በጌቴ ሴማኔ በአትክልቱ ቦታ(2)

ለኛ ሲል ጌታችን በዓለም ተንገላታ(2)

አዳምና ሔዋን ባጠፉት ጥፋት(2)

እኛም ነበረብን የዘለዓለም ሞት(2)

ድንግል አልቻለችም ዕንባዋን ልትገታ(2)

እያየች በመስቀል ልጇ ሲንገላታ(2)

መስቀል ተሸክሞ ሲወጣ ተራራ(2)

ይገርፉት ነበረ ሁሉም በየተራ(2)

በአምላክነቱ ሳይፈርድባቸው(2)

እንዲህ ሲል ጸለየ አባት ሆይ ማራቸው(2)

ተጠማሁ፣ተጠማሁ፣ተጠማሁ፣ ሲላቸው(2)

ሆምጣጤ አመጡለት በሰፍነጉ ሞልተው(2)

በረቂቅ ጥበቡ ሁሉን የፈጠረ(2)

በሰዎች ተገርፎ ሞቶ ተቀበረ(2)

(ሢራክ ታደሰ)

ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ አባት ለኛ ተንገላታ

ባምስቱ ቅንዋት እጅ እግሩ ተመታ

አዳምና ሔዋን የመጡትን ዕዳ

በመስቀል ሰባብሮ አዳነን ከፍዳ

የጠላትን ቀንበር በመስቀል ሰባብሮ

ነፃ አወጣን ጌታ ሞትን በሞት ሽሮ

አዝ……

ነውር የሌለበት ንጹሕ ቅዱስ ሲሆን

ደሙን አፈሰሰሰ ለኛ ቤዛ ሊሆን

አዝ…..

ተጠማሁ እያለ እሱ በመስቀል ላይ

እንኩ ጠጡ ብሎ ደሙን ለእኛ ሰጠን ኃጢአት ለማስተሰረይ

አዝ….

መካነ ምሥጢራት አንቺ ጎልጎታ

ወድቆ ተነሣብሳብሽ የዓለሙ ጌታ

አዝ…..

(ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል)

  ቸሩ ሆይ(2) ለእኛ ብለህ ተሰቀልክ ወይ

ሔዋን ብትበድል እንዲህ እንደዋዛ(2)

መጣ ተሰቀለ የዓለሙ ቤዛ(2)

አዝ…..

የተከሰሰበት ወንጀሉ ቢወራ(2)

ለምጽ ስላነጻዕውር ስላበራ(2)

አዝ……

አንካሳን ማዳኑ ማቅናት ጎባጣውን(2)

ለፍርድ አቀረቡት እውነት የሠራውን(2)

ባህልን ለውጧል ሰንበትንም ሽሯል(2)

ይህ በደለኛ ነው መሞት ይገባዋል(2)

አዝ…..

ብለው ስለአወጁ ባንድነት ሁሉም

ለእኛ ተሰቀለ መድኃኔዓለም

አዝ…

(ሲራክ ታደሰ)

ሙታንን ያድን ዘንድ የሞት ሞትን ሽሮ(2)

ወልደ አምላክ ሄደ ወደ ኋላ ታሥሮ(2)

ምን በበደለ ነው ምን ባደረገ ነው(2)

ወልድ እንደ ቀማኛ ሲገረፍ የዋለው(2)

ቅዱሳን እጆቹ አዳምን የሠሩት(2)

ቅዱሳን እግሮቹ በገነት የዙሩት(2)

ተቸንክረው ዋሉ በጠንካረው ብረት(2)

ግርማን ለኪሩቤል ያጎናጸፋቸው

ዘውድን ለሱራፌል የሚያቀዳጃቸው

ከለሜዳ ለብሶ ዋለ ከፊታቸው(2)

ሔዋን በፈጸመችው የበደልን ሥራ

አዳም በፈጸመች የበደልን ሥራ

ቸሩ ወልደ አምላክ ዋለ በመከራ(2)

ጌታ በፈቃዱ አጁን ቢሰጣቸው(2)

ተዘባበቱበት የሾህ አክሊል ደፍተው(2)

ትንሹም ትልቁም ሲዘባቱብህ(2)

ዋ ምን ይደንቃል ታላቁ ትዕግስትህ

             (ታዕካ ነገሥት በዓታ ሰንበት ት/ቤት)

የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም ቤዛ

ወገኖቹን ሁሉ በራሱ ደም ገዛ

የሐሰት ምስክር አቁመው ከሰሱት

በሞት እንዲቀጣ ሁሉም ፈረዱበት

ጲላጦስ ገረፈው በሰንሰለት አስሮ

በአይሁድ መካከል እንዲኖር ተከብሮ

ድንግል አልቻለችም ዕንባዋን ልትገታ

እያየች በመስቀል ልጇ ሲንገላታ

በብርሃን ዙፋን ላይ የቆሙት እግሮቹ

በችካር ላይ ቆሙ ምንም አልሰለቹ

የብርሃን አክሊልን ለሰማዕት ያደለ

የሾህ አክል ደፍቶ ቀራንዮ ዋለ

(መዝሙረ ስብሐት)

ሞተሃና ስለኔ ምንም ሳይኖርብህ ጥፋት

በሐሰት ተከሰህ በጲላጦስ ፊት

ኢየሱስ አምላከ ምሕረት ስብሐት ለከ

ያንተ መንገላታት ሁል ጊዜ ያሳዝናል ሲወራ

በመስቀል ላይ ስለ እኛ ያየኸው መከራ

ኢየሱስ የሕይወት እንጀራ ስብሐት ለከ

ከልዑል ቦታ ዝቅ ብለህ ፈጣሬ ፍጡራን አምላክ

በመስቀል ተሰቅለህ ስለሰው የሞትክ

በመስቀል ላይ ተጠማሁ እያልክ ስብሐት ለከ

ክፉ አድራጊዎች ተነሥተው በምቀኝነት መንፈስ

ብዙ ሲጣጣሩ ለደምህ መፍሰስ ስብሐት ለከ

መሐሪ ጌታ አሁንም እንደ ቸርነትህ ብዛት

የኛን በደል ሁሉ ሳትመለከት

አድነን ከዳግም ሞት ስብሐት ለከ

(ሢራክ ታደሰ)

አምላክ ሆይ ወደኛ ባትመጣ ለብሰህ የማርያምን ሥጋ(2)

ባክኖ የኖረው የአዳ ዘር ውጤቱ ነበር የሚያሰጋ(2)

በዚያች ዓመት በዚያች ወር በዚያች ቀን

ድህነትን ለሰው ልጅ ስትሰጥ(2)

ምን ይበዛ ነበር ትሕትናህ፣ ትዕግሥትህ የማይለወጥ(2)

የሾህ አክል ደፍተህ በራስህ ጎንህን ሲወጉህ በጦር(2)

አንተ ግን ለነረሱ ካባትህ ምሕረትን ስትጸልይ ነበር(2)

ግን መቼ አወቁት እነርሱ በኃጢአት ደንድኖ ልባቸው(2)

መድኃኒታቸውን ገረፉህ ሰቀሉህ አንተም ሞትክላቸው(2)

ዳግም ስትመጣ ለፍርድ ከዓለም ፍጻሜ በኋላ(2)

እንዴት ዕድለኞች ናቸው ካንተ የሚያኙት ተድላ(2)

በዚያች በደብረ ዘይት ቦታ  ደስታን ለቅሶ ሲፈልቅ(2)

ከቶ ወዴት ይሆን ዕድሌ ያንጊዜ የኔ አወዳደቅ(2)

የፀፀጽ ሮሮ በፊትህ እንዳያቃጥለኝ እኔን(2)

እርዳኝ ፈጣሪዬ ካሁኑ አንጻው የዛገው ልቤን(2)

                             (የሺህ እመቤት)

ወአንቲኒ ቀራንዮ መካነ ጎልጎታ(2)

እስመ በኃቤኪ(2) ተሰቅለ መድኃኔዓለም

(ቅዱስ ያሬድ)

አልፋና ዖሜጋ ፈጣሪ የሆንክ

በከሐዲዎች እጅ ተይዘህ ቀረብክ

ተገረፍህ ተሰቅለህ በጥፊ ተመታህ

እየደበደቡ ተዘባበቱብህ

ጽድቅን ስለሠራህ በወንጀል ከሰሱህ

ለአዳም ቤዛ ብለህ ብዙ ተንገላታህ

አዝ….

ቅዱሳን እችህ የፍጥኝ አሥረው

ሲገርፉህ ክፉዎች ይቀር አልካቸው

የሁሉ ፈጣሪ ሁሉን የምታውቅ

ዘበቱብህ መቱህ ሸፍነው በጨርቅ

አዝ….

በዚህ አደባባይ ከጲላጦስ ዘንድ

አሳልፈው ሰጡህ ጨካኞች ለፍርድ

ከሐና ቀያፋ ከካህናት ደጅ

ከነሄሮድስ ዘንድ አቀረቡህ በአዋጅ

አዝ….

ግርፋት ሕመሙ አልበቃ ብሎህ

መስቀል ላይ ልትውል ተፈረደብህ

ሣዶር እና አላዶር ዳናትና አዴራ

ተፈልገው መጡ ለችካር በተራ

አምስን ችንካሮች ቅንዋተ መስቀል

አይሁድ አመጡ ሥጋህን ለማቁሰል

አዝ…..

የሰላም ባለቤት አካልህ ተወጋ

ሊወጋ በችንካር እጅህ ተዘረጋ

ግፈኞች አይደሁድ በአንተ ላይ ቀለዱ

ምራቅን ተፉብሕ አንተን ሊጎዱ

አዝ….  (በየነ ድንቁ፣ ዜማ ኪነ ጥበብ)

ዘጠኝ ሠዓት ሲሆን ጌታ ሆይ በመስቀል ሆነህ ጌታ ሆይ

ድምፅን በማሰማት ጌታ ሆይ ነፍስህን ሰጠህ ጌታ ሆይ

አዝ…

የሰማይ ከዋክብት በሙሉ አዘኑ

ጨረቃና ፀሐይ ምስክሮች ሆኑ

ብርሃናት ጨለሙ ጠፍተው ተለያዩ

ሥጋህ በመስቀል ተገልጦ ስላዩ

አዝ……

ጌታችን ክርስቶሽ በመስቀል ላይ ሳለ

አሰምቶ ጮኸ ተጠማሁ እያለ

ማርና ወተትን ለሚመግበው

ሐሞት አመጡለት ቅመሰው ብለው

አዝ…..

ቀኝ ጎኑ ሲወጋ ውሃና ደም ፈሰሰ

በምድር ተረጭቶ ዓለሙን ቀደሰ

የእስራኤል ልጆች ዋይ ዋይ ሲሉልህ

ለእነርሱ አዘንክ እንጂ ለራስህ አላሰብህ

አዝ….

እናትህ ስታለቅስ በመስቀል ሥር ሆና

ዮሐንስን ሰጠሃት ጠብቆ እንዲጽናና

መላእክት ታዩ አጋንንትም ሸሹ

የአይሁድ ሠራዊት ፈርተው ተረበሹ

አዝ….

(በኅብረት)

ዘጠኝ ሠዓት ሲሆን ጌታ ሆይ በመስቀል ሆነህ ጌታ ሆይ

ድምፅን በማሰማት ጌታ ሆይ ነፍስህን ሰጠህ ጌታ ሆይ

(በየነ ድንቁ፣ ዜማ ኪነ ጥበብ)

ምድረ ቀራንዮ ምድረ ጎልጎታ

የዓለም መድኃኒት ባንቺ ተንገላታ

መስክሪ አንቺ ምድር ግኡዚቷ ስፍራ

መድኃኒት ክርስቶስ ያየብሽ መከራ

ሁሉን ማድረግ ሲችል ሥልጣን ሲኖረው

የመስቀል ኃፍረት ፍጹም ታገሠው፣

አዝ…..

እጆቹና እግሮቹን በችንካር ለመታው

ይቅርታ አደረገ ለበደለው ሰው

በመስቀል ላይ ሆኖ ተጠማሁኝ እያለ

ለቤዛ ዓለሙ ቀራንዮ ዋለ

አዝ……

ደሙ እንደ ውሀ ሲወርድ በመስቀሉ ላይ

መከራን ሲቀበል ኃያሉ አዶናይ

መከራ በተራ ሲፈራረቅበት

በደል አልተገኘም ከሱ አንደበት

አዝ…..

ከሰማያት ወርዶ እንዲህ መዋረዱ

ለኛ ሲል ነውኮ ሰውን በመውደዱ

ቸሩ መድኃኔዓለም እባክህ ማረኝ

ኃጢአቴንም አይተህ አንተ ይቅር በለኝ

አዝ……

(በየነ ድንቁ)

ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት(2)

ወሰላም በመድር ሥምረቱ ለሰብእ ሃሌ ሉያ

ሃሌ ሉያ(3) አሜን ሃሌ ሉያ

(ቅዱስ ያሬድ)

መድኃኔዓለም ዘቆምክ በቅደመ ጲላጦስ

መድኃኔዓለም ዘቆምከ በዓውደ ሄሮድስ

ቀራንዮ(2) በዚያ ቦታ

ቀራንዮ(3) ምድረ ጎልጎታ

እጅ እግርህ ታሥረህ በራስህ ፈቃድ

ተገፋህ ተንገላታህ በእደ አይሁድ

ለሸክም ዳረጉህ ለማይቻል ግንድ

አዝ…

እናትህ ስታለቅስ ስለ አንተ መከራ

በቀኖት ሲወጉህ ደምህም ሲዘራ

የራሔልም ልቅሶ በነርሱ ደረሰ

ኀዘን ተሰማቸው ዕንባቸው ፈሰሰ

አዝ….

አይሁድ ባሰባቸው ያዛቸው ጭካኔ

ምራቅን ተፉበት ገረፉት ወይኔ

ዳዊት በገናውን እየደረደረ

አገቱኒ ብሎ ትንቢት ተናገረ

አዝ……(በየነ ድንቁ)

እስመ ለዓለም ምሕረቱ(4)

አያልቅም ብዙ ነው የአምላክ ቸርነቱ(2)

አመሰገኑት ጌታን ሁላችሁ በአንድነት(2)

መሐሪ ነውና ለሰው ልጆች ሕይወት

አዝ…..

የማይሞተው ሞቶ የተቀበረው(2)

በእሳተ ገሃነም እኛን ሊያድን ነው(2)

አዝ….

ከማርያም የነሣው ያ ቅዱስ ሥጋው(2)

በመስቀል ላይ ሲውል የሚያሳዝነው ነው(2)

አዝ……

በፈጠረው ፍጥረት ለሕማም ተሰጥቶ

ነፍሳትን አወጣ ከሲኦል ጎትቶ(2)

አዝ…መ…(ተምሮ ማስተማር)

ፍቅር ሰሐቦ ለወልድ ኃያል እመንበሩ(2)

ወአብጽሖ(3) እስከ ለሞት(2)

አምላክ ለኛ ብሎ ቢያፈሰው ደሙን

ለምን ከለከለች ፀሐይ ብሃኗን

አንቺ ዕለተ ዓርብ ከሁሉ በለጥሽ

ለማያልቀው ሥጋ ገበያ ሁነሽ

ከማያለውቀው ሥጋ ሰዎቹ ቢበሉ

ገነት ገብተው ቀሩ ሳይከለከሉ

የከበረው ሥጋ የከበረው ደም

በመስቀል ላይ ዋለ ኢየሩሳሌም

በሥጋችን ሐኪም ዓለም ተታለለ

ነፍስን የሚያድናት ደጉ ሐኪም ሳለ

ይኸው ደጉ ሐኪም የማይፈልግ ዋጋ

ነፍሥንም ሥጋን ያድናል ካደጋ

መዳን የምትፈልግ ላሳይህ ቤቱን

በሰላም ጠይቃት ቤተ ክርስቲያንን

(ዶ/ር ኢሳይያስ ዓለሜ)

የሾህ አክሊል ጉንጉን ደፍተው በራሱ ላይ

ብለው ዘበቱበት የአይሁድ ንጉሥ ሆይ

በጉልበታቸውም ተንበርከኩና

ሰላም ለአንተ ይሁን አሉት አፌዙና

ራሳቸውንም እየነቀነቁ

መንገደኞች ሁሉ በጌታ ላይ ሳቁ

አወይ ሌለውን ሰው ያድን የነበረው

ምነዋ ራሱን ሳያድን የቀረው

እያሉ ሲነቅፉት በእርሱ ያላመኑ(2)

ምልክት ከሰማይ ታየ ወዲያዉኑ(2)

ፀሐይም ጨለመ ደም ሆነች ጨረቃ(2)

ከዋክብት ረገፉ ዓለት ሁሉ ነቃ(2)

የመቅደሱ ግርዶሽ ከሁለት ሲቀደድ(2)

የሞቱት ተነሡ ከመቃብር ጉድጓድ(2)

አለኝታችን(2) ይሁን ፈጣሪያች(2)

እሱ ስለሆነ(4) የሕይወት ተስፋች(2)

ኢየሱስ ክርስቶስ ተሰቅሎ(2) በቅዱስ መስቀሉ(2)

ፍጹም ሰላም ሆነ (4) ለአዳም ልጅ ሁሉ(2)

ለምታለፍው ዓለም (2) በጨነቅ ይቅርብን(2)

ተስፋችንም ሁሉ (4) በክርስቶስ ይሁን(2)

(ብርሃኑ ውድነህ)

ፈያታዊ ዘየማን መኑ መሀረከ

ወመኑ ነገረከ ታእምር ዘንተ

ነቢያተ ኢሐተትኩ ወሐዋርያተ ኢተሎኩ

አላ ፀሐይ ቀፀበተኒ ሶበ ርኢኩ አመንኩ

ኃይለ መስቀሉ መድኃኒተ ኮነኒ

* * *

መድኃኒቴ አንተነህ ጠባቂ እረኛዬ(2)

በመስቀልህ ምራኝ አቤቱ ጌታዬ(2)

በመስቀል ከአንተ ጋር አብሮ የነበረው(2)

ገነትን ወረሰ እሱ እንደተመኘው(2)

ነቢያትም ሆኑ ደግሞም ሐዋርያት(2)

ያተን መስቀል ቀድመው ሳይሰብኩት(2)

በመንግሥትህ ጌታ አስበኝ እያለ(2)

ወዳንተ ጸለየ በመስቀል ላይ ሳለ(2)

ወዳንተ ለመነ ምንም ሳይሰለች(2)

የእርሱም ሐዋርያ ፀሐይ ነበረች(2)

ፀሐይም ያን ጊዜ ፈጥና ጠቀሰችው(2)

የገነት ማኅተም ወዲያው ተሰጠችው(2)

(ቅዱስ ያሬድ፣ መዝሙረ ስብሐት)

ተፈጸመ አለ ጌታ ነፍሱን ሰጠ

ስለኔ ኃጢአት በመከራ አለፈ

ደፋ ቀና እያለ ሲወርድ ሲንገለታ

ያ ብርሃን ፊቱ በጥፊ ተመታ

አዝ……

በሐሰት ተከሶ በሐሰት ተገደለ

በውርደት ሸንጎ ፊት ባደባባይ ዋለ

በውሀ ጥም ዛለ በረሀብ ተቀጣ

ስለ ሰው ልጆች ሲል የሞት ጽዋን ጠጣ

አዝ….

አንቺ ዕለተ ዓርብ እንዴት ያለሽው ነሽ

ሰማያዊ አባት የተሰቀለብሽ

ከኋላ ከፊቱ በጠላት ተከሶ

ማንም አልነበረም የሚያናናው ከቶ

አዝ…..

ርኁሩኅ ጌታዬ ስኔ ብለህ ነው(2)

ያንን ሁሉ መከራ በትዕግሥት ያለፍከው

አዝ…..         (ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል)