መዋቅራዊ አደረጃጀት

አጭር መግለጫ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከጠቅላይ ቤተ ክህነት እስከ አጥቢያ ካሏት ሰፊ መዋቅራት መካከል አንዱ የሰ/ት/ቤቶች አገልግሎትን የሚመራው እና የሚያስተባብረው መዋቅር ነው፡፡ መዋቅሩም በየጊዜው እየተሻሻለ አሁን አገልግሎት ላይ የሚገኘው በ2006 ዓ.ም በቅዱስ ሲኖዶስ ለሦስተኛ ጊዜ የተሻሻለው የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ዓለም አቀፍ፣ ሀገረ ስብከት አቀፍ፣ ወረዳ ቤተ ክህነት አቀፍ እና አጥቢያ አቀፍ) መመሪያ መሠረት አገልግሎቱን በመምራት ላይ ይገኛል፡፡

የአጥቢያ ሰንበት ት/ቤቶች  ከልምድ፣ ከአባላት ብዛት፣ ከአደረጃጀት ግብዓት፣ ከአካባቢ እና የአገልግሎት ትኩረት አንጻር የተለያየ አቅም ላይ በመሆናቸው በአራት የመዋቅር መደብ ተለይተው እንዲዋቀሩ ተደርጓል፡፡

የሰንበት ት/ቤት ጠቅላላ ተቋማዊ አደረጀጀት ወሰን

  1. የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ
  2. የመንበረ ጵጵስና አገረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ
  3. የወረዳ / የክፍለ ከተማ ቤተክህነት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ
  4. የአጥቢያ ሰንበት ት/ቤቶች ጠቅላላ ጉባኤ

የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ

የሀገረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት አደረጃጀት

የወረዳ / ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት አደረጃጀት

የአጥቢያ ሰንበት ት/ቤቶች አደረጃጀት – ከፍተኛ ምድብ አንድ

የአጥቢያ ሰንበት ት/ቤቶች አደረጃጀት – ምድብ ኹለት

የአጥቢያ ሰንበት ት/ቤቶች አደረጃጀት – ምድብ ሦስት

የአጥቢያ ሰንበት ት/ቤቶች አደረጃጀት – ምድብ አራት