት የቀረቡ አባቶችን ለሕዝበ ክርስቲያኑ ይፋ ማድረግ በኑፋቄ የተበከሉ ሰዎች ተመሳስለው እንዳይገቡ መፍትሔ ይሆናል። በሌላ በኩል ደግሞ ምእመናንን ለመጠበቅ ብቃት ያላቸው አባቶች ከሢመት እንዳይታለፉ ያደርጋል። ይህን ማድረግ ኮሚቴው ያለበትን ኃላፊነትና ተጠያቂነት የሚያቀልል እንጂ ሥልጣኑን የሚጋፋ አይደለም። ኮሚቴው አካሔዱን እንደ ሐበሻ መድኃኒት ምሥጢር ማድረጉ ቤተ ክርስቲያንን ለሚያፈርሱ ወገኖች መዶሻ ማቀበል መሆኑን ሊረዳው ይገባል። በመሆኑም የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ከምልመላ እስከ ሹመት ድረስ ቅርበትን፣ ዝምድናን፣ ቋንቋንና ጎሣን መሠረት ያደረገ መሆን የለበትም የሚለው የቆየው ጩኸት መታለፉ ያስከተለውን ችግር እያየን ሌላ ችግር መጨመር ግልጽ በደል መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚታዩ የጎጥ፣ የትውውቅና የመደለያ መሳሳቦች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መቆም አለባቸው። ይህ ጩኸት በአስመራጭ ኮሚቴውም በቅዱስ ሲኖዶስም   ሊደመጥ ይገባል። በመጨረሻም አስመራጭ ኮሚቴው ሒደቱን የሚከልስበት አግባብ ከሌለ ቅዱስ ሰኖዶስ ጉዳዩን በጽኑዕ ሊመረምረውና እልባት ሊያስቀምጥበት ይገባል እንላለን።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on LinkedIn
  • Share on Telegram
  • Share by Mail
https://eotc-gssu.org/a/wp-content/uploads/teshuamiwoch.jpg 1080 1920 Abenezer Mamushet https://eotc-gssu.org/a/wp-content/uploads/logo-2-1-300x74-1.png Abenezer Mamushet2023-07-03 21:33:542023-07-03 21:33:54ተሿሚዎችን ለምእመናን አለማሳወቅ የሚያስከትለው መዘዝ
Search Search

Recent Posts

  • የሦስተኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
  • የኹለተኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
  • የአንደኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
  • የመስቀል ደመራ በዓል በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ
  • ሦስተኛ ዙር የ፲፪ ክፍል ምርቃት መርሐ ግብር ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ በተገኙበት ተከናወነ።

Archives

  • April 2026
  • September 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • May 2025
  • April 2025
  • October 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • November 2022
  • October 2022
  • September 2022
  • July 2022
  • June 2022
  • April 2022
  • February 2022
  • January 2022
  • October 2021
  • September 2021
© Ethiopian Orthodox Church Global Sunday School Union | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
  • Link to Youtube
  • Link to Telegram
  • Link to TikTok
Link to: ፍኖተ-ጎርጎርዮስ Link to: ፍኖተ-ጎርጎርዮስ ፍኖተ-ጎርጎርዮስ Link to: የኤጲስ ቆጶሳት አስመራጭ ኮሚቴ ያከናወናቸው ተግባራትና ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገባቸው ጉዳዮች Link to: የኤጲስ ቆጶሳት አስመራጭ ኮሚቴ ያከናወናቸው ተግባራትና ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገባቸው ጉዳዮች የኤጲስ ቆጶሳት አስመራጭ ኮሚቴ ያከናወናቸው ተግባራትና...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top