ቅዱስ ሲኖዶስ ዘጠኝ ኢጲስ ቆጶሳትን መረጠ
ቅዱስ ሲኖዶስ ዘጠኝ ኢጲስ ቆጶሳትን መረጠ
—-
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ፤ ዛሬ ረቡዕ፣ ሰኔ 28 ቀን 2015 ዓ.ም. በአካሄደው ልዩ ስብሰባ ዘጠኝ ኢጲስ ቆጶሳትን መርጧል።
ዛሬ የተመረጡት ኢጲስ ቆጶሳት በኦሮሚያ እና በደቡብ ክልሎች፤ ተደርበው በቆዩ፣ ክፍት በሆኑ እና አንገብጋቢ ተብለው በግንቦት 2015 ዓ.ም. በነበረው የርክበ ካህናት መደበኛ ጉባኤ ስብሰባ ላይ በተለዩትና ሰባት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ያሉበት አስመራጭ ኮሚቴ በተሰየመላቸው መሠረት ነው።
ኢጲስ ቆጶሳቱ የተመረጡላቸው ሀግረ ስብከቶች ሰባቱ በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ሲሆን ሁለቱ በደቡብ ኢትዮጵያ የሚገኙ ናቸው። ከይፋዊው የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ላይ ባገኘነው መረጃ መሠረት ዝርዝራቸ፦
ለኦሮሚያ ክልል ሰባት አህጉረ ስብከት፤
1. አባ ሣህለ ማርያም ቶላ – ምዕራብ አርሲ – ሻሸመኔ ሀገረ ስብከት
2. አባ ወልደ ገብርኤል አበበ – ምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት
3. አባ ጥላሁን ወርቁ – ምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት
4. አባ ዓምደ ሚካኤል ኀይሌ – ሆሮ ጉድሩ ወለጋ – ሻምቡ ሀገረ ስብከት
5. አባ ኀይለ ማርያም ጌታቸው – ድሬዳዋ ሀገረ ስብከት
6. አባ ተክለ ሃይማኖት ገብሬ – ምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት
7. አባ እስጢፋኖስ ገብሬ – ቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት
ለደቡብ ኢትዮጵያ ሁለት አህጉረ ስብከት፤
8. አባ ክፍለ ገብርኤል ተክለ ሐዋርያት – ጌድኦ አማሮ እና ቡርጂ ልዩ ወረዳዎች ሀገረ ስብከት
9. አባ ስብሐት ለአብ ወልደ ማርያም – ዳውሮ እና ኮንታ ሀገረ ስብከት ናቸው።