ሦስተኛ ዙር የ፲፪ ክፍል ምርቃት መርሐ ግብር ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ በተገኙበት ተከናወነ።
በሰንበት ትምህርት ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት ከሙከራ ትግበራ ጀምሮ ትምህርታቸውን ለተከታተሉ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችና የዕውቅና መርሐ ግብር ተከናወነ።
የዕውቅና መርሐ ግብሩ የተከናወነው በ2015 ዓ.ም የዐሥረኛ ክፍል ምዘናን በሀገረ ስብከት ደረጃ ወስደው ለዘንድሮ የዐሥራ ኹለተኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ምዘና ለወሰዱ በአዲስ አበባና በሸገር ሀገረ ስብከት የሚገኙ አጥቢያ የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ነው።
ይህ የዕውቅና መርሐ ግብር በትላንትናው ዕለት በጠቅላይ ቤተክህነት ጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ ሲከናወን ለሦስተኛ ጊዜ ነው።በመርሐ ግብሩ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሓላፊ የሆኑት መጋቤ ሐዲስ ጸጋ ወልደ ትንሣኤ የእንኳን ደስ አላቹ መልዕክታቸውን ያስተላለፉ ሲሆን በጉባኤው የተገኙት ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ የማዕከላዊ ጎንደር ሊቀ ጳጳስ “ይህ የትምህርት መጨረሻ እንዳልሆነ እና የተማረ ትውልድ ለቅድስት ቤተክርስቲያን እንደሚያስፈልጋት” ተናግረው አባታዊ መልዕክት እና ቃለ ቡራኬ ሰጥተዋል።
በመጨረሻም ተመራቂ ተማሪዎች የምሥክር ወረቀት እንዲሁም ለደረጃ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት በመስጠት የመርሐ ግብሩ ፍጻሜ ሆኗል። የሰዋሰው ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ሰ/ት/ቤት ከሌሎች ተፈታኝ ሰ/ት/ቦእቶች የላቀ ውጤት በማስመዝገቡ የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶለታል።