መስቀሉን ተሸክመን በእምነት እንራመድ

ለሰማያዊ ክብር እንጓዝ(2) ወደ እርሱ ዘንድ

እግዚአብሔር አብ ላከ አንድያ ልጁን(2)

እርሱ ወዶአልና እንዲሁ ዓለሙን(2)

አዝ….

ከኃጢአት ያዳንከን ደምህን አፍስሰህ(2)

የሰላም ባለቤት አምላክ አንተ ነህ(2)

አዝ…….

አንተ ነህ የሕይወት መንገድና እውነት(2)

አብቃን የኛ ጌታ ለዘለዓለም ሕይወት(2)

አዝ…….

መስቀል ቤዛችን ነው ድል መንሻ ኃይላችን(2)

ከኃጢአት በሽታ የሚፈውሰን(2)

በኃጢአት ጨለማ ተውጠን ሳለን(2)

የክርስቶስ መስቀል ብርሃን ሆነልን(2)

እንድንመስው ጌታችንን(2)

እንሸከመው ዕፀ መስቀሉን(2)

እድንሸከም ዕፀ መስቀሉን

ሰውነታችንን ማንጻት አለብን፡፡

መስቀል ተመርኲዘን ወንጌል ተጫምተን

ሃይማኖትን ሰብከን በክርስቶስ አምነን

ማን ያሸንፈናል እኛ ክርስቲያንን

ክርስቶስ አለልን።

ንግሥቲቷ ዕሌኒ በጣም የታደለች

በዕጣን ጢስ ተመርታ መስቀሉን አገኘች

መድኃኒት ስትፈልግ ኪራኮስን ይዛ

መስቀሉን አገኘች የዓለሙን ቤዛ

አዝ . . .

ሙታን ተነሥተው ያመሰገኑት

ዕፀ መስቀሉ ነው የእኛ መድኃኒት

መስቀል ምርኲዛችን ጎዳና ወንጌል

ወደ ገነት እንጂ አንሄድም ሲኦል

አዝ . . .

ንዑ ንወድሶ ለዕፀ መስቀል

የተሸከመውን የአምላክን ቃል

ንዑ ንወድሳ ለማርያም ድንግል

አክሊለ ምእመናን ምክሐ ደናግል

አዝ . . .

ኀበ ቀራንዮ  ደብረ መድኃኒት(2)

ቀራንዮ(2) ኀበ ቀራንዮ

የመስቀሉ ቃል ለኛ የእግዚአብሔር ኃይል ነው

ለማያምኑት ሞኝነት ነው

ለኛ ግን ሕይወት ነው

እንመሰክራለን ፈጣሪያችን አለ(2)

እንመነው አንካደው ፈጣሪያች ቸር ነው

እመሰክራለን ድንግል አማላጅ ናት(2)

እንመናት አንካዳት የአማኑኤል እናት ናት

መስቀል አበባ ነህ ውብ አበባ

አደይ አበባ ነሽ ውብ አበባ (2)

መስቀል አበባ ተቀብሮ ሲኖር

አደይ አበባ ሥነ ስቅለቱ

መስቀል አበባ ዕሌኒ አገኘች

አደይ አበባ ደገኛዪቱ

አዝ . . .

መስቀል አበባ ጥራጊ ሞልተው

አደይ አበባ አይሁድ በክፋት

መስቀል አበባ ጢሱ ሰገደ

አደይ አበባ መስቀል ካለበት

አዝ . . .

መስቀል አበባ ወንዙ ጅረቱ

አደይ አበባ ሸለቆው ዱሩ

መስቀል አበባ አሸብርቀው ደምቀው

አደይ አበባ ላንተ መሰከሩ

አዝ . . .

(በየነ ድንቁ)

ዕፀ መስቀል የክብር መውረሻ

ሰይጣንን ድል መንሻ

የክብር ባለቤት ፣ ዕፀ መስቀል

የተሠዋበት፣ ዕፀ መስቀል

ዕፀ መስቀሉ ነው፣ ዕፀ መስቀል

የዓለም መድኃኒት፣ ዕፀ መስቀል

አዝ…..

እንደ ዕሌኒ ንግሥት፣ ዕፀ መስቀል

ፍፁም አክብራች፣ ዕፀ መስቀል

ሁላችሁ ገሥግሡ፣ ዕፀ መስቀል

መስቀሉን ይዛችሁ፣ ዕፀ መስቀል

አዝ……

ያለ ኃያለ መስቀል፣ ዕፀ መስቀል

የሰላም አርማችን፣ ዕፀ መስቀል

ሊሸነፍ አይችልም፣ ዕፀ መስቀል

ሰይጣን ጠላታችን፣ ዕፀ መስቀል

አዝ…….

እሳተ መለኮት፣ ዕፀ መስቀል

ያላቃጠለው፣ ዕፀ መስቀል

ሰይጣን የሚያግድ፣ ዕፀ መስቀል

ዕፀ መስቀል ነው፣ ዕፀ መስቀል

አዝ……….

እንደተባረከው፣ዕፀ መስቀል

ቁስጠንጢኖስ ንጉሥ፣ ዕፀ መስቀል

በመስቀል ብርሃን፣ ዕፀ መስቀል

ወደ እውነት እገሥግሥ፣ ዕፀ መስቀል

አዝ……

የተዋሕዶ ልጆች፣ ዕፀ መስቀል

ገሥግሡ በተስፋ፣ ዕፀ መስቀል

ዕፀ መስቀሉን ያዙ፣ ዕፀ መስቀል

ጠላት እዲጠፋ፣ ዕፀ መስቀል

አዝ…..

(በየነ ድንቁ)

ወሪዶ እመስቀሉ (2)

እመስቀሉ አብርሃ ለኩሉ(2)

(ቅዱስ ያሬድ)

ከመ ትባርከነ በመስቀልከ ዘወርቅ(2)

ተዋነይ በጽድቅ(4)

(. . .) ሐመልማለ ወርቅ

(ሢራክ ታደሰ)

በመስቀልከ ርድአነ (2)

ወበኃይልከ ተማኅፀነ(2)

(ቅዱስ ያሬድ)

ይትቀደስ ስምከ በኃይለ መስቀልከ በዕፀ መስቀልከ

ክቡር ዘአዕበይኮ ለስምከ (2)

ስብሐት ለከ ለባሕቲትከ ልዑል(4)

(ቅዱስ ያሬድ)

ዕሌኒ ንግሥት ኃሠሠት መስቀሎ (2)

ዕንባቆም ነቢይ ዘአንከረ ግብሮ (2)

(ቅዱስ ያሬድ)

መስቀል ብርሃን ለኩሉ ዓለም(2)

መሠረተ(3) ቤተክርስቲያን(2)

(ቅዱስ ያሬድ)

ዮምሰ ለእሊአየ (2)

አበርህ በመስቀልየ (4)

መስቀል ኃይልነ መስቀል ፅንዕነ መስቀል ቤዛነ (2)

መድኃኒትነ ለእለ አመነ(4)

ጸጋ ነሣእነ ወሕይወተ ረከበነ

በኃይለ መስቀሉ ለኢየሱስ ክርስቶስ በኃይለ መስቀሉ(2)

ኪያከ እግዚኦ ነአኩት

ወንሴብሐከ እግዚአብሔር(2)

(ቅዱስ ያሬድ)

ጥልን በመስቀሉ ገደለ

በመስቀሉ ለሰው ልጅ ሰላም አደለ (2)

ለዕፀ መስቀሉ እናቅርብ ምስጋና(2)

ክርስቶስ በደሙ ቀድሶታልና(2)

ጎልጎታ ሲኖር ዓፈር ተንተርሶ(2)

ይኸው ተገኘልን በዕሌኒ ልቅሶ(2)

አጋንንት አይቀርቡም ከሩቅ ይሸሻሉ(2)

እኛ ስንባረከ በዕፀ መስቀሉ(2)

አዝ………

ክርስቶስ በደሙ የቀደሰው መስቀል(2)

ድል መንሻ ሆነልን የሰይጣናትን ኃይል(2)

በመስቀል ተሰቅሎ ደሙ ባይሆነን ቤዛ(2)

ወድቆ ይቀር ነበር አዳም እንደዋዛ(2)

አዝ…..

ብርሃን ነው ለዓለም የጌታ መስቀል

የድሆች መጽናኛ የደካሞች ኃይል

አይሁድ ይክዱታል የጌታን መስቀል

ለሚያምኑት ድኅነት ነው የሚሆነን  ኃይል

አዝ…….

አምነው ለተጠጉት ለተከተሉት(2)

መስቀሉ ፈውስ ነው ይሆናል ድኅነት

የዲያብሎስን ኃይል የምንመክትበት

መስቀል ነው ቤዛች ዓለም የዳነበት

አዝ……

(ብርሃኑ ውድነህ)

ዘዕጣን አንፀረ(2)

በጎልጎታ ተረክበ ዕፀ መስቀል(2)

(አርያም፣ ቅዳሴ ያሬድ)

ይቤሎሙ ኢየሱስ

ለአይሁድ እመኑ ብየ

ወእመኑ በአቡየ

አበርህ (2) በመስቀልየ

(ቅዱስ ያሬድ)

ኃይልነ ወፀወንነ ወሞገስነ (2)

ዝንቱ ውእቱ መስቀል (4)

(ቅዱስ ያሬድ)

አለው አለው ሞገስ . . . ኧኸ አለው ሞገስ (2)

የመስቀል በዓል ሲደርስ . . . ኧኸ አለው ሞገስ

አለው አለው ሞገስ . . . ኧኸ አለው ሞገስ

አለው አለው አበባ . . . ኧኸ አለው አበባ (2)

የመስቀል በዓል ሲገባ . . . ኧኸ አለው አበባ

አለው አለው አበባ . . . ኧኸ አለው አበባ

አለው አለው ደስታ . . . ኧኸ አለው ደስታ (2)

መስቀል ሲከብር በዕልልታ . . . ኧኸ አለው ደስታ

አለው አለው ደስታ . . . ኧኸ አለው ደስታ

አለው አለው ሰላም . . . ኧኸ አለው ሰላም (2)

መስቀል ሲታይ በዓለም . . . ኧኸ አለው ሰላም

አለው አለው ሰላም . . . ኧኸ አለው ሰላም

አለን አለን አለኝታ . . . ኧኸ አለን አለኝታ (2)

ዕፀ መስቀል መከታ . . . ኧኸ አለን አለኝታ

አለን አለን አለኝታ . . . ኧኸ አለን አለኝታ

እዩት እዩት ሲያበራ . . . ኧኸ እዩት ሲያበራ (2)

የመስቀል በዓል ደመራ . . . ኧኸ እዩት ሲያበራ

እዩት እዩት ሲያበራ . . . ኧኸ እዩት ሲያበራ

እዩት እዩት ሲያምር . . . ኧኸ እዩት ሲያምር (2)

መስቀል በዓለም ሲከብር . . . ኧኸ እዩት ሲያምር

እዩት እዩት ሲያምር . . . ኧኸ እዩት ሲያምር

(ተምሮ ማስተማር)

መስከረም ጠባ ኢዮሃ አበባ (2)

መስከረም ጠባ አዮሃ አበባ ኢዮ

መስከረም ጠባ ለኛ ኢዮሃ አበባ

መስቀል አበራ ኢዮሃ አበባ

ለእኛ እንዲሆነን ዕድገት እና ልማት

ኢዮ(2) አበባዬ ኢዮ

መስረም ጠባ ለእኛ ኢዮሃ አበባ

በተዋሕዶ የከበረች የእናታችንን

የጥበብ ልጆችዋ እናከብታለን

ሃይማኖት ከምግባር ወንጌል መግባ ስላሳደገችን

የድኅነት መሠረት ቤተክርስቲያን እናታችን

ጥንትም መሪና አስተማሪ በመሆንዋ

በዓለም ላይ ታውቋል ዜናዋ

እየተወሳ በዓለም ዜና ያኮራናል መስቀላችን

ኢዮሃ አበባ መስከረም ጠባ

ኢዮሃ አበባዬ(3)

(አብርሃም መኮንን)

ልዑል እግዚአብሔር(2) ምስጋና ይገባሃል(2)

ለመስቀል በዓል (2) በሰላም በጤና ያደረስከን (2)

መስቀሉሰ ለክርስቶስ ብርሃን ለእለ ነአምን ትብል  ቤተክርስቲያን (2)

ዛኅኑ ለባሕር ወመርሶ ለአህማር ዝንቱ ውእቱ መስቀል (2)

(ቅዱስ ያሬድ)

ኀበሩ ቃለ ኅበሩ ቃለ ነቢያት (2)

ወይቤሉ መስቀል ብርሃን(2) ለኩሉ ዓለም (2)

(ቅዱስ ያሬድ)

ዮም በዓለ መስቀሉ በሰማያት በላዕሉ (2)

ወዘነግሠ በምድር (2) ለአሕዛብ (2)

(ቅዱስ ያሬድ)

እንተ ተሐንፀት በስሙ ወተቀደሰት በደሙ ቤተክርስቲያን(2)

ወተአትበት(2)  በዕፀ መስቀሉ

እስመ ኃይለ እግዚአብሔር ላዕሌሃ (2)

(ቅዱስ ያሬድ)

ኧኸ በመስቀልከ ኧኸ  ጽልመተ አብራህከ (2)

ኧኸ በመስቀልከ ኧኸ ሙታን አንሣእከ

ኧኸ ወዘተኀጕለ ረዳእከ በመስቀልከ (2) 

(ቅዱስ ያሬድ)

ርዕዩ እበዮ ለዕፀ መስቀል(2)

ዘመጠነዝ (2) ትርሲተ ክብር ትሕትና ወፍቅር (2)

ርዕዩ እበዮ ለቅዱስ ዕፀ መስቀል(2)

እውራን ይሬእዩ ወፅሙማን ይሰምኡ

እለ ለምጽ ይነፅኡ እለ መጽኡ አቤሁ

ትርጉም . . .

ኑ እዩ የመስቀሉን ተአምራት

የማያዩ ያያሉ የማይሰሙ ይሰማሉ

ሕሙማን ይድናሉ ወደሱ ይቀርባሉ

መስቀል አብርሃ በከዋክብት አሠርገወ ኢትዮጵያ(2)

እምኩሉሰ ፀሐየ አርአየ እግዚአብሔር (2)

(ቅዱስ ያሬድ)

መስቀል ብርሃን ለኩሉ ዓለም መሠረተ ቤተክርስቲያን

ወኀቤ ሰላም መድኃኔዓለም መስቀል መድኅን ለእለ ነአምን

ሐነፅዋ ለቤተክርስቲያን ወሣረርዋ በመንፈስ ቅዱስ/፪/
እንተ ተሐንፀት በእደ ካህናት ወተቀደሰት በአፈ ጳጳሳት
ወተጠምቀት በማይ ዘውኅዘ አምገቦብ አመ ሕማማቲሁ/፪/

(ቅዱስ ያሬድ)

ተስኢነነ ዘወንጌለ ቃለ (2)

ኅቡረ ተመርጒዘነ መስቀለ (2)